>

"አዲስ አበባ በአዲስ አበባውያን ትተዳደር ማለት ወንጀል አይደለም"  (ጠበቃ አለልኝ ምህረቱ)

“አዲስ አበባ በአዲስ አበባውያን ትተዳደር ማለት ወንጀል አይደለም” 
ጠበቃ አለልኝ ምህረቱ
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አለም አቀፉ ድርጅት አምነስቲ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹንና ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉና ጓደኛው ሚካኤል መላክ ሐሳባቸውን በነፃ በመግለፃቸው ሊታሰሩ አይገባም፤ እንዲለቀቁም በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።
ሔኖክ አክሊሉና ጓደኛው ሚካኤል መላክ “አዲስ አበባ እንደ ሌሎች ክልሎች በራሷ አስተዳደር ልትተዳደር ይገባል ማለታቸውና ከፍልስጥኤም ቆንሱላ ስልጠና ወስዳችኋል በሚል” ለእስር እንደበቁ አትቷል።
“የሔኖክና የሚካኤል መታሰር የኢትዮጵያ መንግሥት የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ቃል በገባባበት ማግስት መፈጠሩ አሁንም ቢሆን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የሚገጥማቸው ችግር እንዳልተቀረፈ ነው” ይላል።
ሐሳባውን በነፃ መግለፃቸውም ሆነ ማህበር መፍጠራቸው ሊያሳስራቸው እንደማይገባ በመግለጫው ተጠቅሷል።
በተለያየ ጊዜ በሽብር ለተከሰሱ ሰዎች በጠበቃነት በመቆም የሚታወቀው ሔኖክ አክሊሉና ጓደኛው ሚካኤል መላክ ረቡዕ ምሽት ላይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን በትናንትናውም ዕለት ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
ሔኖክና አብሮት የታሰረው ጓደኛው አቶ ሚካኤል ትናንትና ፍርድ ቤት ቀርበው የነበረ ሲሆን ፖሊስ አዲስ አበባን ከአዲስ አበባዊ ውጭ ሊያስተዳደር አይገባም በሚል እምነት የአዲስ አበባን ወጣት በማደራጀትና ከፍልስጤም ኤምባሲ ጋር ግንኙነት በመፍጠር ጠርጥሬአቸዋለሁ ብሏል።
በትናንትናው ዕለት ለአቶ ሔኖክ ሶስት ጠበቆች ቆመው የነበረ ሲሆን አንደኛው ጠበቃ አቶ አለልኝ ምህረቱ ለቢቢሲ እንደተናገሩት
” ሀሳባችሁን ስትገልፁ ህዝብ እርስ በርሱ እንዲጠራጠርና ሌሎች ላይ ስጋት እንዲፈጠር አድርጋችኋል፤ አዲስ አበባ ላይ ጥርጣሬ እንዲፈጠር አድርጋችኋል” በሚል እንደሆነ ጠቅሰው ጨምረውም
“አዲስ አበባ በአዲስ አበባውያን ትተዳደራለች ማለት መብትም ነው፤ በሌላ በኩል አዲስ አበባ የራሷ የአስተዳደር እርከንም ያላት ነው። ይህን ማለት ወንጀል አይደለም፤ ወንጀልም ሆነ እንዴት እንደቀረበ አናውቅም”
ይህ ሀሳብን መግለፅ ወንጀል አይደለም የሚሉት ጠበቃው በመጨረሻ በማን እንደምትተዳር የሚወስነው ህዝብ ነው።
የጠበቃ ሄኖክና ጓደኛው አቶ ሚካኤል መላኩ ቀጣይ ቀጠሮ ጥቅምት 15 ነው።
ምንጭ – ቢቢሲ አማርኛ
Filed in: Amharic