አሰፉ ሀይሉ
* “ነገርን ሁሉ የሚያከብረውም፤ የሚያስከብረውም ‹የእኛ ፡ የሰዎች ፡ የጋራ ፡ ስም ምነት ፡ የመሆኑ ፡ የነጠረ ፡ እውነት› ነው!!”
ይህ የዓለማችን ታዋቂ የአልማዝ ፈርጦች አቅራቢ የ ʿዳ-ቢርስʾ (Da Beers) ሊቀመንበር ኒኪ ኦፕንሄይመር ‹‹ The Independent›› በተሰኘው ጋዜጣ እ.ኤ.አ. በፌብሯሪ 13፤ 1999 ዓም. ላይ ስለአልማዝ ቀለበቶች ያሰፈረው አስተያየት ነበር፡፡
መጀመሪያ ላይ… ‹‹እንዴ!! ሰውየው አዕምሮውን ስቷል እንዴ?!!›› ብዬ አሰብኩ፡፡ ለአንዲት ‹‹ሽንብራ›› የምታህል የአልማዝ ፈርጥ እኮ ሙሽሮች በርካታ ሺኅ እና ሚሊዮኖች ዶላሮችን ሊከሰክሱ ይችላሉʿኮ….! (‹መከስከስ!› ስል ልክ እኔ ግንባሬን እንደምከሰክሰው ማለት ሳይሆን ‹እጅ-በጅ›› ብሩን ዱብ ያደርጋሉ ማለትʿኮ ነው!!)
‹‹ታዲያ ኦፕንሄይመር ምን ነክቶት ነው የአልማዝን ተፈጥሯዊ ዋጋ ‹‹ዜሮ!!›› ያስገባው…??›› ብዬ ሳስብ… አንድ ሃሳብ በአይኔ ላይ ‹‹ብልጭ!›› አለብኝ!! ለካ እውነቱን ነው… አልማዝ ድንጋይ ነበር፡፡ በራሱ ተፈጥሮ ምንም ዋጋ የማያወጣ ከመሬት ተቆፍሮ የሚገኝ የድንጋይ ከሰል ነበር፡፡ ከመሬት አፈር ተከስክሶ የሚወጣ ድንጋይ ነው አልማዝ ፡፡
ይህ ድንጋይ ውድ ዋጋ እንዲያወጣ፤በጥቂት ሰው እጅ ብቻ እንዲገኝ ፣ ብርቅዬ እንዲሆን ያደረገው … የሰውልጅ ስምምነት ነው፡፡ አዎ!!!
ለምሣሌ ወርቅን እንውሰድ፤ ወርቅ simply ብረት ቢሆንም ውድና ብርቅዬ ጌጥ ነው፤ ለዚህም ውድ ዋጋ ይቸረዋል። አልማዝም ተራ የከርሰ-ምድር ከሰል ቢሆንም … ግን … “እጅግ የከበረ ዋጋ ይሰጠው”… “በጥቂቶችም እጅ ብቻ ይገኝ” ብሎ የሰው ልጅ ስለተስማማ ነው!!! እኛ ባንስማማ ኖሮ… በቃ… ወርቅም ተራ ብረት፤ የአልማዝ ፈርጦችም ተራ ባልጩት-ድንጋዮች ሆነው ይቀሩ ነበር!!!
ይህ እውነት ለብር ቅጠሎችም ያገለገለ እውነት ነው። ‹ዶላር› ወይም ‹ብር› ዋጋ እንዲኖራቸው የሚያደርገው… የዜጎች ወይም የሚገበያዩ ሰዎች ስምምነት ነው፡፡ ሰዎች ካልተቀበሏቸው፣ ሰዎች ባይስማሙና ዋጋ ባይሰጧቸው ኖሮ ግን… ዶላርና ብር …ተራ ቁራጭ-ወረቀቶች ሆነው ይቀሩ ነበር!!
ከዚህ ሃቅ ነጥሮ የሚፈነጥቅልን ታላቅ እውነት ምንድነው? ታላቁ እውነት ይህ ነው፡–
“ነገርን ሁሉ የሚያከብረውም፤ የሚያስከብረውም ‹የእኛ ፡ የሰዎች ፡ የጋራ ፡ ስም ምነት ፡ የመሆኑ ፡ የነጠረ ፡ እውነት› ነው!!”
እናማ ወገን ሆይ፡- ነገራችን ሁሉ እጅግ የከበረ ዋጋ ይኖረው ዘንድ… የእኛ የሁላችን ስምምነት አስፈላጊ ከሆነ… እርስ-በርሳችን ተስማምተን ያረከስናቸውን፤… ዳግመኛ እርስ-በርሳችን ተስማምተን ማክበር…፤ ባልጩት ድንጋዮችን… ሚሊየኖች ዋጋ የሚያወጡ አልማዞች ማድረግ ይቻለናል ማለት ነው!!!
ታዲያ… የመክበር ዋነኛ ምንጩ የጋራ ስምምነታችን ከሆነ… በሌሎችስ ጠቃሚ ነገሮቻችን ላይ ስምምነት የማይኖረን ለምን ይሆን??!!!
ለማንኛውም እኛነታችንን ከፍ ለሚያደርጉ፣ ለሚያከብሩንና ለሚያስከብሩን የጋራ ስምምነቶቻችን…. የጋራ-ፅዋ እናንሣ!! Cheers for our Precious Agreements… that make us precious!!! ቺርስ!!!!