>

ሀኒሻ ሰለሞን "መንግስትን ትቃውማለች" በሚል ሰበብ ከመድረክ ተገፋች!!! (አበበ ቶላ)

ሀኒሻ ሰለሞን “መንግስትን ትቃውማለች” በሚል ሰበብ ከመድረክ ተገፋች!!!
አበበ ቶላ
በጀርመን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ሲመጡ በሚኖረው ዝግጅት ላይ ዝግጅት እንድታቀርብ ብትጠቆምም በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰዎች አርቲስቷ ኢትዮጵያ ውስጥ ወንድሟ ስለታሰረባት ይሄንን አቤቱታም በገ ላይ ደጋግማ ስታሰማ ስለነበረ ምናልባት መድረክ ላይ ተቃውሞ ልታቀርብ ትችላለች በሚል በዝግጅቱ ላይ እንዳትገኝ ከልክለዋታል።
የአርቲስቷ ወንድም በምን ምክንያት እንደታሰረ እሷም ቤተሰቦቻቸውም ታሳሪው ወንድማቸውም በርግጠኝነት እስካሁን እንደማያውቁ እና ክሱ በየግዜው እየተቀያየረ የፍትህ ያለህ እያለች ነበር!
የጀርመን ኤንባሲ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀባበል ኮሚቴ ሰዎች ሆይ ይህ አይነቱ ባልተጨበጠ ነገር ላይ የተመሰረተ ማግለል ለማንም አይጠቅምም።
ሀኒሻ ሰለሞን በገጿ ክልከላውን አስመልክታ ይህንን አስፍራለች:-
ኢትዮጲያዊያን ወገኖቼ አድናቂዎቸ  ከጀርመን ከሆላድ ከኖርዌ፥ ከስዊዘርላድ፥ ከስዊድን፥ ከፈረንሣይ እና ከሌሎችም አገራት የምትገኙ በተለያየ መንገድ በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ ለዶር #አብይ በሚደረግላቸው አቀባበልና ድጋፍ ላይ ትገኛለሽ ወይ? ብላችሁ ለጠየቃችሁኝ መልሴ አልገኝም ነው……
ምክንያቱም እንደሰማሁት ከሆነ በጀርመን ያለው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ኮሚቴ በዶ/ር አብይ ዝግጅት ላይ ወንድሜንና እንደወንድሜ ያሉ በጥርጣሬ ብቻ ተይዘው ታስረው እየተንገላቱ ላሉት በሶሻል ሚድያ ባሰማሁት የፍትህ ጉለድት፥ መንግስትን ተቃውማለች የሚል ሰበብ በመጠቀም በዶ/ር አብይ መድረክ ላይ ተካፉይ እንዳልሆን ተደርጓል….
እንግዲህ የመናገር መብት ባለበት ሃገር ላይ ተቀምጠን፥ በተግባር ባንፈጽመውም በሃሳብ ደረጃ እንኳ መቀበል ያልቻልን ሰዎች በመሆናችን አሳፋሪና አሳዛኝ ሆኖ አግኝቸዋለሁ….
ስለዚህ እኔ በዝግጅቱ መድረክ እንዳልሳተፍ ያሴሩት በጀርመን የኢትዮጵያ ኢባሲ ባልደረቦች የዝግጅቱ እስተባባሪዎች እንዲያውቁት የምፈልገው #እኔ_የድል_እጥቢያ_አርበኛ_እይደለሁም!!!
እኔ ከናንተ በፊት ስለ #ኢትዮጲያዊነት፣ ስለጀግኖቿ መስዋእትነት፣ በህዝቦቿ መካከል ስለሚኖረው አንድነትና ፍቅር ድምጼን ከፍ አድርጌ ያዜምኩ የለውጡም አካል ነኝ….
ስለዚህ የዶ/ር #አብይ የአቀባበልና የምስጋና ዝግጅት ላይ መድረክ ላይ ወጥቼ ዜማዎቼን ማሰማት እንጂ የለውጡ አካል እንዳልሆንኩ ተገፍቼ ተመልካች ብቻ አልሆንም…..
በዚህ በጠቅላይ ሚንስትሩ አቀባበል ላይ እንዳልገኝ ባልሆነ ምክንያት መፈጠሩ እጅግ በጣም አሳዝንኖኛል….
ለተከበሩ የ #ኢትዮጲያ ጠቅላይ ምንስተር ዶር #አብይ አህመድ ጉዞአቸው የተሳካ እንዲሆን መልካም ምኞቴን ከወዲሁ ሳልገልጽልዎ አላልፍም….
Filed in: Amharic