>
5:13 pm - Saturday April 18, 4753

አንድ ሌት በቺቺኒያ ... እንደወረደ (ታምሩ ተመስገን )

አንድ ሌት በቺቺኒያ (እንደወረደ)
ታምሩ ተመስገን
… ኑሮ ሀሞትና እሬቱን ደባልቆ እየጋተህ ነው? ህይወት ቅጠል ቅጠልም አፈረ አፈርም አትልህም? ጧት ስትነሳ ከምስጋና ይልቅ እሮሮህ ይቀድማል? ይሄኔ እኮ ያቃናኸው እየተደፋብህ፣ የካብከው እየተናደብህ ህይወት ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ሆናብህ “ኤጭ አሁንስ በጣም በዛ…” ብለህ በሶስት ብር ሲባጎ የኩሽናችሁ አውራጅ ላይ ተንጠልጥለህ ሲጥ ለማለት ከዛሬ ነገ እያልክ ይሆናል መቼም!
ወዳጄ በመጀመሪያ አጥብቄ እምመክርህ እንድትረጋጋ ነው፡፡ ሰከን እንድትል፡፡ ለምን መሰለህ ሁሉም የየራሱን ያንቀላፋ ሞት በጀርባው አዝሎ ስለሚዞር ያንተን ያገጠጠ ሞት ማንም አይነጥቅህም፡፡ እተውከው ቦታ ላይ ተዘርፍጦ ይጠብቅሃል፡፡
ይልቁንስ ከመሞትህ በፊት የግድ ማየት ያለብህ አንድ ቦታ አለ፡፡ አንድ ሌት፤ አንድ ሌት ብቻ በዚህ ቦታ እንድታሳልፍ አጥብቄ እመክርሃለሁ፡፡ ምናልባት በዛች አንድ ሌት ላለመሞት አንድ ሺ ምክንያቶችን ልታገኝባት ትችላለህ፡፡ ቺቺኒያ! 
“ገንዘብ ደስታን አይገዛም፡፡” ብለው ለሚሞግቱህ “ገንዘብ ደስታን ይገዛል፤ ይልቁንስ ደስታ የሚሸጥበትን ቦታ ስለማታውቁ ነው፡፡” የሚል መልስ እንድትሰጥ እድሉን ትሰጥሃለች፡፡ ቺቺኒያ፡፡
ቀን በሸቀጥ ንግድ ስትናጥ የምትውለው ቺቺኒያ ሌት ደግሞ በወሲብ ሸቀጥ ስትጋለብ ታነጋዋለች፡፡ እዚህ እርጋታንና ፀጥታን “ፃ እርኩስ መንፈስ” ብለው አባረው ትርምስን አበጀህ ብለው ተቀብለዋል፡፡
ማታ 3 ሰዓት አካባቢ ሂድ፡፡ የሚያውቀኝ ሰው ድንገት ቢያየኝስ ብለህ እንዳትሰጋ፤ ሲጀመር እሱን እዚህ ምን አመጣውና? እዚህ ጋር አንድ ጨዋታ አስታወስከኝ….
(እዚሁ መሀል ሀገር የሆነውን ልንገርህ፤ ባልና ሚስት ልጥጥ ናቸው አሉ፡፡ ቅባቴ! ሀብት እስከጉሮሮአቸው ያነቃቸው፡፡ ግና እርጅና ነው መሰል ሁለቱም ተሰለቻችተዋል አሉ፡፡ ታዲያ የልባቸውን በልባቸው አድርገው በየፊናቸው ከሌላ ጋር ይማግጣሉ፡፡ አንድ ቀን ሚስት እንደ ውሃ በምትፈስ ውድ መኪናዋ ከአንድ ወጣት ጋር ፍስስ እያለች ፔኒሲዮን ስትገባ የበሏን መኪና እዛው ፔኒሲዮኑ ውስጥ ቆሞ ማየት። ወዳጄ ትደነግጣለች ብለህ አስበህ ከሆነ ተሳስተሃል ይልቁንስ ረጋ ብላ ጥበቃውን ጠየቀችው፡፡ አንዲት ልትፈነዳ ጫፍ የደረሰች እንቡጥ ይዞ ገብቶ እየቀጠፋት እንደሆነ ነገራት፡፡ እሷም አራዳ ነች ወዲያው መኪናዋን አዙራ ወደ ሌላ ፔኒሲዮን ሄደቻ፡፡
አየህ “ማነህ? ስትባል እኔ ነኝ” በማትልበት ቦታ አትቁም ይሉሃል ይሄ ነው፡፡ ምን አፍ አላትና በሏን ከመኝታ ክፍል ጎትታ ታስውጣው?
ስለዚህ ዛሬ አንተም ፈታ በል እዚህ የሚመጣሁ ሁሉ አንተ የፈለከውን ፈልጎ ስለመጣ ሙሉ ነፃነት ይሰማህ፡፡
ቺቺየ አታሳፍርህም እንደኪስህ ማማር እንደ አንደበትህ አሳማኝነት የተመኘሃትን እንስት አቅፈህ ልታነጋው ትችላለህ፡፡
ወደ Havana በሚወስደው መንገድ ግራና ቀኝ ከሚገኙ ጠባብ አርከበ ቤቶች ክትፎ በኬክ የሆኑ ውብ እንስቶች ይጠብቁሃል፡፡
ቅላት ብትል፣ ቅርፅ ብትል፣ ውበት ብትል፣ ጠረን ብትል፣ ፈገግታ ነፃነት ብትል… ብቻ ምን አለፋህ እነዚህ እንስቶች ጭብጥ የማይሞላ ቅስር ጡታቸውን ያለጡት ማስያዣ በስስ አላባሽ ለብሰው የጡታቸው ጫፍ ከአላባሹ ስር እየተሽኮረመመ ያባብልሃል! ይጠርሃል፡፡ ናና ይልሃል። ምራቅህን ስትውጥ ይታወቅሃል፡፡ ቦርጭ የሚባል ነገር ድርሽ ያላለበት ወገባቸው ደግሞ ቅንጥስ ብሎ የሚወድቅ መስሎህ ከስሯ ልትነጠፍ ይቃጣሃል፡፡ ከፓንታቸው ረዝሞ በማይረዝመው ሚኒያቸው ውስጥ ያበጠ ዳሌአቸውን ሲራወጥ አይተህ በነሆለልክበት መኪና ደፍልሶህ ቢሄድ እንኳን የሚታወቅህ አይመስለኝም፡፡ ጭናችው ደግሞ፣ ማማሚያ……….. ፖም ገምጠህ ታውቃለህ? ፖም! ጭናቸው ፖም ነው፤ የሚገመጥ፡፡ የሚሳም፤ እንደ አይስኬሬም የሚላስ! ቺቺኒያ ከራስ ፀጉራቸው እስከ እግር ጥፍራቸው ድረስ ቁርጥምጥም ተደርገው የሚበሉ እንስቶች ጧት ተዘርተው አመሻሹ ላይ የሚበቅሉባት የቅንዝር እንብርት ናት፡፡
አይናፋር ነኝ ብለህ አልፈሀቸው ለመሄድ ብትሞክር እነዚህ የውበት አማልክቶች የቅንዝር ጠበብቶች ዙሪያህን ይከቡሃል፡፡ ጡታቸውን ያስነኩሃል፡፡ (በነፃ)፡፡ ጭናቸውን ያስዳስሱሃል፡፡ (ይሄንንም በነፃ)፡፡ መቀመጫቸውን ያስጨምቁሃል፡፡(ሁሉንም በነፃ)፡፡  አይገርምም ግን!? በቃ እንደዚህ ናቸው፤ ይጫረቱሃል፡፡  ያሸነፈችዋ ጠባቧ ኮንቴነር ውስጥ ወስዳህ ጭንህ ላይ ቁጭ ብላ በጡቷ እየተሻሸችህ በሙቅ ትንፋሿ አንገትህን እያረጠበችህ ስታባብልህ ጭኗን ስታስዳስስህ ከቤቱ ዲምላይት ድንግዝግዝነትና ጆሮ ከሚበጥሰው ሙዚቃው ላይ ተዳምሮ ራስህን ሁሉ ልትስት ትችላለህ፡፡  እውነት እልሃለሁ ይሄን ጊዜ ከአፍህ የሚወጣው አንድ ጥያቄ ብቻ ነው “አዳር ስንት ነው?” አንተ በዋጋ ተስማማ እንጂ እንስቶቹ ችግር የለባቸውም፡፡ ሌሊቱን ሙሉ በፍስሃ ዓለም ሲጋልቡህ አድረው ሰውነተህ ውልቅልቅ ብሎ በሳንሳ ወደቤት ልትመለስ ሁሉ ትችላለህ፡፡ አቅም የለኝም ካልክ ደግሞ በጊዜ ተጠናቀህ ሙቅ ደረታቸው ላይ ክብ ጡታቸው መሀከል አስተኝተው ፀጉርህን እያሻሹ ስለ እንቅልፍ አዲስ ታሪክ ያስተምሩሃል፡፡ ልጅነትህን ያስናፍቁሃል፡፡
ምናልባት ደግሞ እነዚህ ቤቶች ላይ መታየት ከደበረህ ጣጣ የለውም ቺቺኒያ ሌላም መፍትሄ አላት፡፡ ሂድ ማሳጅ ቤት፡፡ ሌላ ዓለም ላሳይህ፡፡  በማሳጅ ቤት ማልያ የሚሰራው ጉድ እንዲህ ተነግሮ አያልቅም፡፡ ከነጋዴ እስከ ባለስልጣን፣ ፊደል ከቆጠረው እስከ መሀይሙ፣ ከልጅ እስከ ወጣት፣ ከታዋቂው እስከ አዋቂው፣ ከጥበብ ሰው እሰከ ተራ የመንደር ወሬኛ፤ ከባለትዳር እስከ ፈት ድረስ ልትገምተው እንኳን የማትችለው ህዝበ አዳም በአይነት በአይነት ወደ ማሳጅ ቤቶች ይጎርፋል፡፡ በቡድንም በነጣላም፡፡ ለመታሸት ብቻ ከመሰለህ ወዳጄ በጣም ተሳስተሃል፡፡ extra ስለሚባል የጨዋ መዝናኛ ልንገርህ…
ልክ ስትገባ ሪሴፕሽን ላይ ውበታቸው ለምቦጭ የሚያስጥሉ ደማም እንስቶች ሶፋ ላይ ተቀምጠው ስማርት ስልካቸውን እንደ ሎሊፖፕ በሚጠባ ረዣዥም ውብ ጣታቸው እየነካኩ በፈገግታ ይመለከቱሃል፡፡ ወሬ ሳታበዛ ይበልጥ የተመቸችህን መርጠህ ወደ መታሻ ክፍል ትገባለህ፡፡
መታሻ ክፍሉ ዲም በሆነ አንፖል የፈዘዘ ሲሆን ጥግ ላይ አንድ ሌዘር ፍራሽ ነጭ አንሶላ ለብሶ ታገኛለህ፡፡  ልብስህን አወላልቀህ ፎጣህን አገልድመህ ትጠብቃታለህ፡፡ የመረጥካት ቆንጆ ከተፍ ትልና ሻማ ለኩሳ እየተስለመለመች እጇ ላይ የለቀለቀችውን ሎሽን አልያም ዘይት ሞቅ እያደረገች “ልብስህን አውልቃ” ትልሃለች፡፡ ከሎሽኑም ከዘይቱም ይልቅ በስስ የሌሊት ልብሷ ውስጥ የሚራወጠው ወፍራም ዳሌዋ ከንፈርህን በምላስህ እንድታረጥብ ያስገድድሃል፡፡ ከጡት ማስያዧዋ ያፈነገጠው መንደሪን የመሰለው ጡቷ ከአይንህ አልሸሽ ይልሃል፡፡ ስትራመድ አልፎ አልፎ ግልጥ ግልጥ ግልጥ የሚለው ጭኗ ጭኖችህ መሀከል ሙቀት እንዲሰማህ ያስገድድሃል፡፡ ወዳጄ እንግዲህ መታሸት ከሆነ አላማህ በፊትህ መንበልበል ትችላለህ፡፡ ፍላጎትህ ግን ከዛም ላቅ ያለ ከሆነ ወሬ ሳታስረዝም “extra ነው ምፈልገው፡፡” በላት፡፡ ፖሊስ ምናምን አለመሆንህን ለማረጋገጥ ሆንብላ “extra ምንድን ነው?” ብላ ልትገግምብህ ትችላለች፡፡ ይህ የተለመደ ነው፡፡ ለደቂቃዎች ከተነጋገራችሁ በኋላና የህግ ሰው አለመሆንህን ስታውቅ በextra የሚሰጡ የደስታ አገልግሎቶችን እየተቅለሰለሰች አንገትህን እየላሰች  ሙቅ ትንፋሿን በመላ አካልህ እየዘራች አንድ በአንድ ትዘረዝርልሃለች፡፡ ያኔ ከቀረበልህ ሜኑ ውስጥ የተመቸህን ብልግና መርጠህ…
ቺቺኒያ በህይወት ለመኖር ከዚህም በላይ ብዙ ሺ ምክንያቶች ታስገኝልሃለች፡፡ አለመቀዝቀዝህን ትመሰክርልሃለች፡፡ አለም ሌላም ገፅ እንዳላት ታበስርሃለች። ገንዘብ ይኑርህ እንጂ ደስታ እንዴት እንደሚሸመት እጅህን ይዛ ታስተምርሃለች፡፡ የብልግና ሀሁ ታስቆጥርሃለች። ቺቺየ ሀኒ ሲመሽ ይነጋላታል፡፡  ሲነጋላት ደግሞ እኛ አድናቂዎቿ  ከያለንበት ሄደን ኮከቦቿን እናድናቸዋለን፡፡
.
ማሳሰቢያ፡- ሰውየ አሁን በዚህ ሰዓት ከላይ የፃፍኩትን አንብበህ ሽፍደት ቢጤ ማሰቢያህን ነጥቆህ ቺቺኒያ ካልሄድኩ እያልክ ልትገለገል ትችል ይሆናል፤ እኔ ግን የማያዘልቅ መንገድ እንዲሁ አትጀምር እልሃለሁ፡፡ እንዴ ለራስህ ክብር ይኑርህ እንጅ!! ሸፋዳ፡፡ 
አበቃሁ፡፡
Filed in: Amharic