>

የትህነግ ክፉ ሴራው እየመከነበት ነው!!! (የሽሀሳብ አበራ)

የትህነግ ክፉ ሴራው እየመከነበት ነው!!!
የሽሀሳብ አበራ
*   አቶ ሙስጠፋ ኡመር ለ SBS ራዲዮ እንደተናገሩት” ለበርካታ ዓመታት በአማራው ላይ ስር የሰደደ አሉታዊ ስብከቶች ስለነበሩ፤ የመጀመሪያ ልዑካን ቡድናችንን በቅርቡ ወደ አማራ ክልል እንዲሄድ እናደርጋለን” ብለዋል!
ጥላቻችን እንደ ርዕዮተዓለም ፣ክፉነትን እንደመርህ፣መነጣጠልን እንደ ግብ ማስፈፀሚያ ወስዶ በየዋሁ የኢትዮጵያ  ህዝብ ላይ አረም ሆኖ የቆየው ትህነግ ክፉ ሴራው እየመከነበት ነው፡፡
የኢትዮጵያ  ሶማሊያው ርዕሰ መስተዳድር  አቶ ሙስጠፋ ኡመር ለ SBS ራዲዮ እንደተናገሩት፡” ለበርካታ ዓመታት በአማራው ላይ ስር የሰደደ
አሉታዊ ስብከቶች ስለነበሩ፤ የመጀመሪያ ልዑካን ቡድናችንን በቅርቡ ወደ አማራ ክልል እንዲሄድ እናደርጋለን” ብለዋል፡፡
 …
ለትህነግ የበቀል አዝርዕት  መውቂያ የነበሩት አቶ አብዲ ኢሌ” ህዋኃት ወንድማችን ነው፡፡አማራ እየለያችሁ ግደሉ፡፡አማራ እና  ሀበሻን አጥፉ” ሲሉ ለጎሳ መሪዎች  መልዕክት አስተላልፈው ነበር፡፡ የመልዕክቱ አስተላላፊ  ትህነግ ነበረች፡፡ትህነግ አብዲን ለክፉ ዓላማ ተጠቅማ ወደ እስር ሲገባ አላደነችውም፡፡
 …
የትህነግ መንገድ አክሳሪ ነው፡፡ የትህነጉ ጌታቸው ረዳ ” ወልቃይትን ወደ ጎንደር ክፍለ ሃገር፣ራያን ወደ ወሎ ክፍለ ሃገር ለመመለስ መሞከር ፀረ ህገመንግስት እና የድሮ ስራዓትን መናፈቅ ነው የሚል ይዘት ያለው ሃሳብ በዋልታ አንሸራሽረዋል፡፡
 ….
ቅን የሆኑት አቶ ጌታቸው ወልቃይት የጎንደር፣ራያም የወሎ እንደነበር አምነዋል፡፡ነገሩ ራሳቸው አማራ ነኝ ብለው በመቀሌ ዮኒቨርስቲ በ1996 ረብሻ ፈጥረው ነበር፡፡ ሲረብሹ ትህነግ ስልጣን ስትሰጣቸው ማንነታቸው ቀይረው ራያዎችንም ማንነታቸውን እንዲሸጡ ለመኑ፡፡ ልመናቸውንም በዋልታ አሰሙ፡፡ ማንነት በልመና፣በማሰር፣በማባባል አይሸጥም፡፡ ሰውን ከሰው ልዮ የሚያደርገው ከቆዳ ቀለሙ ቀጥሎ ማንነቱ ነው፡፡ማንነት ከግለሰብነት እስከ ቡድን ማንነትን ይጠቀልላል፡፡ ማንነትን መግዛት እንደ ህገወጥ የሰው ልጅ ዝውውር(human trafficking) ይቆጠራል፡፡ ትህነግ የዚህ ወንጀል ተጠያቂ ናት፡፡
 …
አዴፓ በዚህ ጉዳይ  አንድ ወሳኝ አቋም ይዟል፡፡
የኢትዮጵያ  ክልሎች የተዋቀሩት በ 1984  ነው፡፡በ 1985 ክልል ተመስርቷል፡፡ ህገመንግስቱ የፀደቀው  ህዳር 29 ቀን 1987 ዓም ነው፡፡ ስለዚህ ህገመንግስቱ እና የክልል አወቃቀር አይተዋወቁም፡፡ይልቁንም ህገመንግስቱ ማንነት እንዲከበር ይወተውታል፡፡
 …
የፌዴሬሽን  ምክር ቤት ሃላፊዋም የወልቃይት  ጥያቄ ህገመንግስታዊ አይደለም ብለውታል፡፡ይበሉት ግድ የለም፡፡ህገመንግስት የሰው ይገዛል እንጂ ህገመንግስት ሰውን በግዳጅ አይገዛም፡፡ ደግሞ የፌዴራል ስልጣን ተይዞ ወደ መጡበት አካባቢ  ወግኖ መከራከር ነውርም ነው፡፡
 …
በአጠቃላይ ለፖለቲካችን በመውቀስ እና ለወቀሳው መልስ በመስጠት መፍትሄ አይመጣም፡፡ ቁምነገሩ   ተግባር ነው፡፡
 ….
አዴፓ ወቅቱን የሚመጥን ምደባ ያካሂዳል ብለን ነበር ከዴኤታ ላይም ሆነ ሚኒስተር ላይ  ወቅቱን ያነበበ አመራር ያመጣ አይመስልም፡፡የዶክተር ስዮም መስፍን ዴኤታነት ባይመጥነውም፣መመረጡ ግን መልካም ነው፡፡ዶክተር ስዮም ወቅቱን የተረዳ፣አስተዋይ እና አሰላሳይ ፖለቲከኛ ነው፡፡
አማራ እንደ መርዶክዮስ
ሳምሶን አለብን
መለስ አድዋ ተወልዶ አራት ኪሎ ሲኖር “የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር” ይባላል። አንድ ጎጃም የተወለደ አርሶ አደር ጉራፈርዳ ሲኖር “ሰፋሪ” ይባላል!
 የሶማሌው ፕሬዝዳንት ስለአማራ ሕዝብ ተናገሩት የተባለውን ነገር ሳይ መጽሐፈ አስቴር ታወሰኝ፤ የመርዶክዮስ እና የሐማ ታሪክ።
አማራን ከደርግ መንግስት ጋር በመደፍጠጥ ጨፍጫፊ አረመኔ ለማስመሰል ያልተፈነቀለ ድንጋይ የለም። የሞሶሎኒ፣ ሻዕብያና የህወሓትን የጦርነት ዘመን ታሪክ በጥቂቱ ማዬት ብቻ በአማራ ላይ የተዘመተውን ሰይጣናዊ ትርክት መረዳት ይቻላል።
ድህረ ደርግ ማለትም በዘመነ ህወሃት በመንግስት መዋቅር የአማራን ሕዝብ ከሌሎች የሐገሪቱ ነገዶች ጋር እስከዘላለም ለመለያየት የተነዛው ውሸት ቀላል አልነበረም።
በምዕራቡ ዓለም በተለይም በአሜሪካ እና እንግሊዝ የአማራ ሕዝብ እንደ ሶሻሊስት ይቆጠራል። ይህ ማለት አንድ የአሜሪካ ወይም የእንግሊዝ ዲፕሎማት አንድን አማራ የሚመለከተው እንደ ሩሲያው ፑቲን ጽንፈኛ ሶሻሊስት እንደሆነ ነው። ይህን የተዛባ ፍረጃ መልክ የሚያሲዝ ጠንካራና አለማቀፋዊ የአማራ ‘Diplomatic Team’ ሳያስፈልገን አይቀርም።
በህወሃት ዲክሽነሪ “ደርግ” ማለት አማራ ማለት ነው። በእናቱም በአባቱም ሙሉ ኦሮሞ የሆነው ኮሎኔል መንግስቱ ሐይለማርያም በህወሃት መነጽር ሲታይ ግን አማራ ነው። ምክንያቱም መንግስቱ ሐይለማሪያም ኢትዮጵያዊ ስለሆነ።
መለስ አድዋ ተወልዶ አራት ኪሎ ሲኖር “የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር” ይባላል። አንድ ጎጃም የተወለደ አርሶ አደር ጉራፈርዳ ሲኖር “ሰፋሪ” ይባላል።
መለስና በረከት ከጭፍራዎቻቸው ጋር በመሆን በየብሔሩ ለአማራ የሚሆን የመከራ መስቀል ሲቸነክሩ ኖረዋል። ሐማ ለመርዶክዮስ መስቀያ ይሆን ዘንድ እንጨት እንዳዘጋጀው ማለት ነው።
ነገር ግን ሐማ መርዶክዮስን ሊሰቅል ባዘጋጀው ግንድ ላይ ራሱ ተሰቀለ። የመርዶክዮስም ሐዘን በደስታ ተቀየረ።
የሐማን ርካሽ የዘመናት አሉባልታ በአደባባይ በመመስከር፦
‹‹ለበርካታ ዓመታት በአማራው ላይ ስር የሰደደ አሉታዊ ስብከቶች ስለነበሩ፤ የመጀመሪያ ልዑካን ቡድናችንን በቅርቡ ወደ አማራ ክልል እንዲሄድ እናደርጋለን…›› ሲሉ ተደምጠዋል የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ።
በሀሰት ክስ ሞት የታወጀበት የመርዶክዮስ ሕዝብ ነጻ ወጣ።
በመጨረሻም፥ የመርዶክዮስ ቤተሰብ  ሌሎች ቅን ሲሆኑ ብቻ ንጽህናውን የሚመሰክሩለት መሆን የለበትም። ራሱ የሐዘኑን ማቅ ከላዩ ላይ ወርውሮ ጥሎ ከቁዘማ በመውጣት ከደሙ የነጻ ህዝብ መሆኑን ማወጅ አለበት።
Filed in: Amharic