>
4:42 am - Friday February 3, 2023

የፖለቲካ ዘማዊነቱ በአስቸኳይ ካልቆመ አገሪቱን ከማጥወጣበት ኪሳራ ዉስጥ ይጨምራታል!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

የፖለቲካ ዘማዊነቱ በአስቸኳይ ካልቆመ አገሪቱን ከማጥወጣበት ኪሳራ ዉስጥ ይጨምራታል!!!
ቬሮኒካ መላኩ
በ1848  እንግሊዟ ሀያል  የነበረችዉ ንግስት ቪክቶሪያ  የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረዉን  ሎርድ Parlmerston John Henry Templeን ቤተመንግስታቸዉ በመጥራት ፤
.
 “ለመሆኑ በዛሬዉ ዕለት የእንግሊዝ ወዳጆችና ጠላቶች እነማን ናቸዉ?” ብለዉ ይጠይቃሉ።
.
 ጠቅላይ ሚኒስትሩም ቀልጠፍ በማለት …. “ ንግስት ሆይ ! እንግሊዝ የዘለቄታ ጠላትም ሆነ የዘለቄታ ወዳጅ የላትም። የዘለቄታ ጥቅም እንጂ” (England has no eternal friends, England has no perpetual enemies, Englandhas only eternal and perpetual interests  በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መለሰላት፤፤
ይሄ የጆን ሄነሪ ንግግር  በአለም ከተሰማ በኋላ ‹‹በአገሮች መካከል ዘላቂ ጥቅም እንጅ ዘላቂ ጠላትም ሆነ ዘላቂ ወዳጅ የለም›› የሚለዉ አባባል አለማችን አሁን የምትመራት የፖለቲካ ቀኖና ሆኗል፤፤ የዘመናዊ መንግስት አልፋና ኦሜጋ የአገሩን ጥቅም ማስጠበቅ ብቻ ነዉ፤፤በፖለቲካቸዉ ውስጥ ጥቅም እንጂ ሞራሊቲ የሚባል ቅመም የለም።
..
ዛሬ SHEGER FM 101 ባወጣዉ ዜናዉ ኢትዮጵያ በዉጭ ምንዛሬ በሆነዉ ዶላር የምትገዛዉንና  ለመስማት በሚዘገንን የወደብ ኪራይ ከፍላ የምታስገባዉን ነዳጅ የኤርትራ የነዳጅ ቦቴዎች በየቀኑ እየገቡ ከልሙጥ ሉክ ወረቀት የበለጠ ዋጋ በሌለዉ የኢትዮጵያ ብርና ናቅፋ  እየቀዱ ወደ አገራቸዉ እያስገቡት ነዉ፤፤ይሄ እጅግ የሚያሳዝንና ፍትሀዊ ያልሆነ መስተጋብር ለኢትዮጵያ እንደዉርደት የሚቆጠር ነዉ፤፤
..
 ባለፈዉ ክረምት  ጠ/ሚ አቢይ አህመድ ወደ አስመራ ባቀናበት ወቅት  ‹‹  ፕሬዚደንት ኢሳያስ የኤርትራ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን እንድሰራ ይፈቀድልን ›› በማለት ሲለምን አለም ሰምቶ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር ፤፤ ዛሬም ደሞ ደ/ር አቢይ አህመድ የኤርትራ ዉጭ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የኤርትራ የንግድና ኢኮኖሚ ሚኒስትር በመሆን እየሰራ ይመስላል፤፤
..
ኢትዮጵያ ከባለፉት 27 አመታት ወድህ ጥቅሟን የሚያስከብርላት ሳይሆን ጠቅሟን አሳልፈዉ በሚሰጡ መሪዎች እየተገዛች ነዉ፤፤ መለስ ዜናዊ  በአነድ ወቅት ‹‹ ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ለአንድ ሰአት ማዉራት ማለት መቶ መጽሀፍት እንደ ማንበብ የቆጠራል ›› በማለት ገድብ የሌለዉ አምልኮቱን በመግለጽ አገሪቱንም ለአመታት ኢሳያስ አፈዎርቂ የሚዘዉራት አገር አድርጓት ነበር ፤፤
 በዛን ወቅት በነበረዉ ፍትሀዊ ባለሆነዉ የሁለቱ አገራት የኢኮኖሚና የፖለቲካ መስተጋብር ኤርትራ ከኢትዮጵያ በምትዘቀዉ የቡና ምርት ከአለም ኤክስፖርተሮች አንዷ ተብላ መመዝገቧን የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነዉ ፤፤ በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ ዜጎች ሞት ምክንያት የሆነዉም የሁለቱ አገሮች ጦርነት መንስኤ ፍትሀዊ ያልሆነ የኢኮኖሚ ዘረፋ እንደነበር አለም ለአመታት ሲያቦካዉ የነበረዉ ሀቅ ነዉ፤፤ አሁንም ግን የኢትጵያ መሪዎች ይሄ የገባቸዉ አይመስልም፤፤ ከዚች ደሃ የኢኮኖሚ ቋታችን ኣድፋፍተዉ ቢወስዱብን የሚሰማቸዉ እንዳች የህሊና ወቀሳ የለም። አሁንም የማስጠነቅቀዉ ነገር ቢኖር ይህን መሳይ የፖለቲካ ዘማዊነት በአስቸኳይ ካልቆመ አገሪቱን ከማጥወጣበት ኪሳራ ዉስጥ ይጨምራታል፤፤
Filed in: Amharic