>

ወቅዱስ  አቡነ ማትያስ  የስራ መልቀቂያ ሊያቀርቡ ነዉ!

 

ወቅዱስ  አቡነ ማትያስ  የስራ መልቀቂያ ሊያቀርቡ ነዉ!!!

 

ከቄስስ ኃብተ ጊወርጊስ ዘውዴ

*ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሶስት ፓትሪያኮች ልትመራ ነው!!!

ቅዱስ ነታቸዉ  ዛሬ ማታ ለሚቀርቡአቸ ዘመዶቻቸዉ አማክረዋል በኔ ምክንያት እናቴ ቤተክርስቲያን መታመስ የለባትም እኔ በፀሎት ባግዝ ይሻላል ቅዱስ ሲኖዶስም እንደሚቀበለኝም አምናለሁ በማለት ሲመክሩ እንዳመሹ የዉስጥ መረጃ አለ  ነገርግን በስልክም በአካልም  ቅዱስነተዎ አስበዉበት  ነወይ ለማን ብለዉ ይለቃሉ የሚሉም እንዳሉና ቅዱስነታቸዉም አይ የሰሞኑን አክራሞቴን ማንም አያዉቅልኝም  እኔነኝ የማዉቀዉ ተዉኝ ይብቃኝ በማለት ግትር ሀሳባቸዉን አጠንክረዉ አምሽተዋል ።

ዕዉነት ከሆነ መቸስ እግዚአብሔር አመልክቶዎታል ነዉ የሚባለዉ በቃኝን ያስተማሩ በፈቃደኝነት ስልጣንን አልፈልግም ማለት መታደል በህዝብም ዘንድ ክብርና ሞገስ አለዉ ።

 

ተያያዥነት ባለው ዜና:-

ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሶስት ፓትሪያሪኮች ልትመራ ነው!!!

 

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቅድስት ቤተክርስቲያን ከ27 አመታት በኋላ በአንድ ቅዱስ ሲኖዶስ ሥር ለመምራት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጥሪ ቀርበ ።

ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ በሶስት ፓትሪያኮች ልትመራ ትችላለች ።

ለ27 አመታት በታሪክ አጋጣሚ በተለያዩ ሲኖዶሶች ተከፋፍላ የቆየችው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የመጀመሪያው ወሳኝ አንድነት ከፈጠረች በኋላ ቀጣዩ

አንድነት ከኤርትራ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተከርስቲያን ጋር ለመፈጸም እንደታሰበ ብጽኡ ወቅዱስ ፓትሪያክ አቡነ ማቲያስ በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ንግግራቸው ገልጸዋል ።

ብጽኡ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በንግግራቸው “ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን በታሪክ ና በሐይማኖት አንድ ህዝቦች ናቸው ብለዋል : አክለውም ለኢትዮጵያዊያን ከኤርትራውያን በላይ ቅርብ ወንድም ለኤርትራውያንም ከኢትዮጵያውያን በላይ የሚቀርባቸው ወንድም የለም ብለዋል ።”

በመጨረሻም ለኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እህት ቤተክርስቲያን የአንድነት ሲኖዶሳዊ አስተዳዳር ለመፍጠር ጥሪ አቅርበዋል ።

ከኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዘንድ በወርሀ ሐምሌ 2010 ዓም የአንድነት እና የትብብር ጥሪ መቅረቡ አይዘነጋም ።

የኤርትራ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትሪያክ ከግብጽ የማርቆስ መንበር ወደ ቀደመ ማንነቱ የአቡነ ተክለኃይማኖት መንበር ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል ። selanews24.net

Filed in: Amharic