>
5:28 pm - Tuesday October 9, 5145

የወልቃይት ጠገዴ ተፈናቃዮች ለጠ/ምኒስትር አብይ ደብዳቤ ጻፉ!!!

የወልቃይት ጠገዴ ተፈናቃዮች ለጠ/ምኒስትር አብይ ደብዳቤ ጻፉ!!!
ለኢፌድሪ ጠ/ሚኒስቴር
    አዲስ አበባ       
 በትግራይ መንግስት ከወልቃይት ጠገዴ ከተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች የቀረቡ ጥያቄዎች
ወልቃይት ጠገዴ 1983 ዓ.ም በትግራይ መንግስት በኃይል መያዙ ይታወሳል፡፡ የትግራይ መንግስት ወልቃይት ጠገዴ የማንንት ጥያቄ ባቀረቡ  የወልቃይት አማራዎች ላይ አስር፤ሰቆቃ ግድያ ሲፈፀም መቆየቱ ይታወቃል፡፡የትግራይ መንግስት  አማራዎችን በማፈናቀል በአንፃሩ የህዝቡን ስብጠር ለመቀየር ትግሬዎችን ከአድዋ፤ከአድግራት ፤ከአንደርታ ፤ከአክሱም…ወዘተ  በማምጣት በወልቃይት ለም መሬቶች ላይ አስፍሯል፡፡በአካባቢው የትግራይ መንግስት በዘረጋው የአፈና መዋቅር  የወልቃይት ጠገዴ አማራ ተወላጅ ላይ የተጠና አስተዳደራዊ በደል እየፈፀመ ይገኛል፡፡ የሚፈፀመውን በደልና ግፍ በመሸሽ ከመስከረም /2011 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ  የወልቃይት ጠገዴ አማራዎች ተፈናቅለዋል፡፡ የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስቴርም እየተፈፀመ ያለውን በደል እንዲረዳና አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጠን የሚከተሉትን ዋና ዋና ጥያቀዎቻችን እናቀርባለን፡፡
1 – የትግራይ መንግስት በወልቃይት  ጠገዴ አማራ ላይ የሚፈፅመውን ግድያ፤ አፈና፤ ሰቆቃ፤ አስር  እና መፈናቀል በአስቸኳይ እንዲያቆም
2- የወልቃይት ጠገዴ አማራዋች በቋንቋችን በአማርኛ የመናገር የመማር የመፃፍ፤በበህላችን ሀዘንና ደስታችን የመግለፅ መብታችን አንዲከበር
3-በትግራይ መንግስት የሚፈፀም  የመሬት ዝርፊያ እንዲቆምልን እና ሑብት ንብረት የማፍራት መብታችን እንዲረጋገጥ
4-በማንነታቸው ምክንያት ከወልቃይት ጠገዴ ተፈናቅለው ሶሮቃ ጎንደር አድስ አበባ በጊዚያዊ መጠለያ የሚገኝ የወልቃይት ጠገዴ አማራዎች በአስቸኳይ ወደ ትውልድ ቀያቸው እንዲመለሱና የተረጋጋ ሕይወት እንዲመሩ እንዲደረግ
5-ትግራይ ፀጥታ አካላት ወልቃይት ጠገዴን ለቀው እንዲወጡ እና  የፌደርል የፀጥታ አካላት በቦታው እንዲተኩ እንዲደረግ
6-የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማነንነት ጥያቄ በአስቸኳይ እንዲመለስ
7- ወደ ወልቃይት ጠገዴ የመጡ የትግራይ ሰፋሪዎች በማንነታችን ጥያቄ ላይ የሚፈፅሙትን ሴራና ደባ እንዲቆሙልን
ግልባጭ
ለፌደሬሽን ም/ቤት
ለተወካዮች ም/ቤት
ለኢት/ያ ሰባዊ መብት ኮሚሽን
ለኢህዴግ ጽ/ቤት
አዲስ አበባ
ለሁሉም ሚዲያ ተቋማት
ባሉበት
ለትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት
ለህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ/ህወሃት/
መቀሌ
ለአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት
ለአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ/አደፓ/
 ባሕር ዳር
Filed in: Amharic