>

የአቋም ለውጥ - ከጋዜጠኛና ኣክቲቪስት ኣበበ ገላው

የአቋም ለውጥ
Meles-abeየዛሬ ሁለት አመት ከእነ እስክንድር ነጋ፣ አንዱአለም አራጌ፣ ኦባንግ ሜቶ፣ አብይ ተክለማርያም፣ መስፍን ነጋሽ፣ አበበ በለው እና በርካታ ኢትዮጵያዊያን ጋር በሃሰት የግንቦት ሰባት አመራር በመሆን ከኤርትራ መንግስት ትእዛዝ በመቀበል “ሽብር” በመፈጸም ወንጀል “ጥፋተኛ” ሆነን በመገኘታችን ቅጣት ተላልፎብን ነበር። በዚሁ የሃሰት ውንጀላ ሳቢያ እነ አንዱ አለም፣ እስክንድር ነጋ እና በርካታ ኢትዮጵያዊያን በየእስር ቤቱ በመማቀቅ ላይ ይገኛሉ። በህወሃቶች የቀልድ ፍርድ ቤት እኔም በሌለሁበትና ባልተሳተፍኩበት ልብ ወለዳዊ ወንጀል የ15 አመት እስር ተላልፎብኛል።
እንደ አብዛኛቹ ተከሳሾች ሁሉ የፖለቲካ የድርጅት አባል ሆኜ አላውቅም። አሁን ግን አቋሜን ቀይሪያለሁ። ታግሎ ሊያታግል በሚችል ድርጅት ተቀልቅዬ ከተራ አባልነት እስከ አመራር አቅሜ የፈቀደለኝን ሁሉ ለማድረግ ወስኛለሁ። ይህንንም የቋም ለውጥ በተግባር እና በይፋ በቅርቡ አሳውቃለሁ። ህዝባችንን የበለጠ አደራጅተንና አስተባብረን መታገል የወቀቱ ታሪካዊ ጥሪ ነው። እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ! እኔም አሸባሪ ነኝ!

ጋዜጠኛና ኣክቲቪስት ኣበበ ገላው ሜይ18.2012 ለታሰሩት፣ለተገረፉት፣ለተሰደዱት የድምጾች ሁሉ ድምጽ በመሆን የወያኔ ቁንጮን ኣንገት ያስደፋበትን ቪዲዮ ለትውስታ።

Filed in: Amharic