>
5:13 pm - Tuesday April 19, 3859

''ኣባሎቻችን ሁሉ ኣንዳርጋቸው ጽጌዎች ናቸው'' የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ

ከዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጲያ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ በወያኔ እና በየመን መንግስት የተቀነባበረው የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን መታፈንና አሳልፎ መስጠትን ኣስመልክቶ የወጣ መግለጫ!    

DCESON

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ከሚደግፋቸውና በቅርብ ኣብሮ ከሚሰራቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ኣንዱ የሆነው የግንቦት 7 የፍትሕ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሕፊ ኣቶ ኣንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ መንግስት ደባ በየመን የፀጥታ ኃይሎች በሕገወጥ መንገድ መታገት ከተሰማበት ወቅት ጀመሮ የድጋፍ ድርጅታችን ኣባላትን እጅግ በመረረ ቁጣ ውስጥ ከቷል።

ሐሙስ፣ 03 ጁላይ በብሪታኒያ ኤምባሲ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ፣ የእንግሊዝን መንግስት ስናስጨንቅ ውለናል። የዜጋችሁን መብት ኣስጠብቁ፣ መሪያችንን ኣስረክቡን በማለት። በግማሽ ቀን ባደረግነው ጥሪ በርካታ ኢትዮጲኣውያንን በመየታችንም በተቃውሞ ቤተሰብ ላይ እጅግ እንድንኮራ ኣድርጎናል።

ይህ የሁለት የማይረቡ መንግስታት ኣምባገነናዊና ተልካሻ ደባ የትግል ስሜታችንንም ሆነ ወኔያችንን ኣያቀዘቅዘውም። ኣይታሰብምም። እኛ ዲሞክራሲያዊ ለውጦች ከእባብ እንቁላል እርግብ ጠብቀን ኣናውቅም። የየመን መንግስት የፈጸመው ታሪካዊ ስህተት ግን ቀን የማይሽረው ታርካዊ እዳ ያስከፍለዋል።

የትግል መሪያችንን በማሰር ትግላችንን ማሰር ኣይቻልም። ተስፋም ኣያስቆርጥም። በማይታመን እልክ ውስጥ ይከታል እንጂ። ትግሉን እንድ ሰደድ እሳት ያንቦለብለዋል እንጂ። ተቃዋሚውን ቤተሰብ ኣንድ ኣድርጎ ትግሉን በማሳደግ፣ የወያኔን ቤተሰብ ከኣገራችን ቅዱስ ምድር ይጠራርጋል እንጂ።

ኣንዳርጋችው ጽጌ ከዲሞክራሲያዊ ለውጥ ጋር በቅርብ የሚሰራ በምንፈልገው ጉዳይ ሁሉ ኣንድም ቀን ከጎናችን ያልተለየ እጅግ የምንኮራበት መሪ ነው። ኣባሎቻችን ሁሉ ኣንዳርጋቸው ጽጌዎች ናቸው። ወያኔን ጠራርጎ በመጣል ኣገራችንን መረከቢያውን ሰዓት ለማቅረብ በማይበርድ ቁጣ ተነስተናል።

ለኛም ኣንዳርጋቸው ጽጌ ኣንድ ግለሰብ ሳይሆን፣ ጽኑ መንፈስ ነው።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ

Filed in: Amharic