>

ከህወሃት ዉድቅት ምን እንማር!!! (ሚኪ አምሀራ)

ከህወሃት ዉድቅት ምን እንማር!!!
ሚኪ አምሀራ
 
* አቦይ ስብሃት ቤተሰቦችን ይዞ (14 ናቸዉ) ነበር 100 አመት እገዛለዉ የሚለዉ፡፡ በስነምግባር፤ በእዉቀት፤ በመሪነት ክህሎት የታነጸ ይሄን የቤተሰብ ስርወ መንግስት ሊያስቀጥል የሚችል አላዘጋጁም፡፡  አሁን ቀዉጢ ቀን ሲመጣ ምኑን ከምኑ ያርጉት፡፡ ሽማግሌው ጃጅቶ መንገድ ሁሉ ስቶ ያልሆነ ቦታ ይሄዳል ተከታዮቹም መድረሻውን ባላወቁት የቅጣት አለም ይባዝናሉ!!!
 
ህወሃት መስገብገቡ እኔ ብቻ ማለቱ ለዛሬዉ ዉድቀቱ ዳርጎታል፡፡ ህወሃት ብቻዉን አይደለም የወደቀዉ ይዞት የወደቀዉ የማህበረሰብ ክፍልም አለ፡፡ ” 100 አመት የመግዛት እቅድ ነዉ ያለን” እያለ የትግራይን ወጣት እንዳይሆን አድርጎታል፡፡ ግብረገብነት እንዳይማሩ አድርጓል፤ ከሌላዉ ማህበረሰብ ጋር በሰላም እንዳይኖሩ አድርጓል፤ እራሳቸዉን እንደ አንደኛ ዜጋ በመቁጠር ሌላዉ ስለ ሃገሪቱ እንደማያገባዉ አድርገዉ እንዲያስቡ አድርጓቸዋል፡፡  በጦርነት እነሱን የሚያሸንፍ ሃይል እንደለሌለ ተነግሯቸዋል፡፡ ዩኒቨርስቲ ሳይገቡ የዲግሪ ወረቀት ከትምህርት ሚኒስቴር የተሰራላቸዉ በሽዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች አሉ፤ በአካዉንታቸዉ ቁጥሩን የማያዉቁት ገንዘብ አለ፡፡
 ዱባይ፤ ሲሸልስ እና ታይዋን ድራግ ይዘዉ የሚመላለሱ ናቸዉ፡፡ አዲስ አበባ በየመሸታ ቤቱ ጠዋት እንደኮርኪ ተጠርገዉ የሚወጡ ወጣቶች ነዉ ያፈሩት፡፡ተተኪ ወጣት ሳይሆን 22 ማዞሪያ ዉስኪ የሚራጭ ወጣት ነዉ ወያኔ ያፈራዉ፡፡ ይህ ሁሉ ወያኔ ከጫማዉ ስር አርቆ እንደማያስብ ያሳያል፡፡ አቦይ ስብሃት ቤተሰቦችን ይዞ (14 ናቸዉ) ነበር 100 አመት እገዛለዉ የሚለዉ፡፡ በስነምግባር፤ በእዉቀት፤ በመሪነት ክህሎት የታነጸ ይሄን የቤተሰብ ስርወ መንግስት ሊተካ የሚችል አላዘጋጁም፡፡
አሁን ቀዉጢ ቀን ሲመጣ ምኑን ከምኑ ያርጉት፡፡ አቦይ ስብሃትም ጃጅቶ መንግድ ሁሉ ስቶ ያልሆነ ቦታ ይሄዳል፡፡ ቅዠት እያስተማሩ ያሳደጓቸዉ ወጣቶችም እየተካሄደ ያለዉን ፖለቲካ ምኑንም ሊረዱት አልቻሉም፡፡ ሁሉም ተያይዞ ቁዘማ ላይ እና እንዴት እንዲህ እንደሆነ ብቻ ማንሰላሰል ላይ ናቸዉ፡፡
ከዚህ ዉድቅት ትምህርት ያስፈልጋል፡፡ ሌላው ኢትዮጵያዊ ወጣት የመሪነት ጥበብ እና ክህሎቱን ሊያሳድጉ ይገባል፡፡ ግብረገብነት እና የማህበረሰቡን እሴቶች ማክበር ለረዥም ጊዜ የማህበረሰባችን ደህንነት እና ጤንነት ጠቃሚ ነዉ፡፡ከቴክኖሎጅ ጋር መላመድ፤ መማር፤ ፖለቲካዉን ኢኮኖሚዉን በንቃት መከታተል፡፡ እራስን በሙያ፤ በእዉቀት፤ በሃብት በማበልጸግ የወጡበትን ማህበረሰብ ማገልገል ወሳኝነት አለዉ፡፡
እራስን ከሱስ እና አልባሌ ቦታች ማራቅ እና በዚህ በቴክኖሎጅ ዘመን አለም በብርሃን ፍጥነት እየተንቀሳቀሰ ባለበት ወቅት እጅን አጣጥፎ መቀመጥ ወይም አረንጓዴ ቅጠል እንደሰባራ ጋን አፍ ዉስጥ ወትፎ መሬት ለመሬት መንደባለል ልክ የወያኔ ወጣቶች ዉድቀት የገጠማቸዉ አይነት ነገር ያጋጥማል፡፡ ህይወትን በአላማ እና በራእይ መምራት፤ አድርጌ ማለፍ ያለብኝ ነገር ምንድን ነዉ ብሎ እራስን መጠየቅ እና እራስን ማወቅ የስኬት ምንጮች ናቸዉ፡፡
 የሰዉ ልጅ ሲፈጠር ሁሉም ተመሳሳይ potential ይዞ ነዉ የሚፈጠረዉ፡፡ ልዩነቱ ይሄን የተሰጠንን potential በሚገባ exploit አድርገነዋል ወይ የሚለዉ ነዉ፡፡ ዳርዊን the fittest will survive እንዳለዉ ያለንን አቅም በመጠቀም የዛሬዉን ብቻ ሳይሆን ነገንም fit በማድረግ በቴክኖሎጅ፤ በኢኮኖሚ እና ስነልቦናዉ ጠንካራ ያሆን ማህበረስብ መፍጠር ይጠበቅብናል፡፡በተቃራኒዉ ከተጓዝን እንደ ወያኔ ወጣቶች የስነልቦናዊ እና ማህበራዊ ቀዉስ ዉስጥ እንገባለን፤ አላማ የሌለን disoriented ዜጎች እንሆናልን በመጨረሻም የዚህ ድምር አንድነቱ ያልጠነከረ እና የተበታተነ ህብረተሰብ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡
Filed in: Amharic