>
5:13 pm - Wednesday April 18, 1027

ኦነግን ከራሱ ማዳን (ቾምቤ ተሾመ)

ኦነግን ከራሱ ማዳን

 

ቾምቤ ተሾመ

 

 አንድ የማንክድው የኦነግ እውነታ ቢኖር ወያኔ የጣለበት ጠባሳ ነው፡፡ ኦነግ ከወያኔ ጋር አብሮ አዲስ አበባ ሲገባ ያሳይ የነበረው መሰረት ያልነበረው ትእቢት ፤ለወያኔ መሳሪያ ሆኖ ያቀርባቸው የነበራችው ኋላፊነት የጎደላቸው  የኢትዮጵያን ህዝብን ፍላጎት ያላካተተ ጥቄዎቹም ሆነ የፖለቲካ ብስለት የጎደላቸውና ዘለፋዎቹ ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለዲሞክራሲ ግንባታ እንደ አጋር ሳይሆን የተመለከተው ለሀገሪቱ ሰላምና ዲሞክራሲያዊ ልክ እንደ ወያኔ ጸረ – ህዝብ ድርጅት እንደሆነ አድርጎ ድምዳሜ እንዲወሰድ  አስገድዶታል፤ በተጨማሪም ይህ የህዝብ አመለካከት እንዲጠናከር ያደረገው በወያኔ አቀናባሪነትም ይሆን በራሱ አነሳሽነት በተለያዩ የምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ያካሄደው ዘር ላይ ያተኮረ ጭፍጨፋና፤ በአሶሳም ቀደም ብሎ ከያካሄደው ተመሳሳይ ድርጊት ህዝቡ ልብ ውስጥ ተቀባይነት እንዲያገኝ አላደረገውም ፡፡ ይህንን   የኦነግ የተሸረሸረ የህዝብ ድጋፍ መለሰን በወቅቱ ነጻ እጅ ስጥቶት በአጭር ጊዜ ኦነግ ሰራዊትን ትጥቅ አስፈትቶ መሪዎቹን ወደ እስርና ስደት ዳርጎ ስልጣኑን አደላድሎ እንዲገዛ አድርጎታል ፡፡

ይህ ብቻ ሳይሆን የባድሜ ጦርነት እንዳለቀ ኦነግ በኢሳያስ አስታጣቂነትና ስልጠና ሌላ ግንባር በምእራብ በመክፈት ወያኔን ለማዳከም በሺህ እሚቆጠሩ የኦነግ  ስራዊቶችን ልኮ ምንም ትርጉም ያለው ውጤት ኦነግ ሳያዝመዘግብ በኢትዮጵያ ስራዊት ተከቦ እጆን እንዲሰጥ ተደርጎ እንደገና ቅአስም ሰባሪ ሽንፈትን ተቀብላል፡፡ ይህ የሆነው በኦነግ ተዋጊዎቹ ጀግንነት ማነስ ወይንም የሚሊተሪ ስትራቴጂ ድክመት ሳይሆን የፖለቲካ አመራሩ በሚወስደው ግንዛቤ የጎደለው ፓለቲካዊ እርምጃዎች ተከታዮቹን ያስከፈለው የፖለቲካ ኪሳራ ውጤት ነው ፡፡ አሁን ግን ይህ አዛውንት ድርጅት ተመሳሳይ ስህተት እንዳይሰራ ሁሉም የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎችም ይሁኑ የነአብይ መንግስትም ጨምሮ ኦነግ ከገባበት ማጥ ውስጥ ለማውጣት ቀናነት የተሞላበት ጥረት ማድረግ በጣም ተገቢ ነው፡፡

 በአሁኑ ያለንበት ወቅት ኦነግ ለብዙ ግዚ እታገልለታለሁ ሲል የነበረውን የኦሮሞ ህዝብ በጥሩ መጠን የሚወክለው የፖለቲካ ስልጣን  ይገበዋል የሚለው ጥያቄ በአብዛኛ በተመለሰበት ወቅት፤ የኦሮሞ መሪዎች ኦሮሞ በኢትዮጵያ ያለውን ሚና ብቻ ሳይሆን የአጠቃላይ የሀገሪቱን እጣ ፋንታ በተመለከተ ወሳኝ ሚና በሚጫወቱበት  ወቅት ፤ ልክ እንደሌሎቹ የታጠቁ ቡድኖች አዲስ የተፈጠርውን የፖለቲካ መሃድር ስፋት ተገንዝቦ መሳሪያውን አስረክቦ ከገባ በኋላ፤ በመሳሪያ የተደገፈ “ሰላማዊ” ትግል አካሄዳለሁ ብሎ ሌላ የፖለቲካ ቁማር መጀመሩ እንደ አንስታይን አባባል ተመሳሳይ ድርጊቶችን እያደረጉ የተለየ ውጠት የመጠበቅ አባዜ ኦነገ እንዳለቀቀው ብቻ ሳይሆን ፤ ይህ አዛውንት የፖለቲካ ንቅናቄ ከስህተቶቹ  ተመጣጣኝ ትምህርት እንዳልወሰደና ተመሳሳይ ስህተት ለመስራት እየኳተነ መሆኑን ነው ፤ ይልቁኑም በዚህ ወቅት ከኦነግ የሚጠበቀው፤ ለኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ ያደረገው አስተዋጾና በመመርኮዝ ለወደፊቱ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ግንባታ የሚጫወተውን ሚና ግልጽ አድርጎ ፕሮግራሙን በማስቀመጥ በመላው የኢትዮጵያ ተቀባይነት አግኝቶ በፓርላማ ውስጥ የሚጫወተውን ሚና ማስፋት ነው ፡፡

ነገር ግን አሁን እየተካሄደ ያለው በመንግስት  ውስጥ መንግስት ለመመስረት የሚደረግ ሙከራ፤ ተጠያቂነት በጎደለው መልኩ በህገ ወጥ መንገድ አስተዳደር አፍርሶ የኦነግን  አስተዳደር ለመመስረት የሚደረግ ሙከራ ለኦነግ “ ስራዊትም” ይሆን ይህንን ህገወጥ እንቅስቃሴ እንደግፋለን ለሚሉ የሚያመጣው ነገር ቢኖር ሌላ የፖለቲካ ክስረት ነው፤፡ ስለዚህ  የአብይ አስተዳደርም ይሁን የለማ አስተዳደር ምንም እልህ አስጨራሽም ቢሆንም ኦነግ የፍጠረውን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ከሚሰጡት ተከታታይ መግለጫዎች መረዳት ይቻላል፡፡ አሁንም ቢሆን በጭራሽ አማራጭ ጠፍቶ ነዋሪውም ይሁን በአካባቢው የሚኖሩ ህዝቦች ችግር ላይ ናበስተቀር ድርድሩን በውስጥ መቀጠሉ ኦነግ ይሁን ተከታዮቹን ክብራቸው ሳይነካ የፖለቲካ እንቅስቃሲያቸውን በሰላም የሚቀጥሉበት መንገድ ለማመቻቸት  ድርድሩ በተቻለ መጠን ሰፋ ባለመልኩ መካሄድ አለበት? የዚህ ውጤት ድግሞ ሁሉንም አሸናፊ አርጎ ከቁርሾ ከምሬት ፖለቲካ ያወጣል፡፡ ነገር ግን እነዚህ የታጠቁ ቡድኖች የኦነግ ስም እየተጠቀሙ ነገር ግን ኦነግ የማይቆጣጠራቸው ቡድኖች ከሆኑ ፤ ወይም ኦነግ የፖለቲካ ሽፋን እየሰጠ የሚንቀሳቀሱ ነገር ግን ቁጥጥር ባጣ መልኩ በቡድን ተደረጃተው የህዝብን ሰላም የሚያደፈርሱ የተለዩ ቡድኖች ድርጅቶች መሆናቸው ከተረጋገጠ፤ ሽፋን ለሚሰጠውም ቡድን ይሁን ህዝብ ማህከል ገብተው ህዝቡን የሚረብሹትን ሁለቱንም መንገስት የሚወሰደውን እርምጃ በግልጽ ካሳወቀ በኋላ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ መውሰድ አግባብ ይሆናል፡፡

ይህ ምስቅልቅል የፖለቲካ ሆኔታ አረጋግቶ መፍትሄ እንደመፈለግ ፤ሌላው የፖለቲካ ደዋሪው ጀዋር  ፤ አንዴ አክቲፊስት ፤ አንዴ የፖለቲካ ፓርቲ መሪ፤ ሌላ ግዜ ደግሞ የሚዲያ ሃላፊ ፤ ሌላ ግዜ ደግሞ ህዝቦችን አጋጪ ፕሮፓጋንዳ ረጪ፤ መልሶ ደግሞ የህዝብ አስታሪቂ፤ በቅርብ ባደረገው ንግግር ደግሞ ኦነግና መንግስት የተስማሙበትን ስምምነት አዋዋይና ተርጓሚ ሆኖ ቀርቧል፡፡ በአሁኑ ትንተናው በመንግስትና በኦነግ መሃከል የተደረገው ስምምነት ኦነግ ተዋጊዎች ትጥቅ እንዲፈቱ ሳይሆን የኦሮሞ ፖሊስ ጋር እንዲዋህዱ ነው የሚል ዉጅንብር እየፈጠረ ነው፤ማለትም መንግስት የኦነግን ወታደሮች ደሞዝ ከፍሎ የኦነግ ፖሊስ ያደርጋቸዋል፤ ይህ ክሆነ ግንቦት ሰባትም ወታደሮቹ መንግስት እየከፈላቸው የግቦት ሰባት ፖሊሶች ሆነው ይቀጥላሉ ማለት ነው   ፡፡ ይህ በመንግስት ውስጥ የፖለቲካ ወታደሮችን መሰግሰግ ለሚሰገስጉት የፖለቲካ ቡድኖች የሂሳብ አወራረዱ ግልጽ ቢሆንም፤ ሀገርን የሚጠብቅ ብሄራዊ ወታደርና የአካባቢ ሰላምን የሚጠብቅ ፖሊስ ከፖለቲካ ተጽእኖ ነጻ የሆኑ አቋሞች መሆን እንዳለባቸው የፖለቲካ ሳይንቲስት ነኝ እያለ ለሚመጻደቀው ጀዋር ጠፍቶት አይደለም ነገር ግን ቀደም ብሎ እየደጋገመ እንደነገረን የረጂም ጊዜ ፕላኑ ውስጥ ካሉ ተግባራዊ ከሚያደርጋቸው ክንዋኔዎች መሃከል አንዱ ስለሆነ ብቻ ነው፡፡

Filed in: Amharic