>

የህወሀት- ሱዳን - ቱርክ የሶስስትዮሽ ስትራቴጂ!!!

የህወሀት- ሱዳን – ቱርክ የሶስስትዮሽ ስትራቴጂ!!!
ናስትሮዳሙስ ኪንግ
ሀገራችን ውስጥ በኮንትሮባንዲስቶች እየተከማቸ ያለው የጦር መሣሪያ የሚገባው በሱዳን በኩል ሲሆን የሚመጣው ደግሞ ከቱርክ ነው፡፡ ቱርክ እና ሱዳን የህወሀት ቁጥር አንድ ወዳጆች ናቸው፡፡ ሁለቱም ከአገራችን መተራመስ ማትረፍ ይፈልጋሉ፡፡  ቱርክ   በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የራሷን ወታደራዊ ቤዝ በመመስረት አካባቢውን ለመቆጣጠር ትፈልጋለች፡፡ ይህን እውን ለማድረግ ቱርክ ከህወሀት ጋር ሥር የሰደደ ግንኙነት መሥርታልች፡፡ መቀሌ ላይም ከፍተኛ ኢንቬስትመንት አላት፡፡ ወደ መቀሌ የሚወስደው የባቡር ዝርጋታ፣ የሞሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ፣ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ በህወሀት እና በቱርክ የሚከናወኑ የጋራ ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡ ህወሀት ባለፉት አሥር ዓመታት ከዓለምአቀፍ አበዳሪዎች ለኢትዮጵያ ከተሰጠው ብድር ወደ 12 ቢሊዮን የሚጠጋውን ወደ ውጭ ያሸሸ ሲሆን ይህ ገንዘብ በኢንቬስትመንት ሰበብ በቱርኮች እና እንግሊዞች አማካኝነት ወደ ትግራይ እየገባ ነው፡፡
ሱዳን ደግሞ የኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማርምን መንግሥት ከህወሀት ጋር ሆና በቀጥታ ከመዋጋቷ በተጨማሪ ህወሀት የምስራቅ አፍሪካ አተራማሽ ሓይል እንዲሆን ጠንካራ ድጋፍ ስትሰጥ ቆይታለች፡፡ በምትኩም ህወሀት ለሱዳን 1600 ኪሎሜትር ርዝመት ያለውን መሬት ከጎንደር እና ከምስራቅ ወለጋ ቀንሶ ለመስጠት ውስጣዊ ስምምነት አድርጓል፡፡ ይሁን እንጂ በፈጣሪ ኃይል የኢትዮጵ መሬት አሁንም በአርሶ አደሮች እየተጠበቀ ነው፡፡
 ስልሆነም ሳውዲ አረቢያ፣ አረብ ኤምሬቶች እና ግብጽ ኢትዮጵን እና ኤርትራን  በመደገፍ የቀይ ባህር   አካባቢ ለራሳቸው ጥቅም ለማዋል እየሰሩ ሲሆን በአንጻሩ ቱርክ፣ ካታር እና ሱዳን ደግሞ ህወሀትን በመደገፍና  የየመን ሁቲዎችን በማስታጠቅ ቀይ ባህርን ለመቆጣተር ይጥራሉ፡፡ ስለሆነም ህወሀት ከሱዳን እና ቱርክ በኮንትሮባንድ በገፍ እያስገባው ያለው የጦር መሣሪያ ወደፊት የተለያዩ ኃይሎች ልክ እንደ የመን ኢትዮጵያን የጦር አውድማ ለማድረግ እና በዚህ መሀል ደግሞ እንደ ሶማሌ ላንድ ሁሉ ትግራይም የሰላም ኮሪዶር እንድትሆን እየተሠራ ስለሆነ ይህን የረቀቀ ሴራ ማክሽፍ የሁሉም ኢትዮጵዊ ግዴታ ነው፡፡
Filed in: Amharic