>

ለመሆኑ በፖሊስ ኮማንደር ደረጃ "የእኛ ልጆች" የሚባሉት እነማን ናቸው?!? (ብርሀኑ ተ/አረጋይ)

ለመሆኑ በፖሊስ ኮማንደር ደረጃ “የእኛ ልጆች” የሚባሉት እነማን ናቸው?!?
ብርሀኑ ተ/አረጋይ
“ዝም ብለህ መፈታትህን አመስግን ድጋሚ ላለመግባትህ እርግጠኛ ነህ? እንዲያውም የኛ ልጆች እስር ቤት ሆነው እናንተ መፈታታችሁ ገርሞኛል”
የአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ሀላፊ ኮማንደር አበራ ቡሊና 
መስከረም 9/2011 ከወዳጄ መኮንን ለገሰ ጋር በፖሊስ በህገወጥ መንገድ በተያዝኩበት ወቅት ለስራ ይዤው የነበረው 50.000 ብር በፖሊስ ኤግዚቢት ተይዞ የነበረ መሆኑ ይታወሳል ከ7ቀናት ቆይታ በኋላ (ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ ውይይት ወቅት እንደተናገረው) ከፖሊስ ጣቢያ ወደ ቤተ መንግስት ተወስደን ከጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አህመድ ጋር ተነጋግረንና በራሳችን ፊርማ እንደምንፈታ ተነግሮን በወጣንበት ወቅት ንብረታችንና ገንዘባችንን በማግስቱ እንድንወስድ ቢነገረንም ከአድካሚና አሰልቺ ምልልስ በኋላ ሞባይልና ላፕቶፖቻችን ተመልሰውልናል።
በወቅቱ ለስራ ይዤው የነበረው 50.000 ብር ግን በተደጋጋሚ እየተመላለስኩ ብጠይቅም “አቃቤ ህግ ይወስን ያላጣራነው ነገር አለ እንዴት እንደተፈታችሁ አልገባንም” ወዘተ በሚል ተልካሻ ምክንያት ሲያመላልሱኝ ቆይተው ዛሬ ከሰአት ልጠይቅ በሄድኩበት ወቅት የአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ሀላፊ ኮማንደር አበራ ቡሊና “ዝም ብለህ መፈታትህን አመስግን ድጋሚ ላለመግባትህ እርግጠኛ ነህ? እንዲያውም የኛ ልጆች እስር ቤት ሆነው እናንተ መፈታታችሁ ገርሞኛል” ወዘተ በሚል የእብሪት ንግግር ድጋሚ ገንዘቡን ለመጠየቅ እንዳትመጣ ብለው መልሰውኛል።
 ለመሆኑ ገንዘቡ ቢወረስ እንኳን ህጋዊ ደረሰኝ መስጠት አያስፈልግ ይሆን? ኮማንደሩ የኛ ልጆች ሳይፈቱ…. ያሉትስ እነማንን ይሆን? ይሁን አስኪ ገንዘባችንንም ተነጥቀን ለማስፈራሪያው እያሟሟቅን ነው!!!
Filed in: Amharic