>

ወጋገን ባንክ በሽልማት ስም የኦ.ዴ.ፓን እና የአ.ብ.ዴ.ፓን ገንዘብ እያሸሸ ነው!!! (ሚኪ አምሀራ)

ወጋገን ባንክ በሽልማት ስም የኦ.ዴ.ፓን እና የአ.ብ.ዴ.ፓን ገንዘብ እያሸሸ ነው!!!
ሚኪ አምሀራ
ወጋገን ባንክ በሚቀጥለዉ ሳምንት የባለአክሲወኖች ስብሰባ አለዉ፡፡ የባንኩ የኮርፖሬት ህግ እንደሚለዉ ሃላፊ ለነበሩ ሰወች ሲወጡ ስጦታ እንዲሰጣቸዉ አይፈቅድም፡፡ እናም የወጋገን ባንክ የቦርድ ሰወች ለባለአክሲዎኑ ሳያሳዉቁ የሚከተሉትን ስጦታወች ለሚከተሉት ሰወች ለመስጠት በጓሮ በር እየሰሩ ነዉ፡፡
የወጋገን ባንክ ፕሬዝደንት ለነበረዉ አቶ አረያ ገ/እግዛብሄር በቅርቡ ከስራ ሰለሚሰናበት የ 11 ሚሊየን ብር ዘመናዊ መኪና ለመስጠት ታቅዷል፡፡ በዚሁ አብሮ ለሚሸኘዉ ወልደገብርኤል ወዳጆ የ 3 ሚሊየን ብር መኪና ይሰጣል፡፡ ስብሃት ነጋ ለረዥም ጊዜ የወጋገን ባንክ ቦርድ አባል ስለነበር የ 4 ሚሊየን ብር ጥሬ ገንዘብ ይሰጣል፡፡ የማነ ግርማ የተባለ ሰዉ የዛሬ 2 አመት በፊት በ 3 መቶ ሚሊየን ሙስና ተከሶ ታስሮ ነበር፡፡ አሁን ሸሽቶ አሜሪካ የሚገኝ ሲሆን ከመንግስት በጀት አጉድሏል የተባለዉን ያህል ወጋገን ባንክ የተወሰነዉን ለመክፈል አቅዷል፡፡
ወጋገን ባንክ ገንዘብ መርጨት ብቻ ሳይሆን  ያሳሰበኝ እና ለመጻፍ የተገደድኩት እዚህ ባንክ ዉስጥ ትልልቅ አክሲዎን ካላቸዉ ድርጅቶች ዉስጥ የእነ በረከት መፈንጫ የነበረዉ አምባሰል ንግድ ስራዎች እና ሌሎች የጥረት ድርጅቶች ይገኙበታል፡፡ይህ ሀብት ደግሞ የአማራ ህብት ነዉ፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን አካዉንታቸዉ እራሱ እዚህ ባንክ ዉስጥ ነዉ ያለዉ፡፡
ደሚቱ የሚባል የኦሮሚያ አካባቢ ድርጅትም ትልቅ ሸር እዚህ ባንክ ላይ አለዉ፡፡ ሸሩን ሽጦ ለመዉጣት ለባንኩ ማመልከቻዉን አስገብቷል፡፡ ስለዚህም የእነጥረትን ገንዘብ መኪና መግዣ እያደረጉት ነዉ፡፡ የክልሉ መንግስት ጥረትን ተረክቢያለዉ ብሏል፡፡ ይሄን የአማራን ህዝብ ንብረት ህዝቡን እንዲያገለግል ማድረግ አለብን፡፡ ሀብታችን ለጠላት የምናበላበት ጊዜ አልፏል፡፡እናም መረጃዉን ለባለአክሲወኖቹ ማድረሴ ነዉ፡፡
Filed in: Amharic