>

"በአጥንትና ደሜ ምዬ የምናገረው  ከኢትዮጵያውያን ከተስማማንበት ቀን የላቀ ደስታ የለኝም!!!" (አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ)

“በአጥንትና ደሜ ምዬ የምናገረው  ከኢትዮጵያውያን ከተስማማንበት ቀን የላቀ ደስታ የለኝም!!!”
አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ:  “ለCGTN, Arabic Survive ከሰጡት ቃለምልልስ የተወሰደ!!
(በአማርኛ ተርጉሞ እንደቀረበው)”
“…በሕይወትህ የተደሰትክበት ቀን ላልከኝ፣ እንደ መሪ ሳይሆን እንደ ግለሰብ ብዙ ማለት ይቻላል። ዩንቨርስቲ የገባህበት፣ ትዳር የያዝክበት፣ ልጅ የወለድክበት፣ ደርግ የወደቀበት ወዘተ ወዘተ። #በአጥንትና_ደሜ_ምዬ የምናገረው ግን አሁን ከኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን ከተስማማንበት ቀን የላቀ ደስታ የለኝም። ለዚህም አብይን ላመስገነው እፈልጋለሁ። እኔ አርጅቻለሁ ብዙ ዘመን የለኝም፣ በአብይ አመራር ግን የወደፊቷ ኤርትራ ጉዳይ አያሳስበኝም። ወያኔ ብዙ ቢናገርም እኛ ለኢትዮጵያውያን ነፃነት እንጂ ክስረት አስበን አናውቅም እመነኝ እኔ #አላስመስልም_አልሰርቅም።”
” ሃያ ሰባት ዓመት ስለ አማራ ክፋት ተናግረን አማራው እንዴት በፍቅር እንደ ተቀበለን ሳይ አንገቴን ደፋሁ። ኢትዮጵያውያን ለኛ ያላቸውን ንፁህ ፍቅር በሕይወቴ ሳለሁ ቆሜ ከማየት በላይ ምን ደስታ አለ?”
“ሆኖም በኢትዮጵያ ወንድሞቻችን ላይ እዛም እዚህም ሞት አለ፣ ይህን እያየን እኛም በሰላም አንተኛም፣ የተሟላ ሕብረት አይኖረንም። ይህን የከሳሪዎች ሴራ ደግሞ ግዜ ቢፈጅም እናሸንፋለን። እኛ ኤርትራውያን ለወንድሞቻችን ሰላምና ደህንነት ጦር፣ ጉልበት፣ ግዜ ብቻ ሳይሆን በግሌ ሕይወቴን ለመስጠትዝግጁ ነኝ። ይህ እምነቴ ነው፣ በነፍሴ የምምለው ውሸት የሌለበት እውነት ነው።”
Filed in: Amharic