>
5:16 pm - Saturday May 23, 7418

ጎንደርና አካባቢዋ፤የአዴፓ የአማራ ክልል መንግሥት ጀሮ ዳባ ልበስ ዝምታ!! (መንገሻ ዘውዱ ተፈራ)

ጎንደርና አካባቢዋ፤የአዴፓ የአማራ ክልል መንግሥት ጀሮ ዳባ ልበስ ዝምታ!!
መንገሻ ዘውዱ ተፈራ
ህወሀት  ሳያስበው ያገኘውን በኢትዮጵያ የበላይነት የሚያከናውነው፤ልጅን ከወላጁ፤ሚሰትን ከባሏ፤ጎረቤትን ከጎረቤት፤መንደርን ከመንደር፤አካባቢን ከአካባቢ በማጋጨት ሰለመሆኑ ማብራሪያ አያስፈልገውም።
የጎንደርን አቅም ለማሳሳትና በዙሪያው የወረሩአቸውን ሊወሩአቸው ያቀዱትን መሬቶች 1967 ማንፌስቶ ማስከበሪያ ድብቅ ስልቶች ለማሳካት መጀመሪያ ረድ እሰከሚንጣቸው የሚፈሩትን የጎንደር ህዝብ የራሱ የቤት ሰራ መስጠት ነው። በዚህ ቁስል ሰጥተህ አሱ ሲያክ አንተ ብላ ዘዴያቸውም፤በማንኛውም መስፈርት ምንም ልዩነት የለለውን፤አማራና ቅማንትነቱ ውበቱ፤ጌጡና ሀብቱ አድረጎ በጎንደሬነት በወንድማማችና አህትማማችነት የሚኖረውን ለማዋጋት ቅማንቱነ በተጠናጥል አንደተጎዳ በመስበክ የማንነት ጥያቄ እንዲነሳ በማድረግ በማን አባቱ ገደል ገባ ሊያዋጉን ላይ ታች ይላሉ።
እኛ  አዴፓ አሁን ነፃነት አለው ብለን እንገምታለን አዴፓም ነፃ ነኝ ኩሩብኝ ብሎ ነበር። ታዲያ ይህ እውነት ከሆነ በሁለቱ ወንድማማቾች አማራና ቅማንት እየተከናወን ያለውን ዘር አጥፊ ዘመቻ እንደአልሰማ አድርጎ ዝም ማለቱ እኮ አጅግ አሳፋሪ ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው። ለዚህም ማስረጃዎቹ፦
1. ከመጀመሪያው ህወሀት እራሱ ባመጣው የዘር ፖለቲካ ለእራሱ የቀረበለትን ከአራት በላይ የማንነት ጥያቄ ሳይመልስ፤አዴፓ የማንነት ጥያቄው ህዝብ የመከረበትና የተስማማበት ተገቢ ነው ብሎ እንደሰጠ፤እንደ ክልል መንግሥትነቱ የማንነት እውቅና ለሰጠው አካባቢ ቀሪ ጥያቄ ካለ በሂደት አንደሚመለስ በመግለፅ የማንነት ባለቤቶቹን ተጠግቶ በመርዳት በማገዝ የማቋቋም ግዴታውን በስዓቱ መወጣት ነበረበት። ለዚህ ፈቃደኛ የማይሆን ህዝብና ህዝብ እንዲዋጋ የሚፈልግ ካለ ደግሞ ለይቶ ለህዝብ አቅረቦ ጉዳዩን በግልፅ ማስፈፀም ሲገባ እንዲህ ለዓመታት ማንዘላዘልና ችግሩ አስከ አሁን አንዲቆይ ማድረግ፤
2. ከሁለት ወር በፊት በጭልጋ ወረዳ ላዛ አካባቢ፤ አርባ ቤቶች ሲቃጠሉና በአማካይ የቤተሰብ ብዛት 4 160 ቤተሰብ ለችግር ሲጋለጥ ለችግሩን እርምጃ አለመወሰዱ ድንገተ ተወሰደ እርምጃም ካለ ስለ ተወሰደው እርምጃ ለአካባቢው ህዝብ እንዲታወቅ በማድረግ ስህተቱን አንደይቀጥል አለመደረጉ፤
3. ከዚያ በመቀጠል ከመተማ እና ሌሎች አካባቢዎች አስፈፃሚ የመንግሥት ሰራተኞች በማንነታቸው ከስራ ገበታቸው ሲፈናቀሉ ከቦታው ቶሎ ደርሶ እልባት አንደመስጠት ተፈናቃዮቹንና ተሰዳጆቹን እየተቀበሉ በሽራ አንደኖሩ ማገዝ፤
4. መጨረሻ ከህዳር 19/2011ዓ/ም ጀምሮ ህግ፣ ህግ አስከባሪና፤አስፈፃሚ ባሉበት ሐገር፤በአደባባይ በድምፅ ማጉያ(ቋራ ገለጉ ከተማ) እየተከናወነ፤በአንዳንዶቹም ሰው እየሞተ፤አሁንም በጎንደር ከተማም ወረቀት እየተበተነ የአዴፓ ዝምታ አጅግ ግራ የሚያጋባ ነው።
ከዚህም በመነሳተ፤አዴፓ አሁንም የህወሀት አጅና ትዕዛዝ ያለበት የጉዳዩ ጠንሳሽ፤ፈፃሚ እራሱ  ይሆን?  ኃላፊነትን ባለመወጣት በህዝብ አስጠያቂነቱን ለመረዳት የአቅም ክፍተት ስለአለበት ይሆን?ወይስ የነበረው የኢህአዴግ ስርዐት እንዲጠፋ አይፈለጉ ይሆን? ወደ ይሆን? የጥርጣሬ ጥያቄ እያስገባን ይገኛል።
በመሆኑም አሁንም እኛ ተቀምጠን እናንተ ምን አገባችሁ ካላላችሁ፤ በእኛ እሳቤ እንደ አባት አደሩ መሰረታዊ መፍትሔ የሚሆነው፤በአካል ቀጥታ ጎንደር ተግኝታችሁ፦
 1.ጉዳዩ የሚመለከታችውን ከጎንደር ከተማ፣ላይ አርማጭሆ፣ ጭልጋ፣ መተማ፣ ቋራ ወረዳዎች ከሚገኙ ቀበሌ አስተዳደሮች፤ ከእያንዳንዱ ቀበሌዎች ተወካዮችን በማስመረጥ፤ከማህበረ ስላሴ፤ሌሎች ገዳማትና፤አብያተ ክርስቲያናት፤በአካባቢው ካሉ መሰጊዶች ተወካዮች በማሰባስብ ውይይት ማድረግና ወደ ጋራ መግባባት ማምጣት ነው።
2.ከዚያም ከእነዚህ ህዝብ ውክልና ከተቀበሉ ጋር በተደረገው ውይይት የተደረሰበትን የጋራ ውሳኔ መሰረት በማድረግ፤በየወረዳዎቹ በመመዳዳብ፤ይህን የጋራ ውይይት ወደ ሕዘብ ማውረድና የጋራ በማድረግ አልባት ማስቀመጥና፤ይልቅስ ምሽግ ቆፍሮ፤ ጦር መሳሪ ያስጠጋውን ቀዳሚ ጠላታችን ህወሀትን ማሳታገስ ነው።
ከዚህ ውጭ አሁን በጎንደርና አካባቢዋ ሚገኘውን ሁኔታ፤አዴፓ የአማራ ክልል መንግሥት ጀሮ ዳባ ልበስ ዝምታ እንወጣዋለን ኃሳብ፤ የተዳፈነው አሳት ይግምና ማንንም ሳይለይ ማቃጠል ሲጀምር ሁላችንም በየአለንበት ምን ነው ባልተወለድን አንደሚያሰኘን መገመት ብልህነት መሆኑን ተረድቶ ወደ እርምጃ ቢገባ ጠቃሚነቱ የላቀ መሆኑን ለማሳየት ነው።
ጎንደርን ፈጣሪ ጠብቆ የተለመደውን የሐገር ኃላፊነት አንድትወጣ ያድርጋት።
ኢትዮጵ በክብር ለዘላለም ትኑር።
Filed in: Amharic