>
4:45 pm - Friday August 19, 2022

አደሬው የደህንነት ቁልፍ ሰው -  ዶ/ር ሀሺም ቶፊክ !!! (ሰይፈአርድ አምደ ጽዮን)

አደሬው የደህንነት ቁልፍ ሰው –  ዶ/ር ሀሺም ቶፊክ !!!
ሰይፈአርድ አምደ ጽዮን
 
እራሱን ከቀንደኛው ለገሰ ዜናዊና ጌታቸው አሰፋ በስተቀር ከማንኛውም ሊቀሰይጣን ወያኔ በላይ ወያኔ አድርጎ ያይ ነበር!!!
* በአንድ ወቅት ጌታው ሊቀሰይጣን ወያኔ ለገሰ ዜናዊ የፍትህ ሚንስትር ዴታ አደረገው ብዙም ሳይቆይ በአቅም ማነስ ተብሎ ወዲያው ተነሳ::
* በግርማ ወልደጊዮርጊስ ጊዜ የፕሬዚደንቱ የህግ አማካሪ ተብሎ ነበር!!!
* የተሰነዩ ህገመንግስት ተብዬ ጥራዝ የሊቀሰይጣን ወያኔ ማንፌስቶ ክርክር ሲያጋጥም 7 ተርጏሚዎች ከተባሉት ውስጥ አንዱ እየተባለ ቩቩዜላ ይነፋለት ነበር!!!
* የኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሌጅ ዋና ዳይሬክተር ተብሎ የምክትል ዳይረክተሩ በአዲሱ የፖሊስ ማዕረግ ረዳት ኮሚሽነር በድሮው ብርጋዴር ጀነራል ፀጋዬ ዳዳ አለቃ ሆኖ ነበር:: ፀጋዬ ዳዳ ግን እንቁ አልማዝ ኢትዮጵያ ያፈራችው ምርጥ በሳል ምሁር የፖሊስ መኮንን ነበር!!! ቀኑን ሙሉ ስትሰማው ብትውል የማትሰለቸው ብቻ ሳይሆን ፍፁም የማይጠገብ ቋንቋው ምግብ ነበር!!! እግዚአብሔር አፈሩን ያቅልለለት: ነብሱን ይማረውና ከኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሌጅ ለቆ በኬኒያ አንድ ትልቅ አለም አቀፍ የሰላም ተቋም ውስጥ በውጭ ምንዛሬ በከፍተኛ ደሞዝ ተቀጥሮ እየሰራ እያለ በድንገት ታመመ ተብሎ በ2006 ዓ/ም ሞተ!!!
• ታዲያ በ1996 ዓ/ም ሀሺም ቶፊክ የኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሌጅ ዋና ዳይሬክተር ለስም በነበረበት ወቅት ለገዳዲ ከተማን መሃል ለመሃል ሰንጥቆ  በሚያልፈው አስፓልት ላይ ከሰንዳፋ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሌጅ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ላይ እያለ በመንግስት መኪና እየተክለፈለፈ በእብሪት ከፍጥነት ወሰን በላይ እያሽከረከረ ሲመለስ አንድ የ9 አመት እንቦቀቅላ ህፃን ልጅ ገጭቶ ገድሏል!!!
ጉዳዩ እድሜ ለዶክተር ኮማንደር ታደሰ ቤካ በወቅቱ የኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሌጅ የጥናትና ምርምር መምሪያ ሀላፊ በነበሩት የአሌልቱ ሸኖ አካባቢ ተወላጅ ገራሚ ሲኒየር የፖሊስ መኮንን አመካኝነት በሽምግልና እንዳለቀ ይታወቃል!!!
ከዛ የኢትዮጵያ ፖሊስ  ኮሌጅ ሀላፊነቱ ወይም ዳይሬክተርነቱ አበቃና በቀጥታ እንደናቱ ቤት ወደሚያየው የአፈና ተቋሙ እንደክብር እቃ ተመለሰ!!!
የኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሌጅማ አይደለም ሀሺም ቶፊክ የሀሺም ቶፊክ አይነት አንድ ሺህ ግልብ ሰው መተካት ወይም በእውቀትና ልዩ ብቃቱ እንዲሁም ችሎታው መለወጥ የሚችለው ረዳት ኮሚሽነር (ብርጋዴር ጀነራል) ፀጋዬ ዳዳ አይደለም የኢትዮጵያን ፖሊስ ኮሌጅ ኢትዮጵያን መምራት በሚያስችለው እውቀቱ እዛው ተምሮ እዛው በክብር ተመርቆ እዛው እስተማሪ ሆኖ እዛው ኖሮ ምክትል ዳይሬክተር ተብሎ ከመጀመሪያውም ወርቅ አድርጎ ሲመራው ነው የኖረው!!!
* ሀሽም ቶፊክ ግን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በብሔራዊ መረጃና ደህንነት ስር ካሉት 5 ዋና መምሪያዎች ውስጥ የአንደኛው ማለትም የቴክኒክ እና መረጃ ዋና መምሪያ በተለምዶ ሊቀሰይጣን ወያኔ ክንፈ ትምህርት ቤት የሚለው በአንድ ጎፍጫላ ሌላ ሰው ስር ምክትል ዋና መምሪያ ሀላፊ ነበር: ለግፍ ዝናብ አዝናቢው ለሊቀሰይጣን ወያኔ ጌታቸው አሰፋም ፍፁም ታማኝ መሆኑ እጅግ ባለጌና እጅግ አደገኛ በዘር ጥላቻ ያበደ ሰው ነበር!!!
ዘረኛነቱን ሳስበው ሁሌም ከአዕምሮዬ የማልዘነጋው እና ሊቀሰይጣን ወያኔ ወድቆ በህይወት ኖሬ አይቼው እል ነበር!!!
በዘረኛነቱ ከሀረር ተነስቶ በደህንነት መዋቅሩ ታቅፎ በዚሁ ሰይጣናዊ የአፈና ተቋም ውስጥ እረጂም ጊዜ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የጭካኔ በትር አሳርፏል ብልግናውም ከሊቀሰይጣን ወያኔ በላይ ይሆናል እንጂ አያንስም!!!
በተለይ በፀረአማራነት: በፀረ አዲስአበቤነት: በፀረአርንጏዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅዓላማ እና ጥላቻው የሚወዳደረው አለ ብዬ በፍፁም አልገምትም!!!
> በአንድ ወቅት የወንጀል መከላከል ተብዬው እኛ የወንጀል ማምረቻ ተቋም የምንለው እና የፌደራል ፖሊስ አመራር ተብዬ የደደቢት ሚሊሻ ጥርቅም እነግርማይ ማንጁስ (ግርማይ ከበደ) እነተክላይ ፀሐይ ሌሎችም ባሉበት መድረክ ስብሰባውን ሊመራ ሲገባ በሚቀመጥበት ወንበር ፊትለፊት ባለው ጠረጴዛ ላይ የተነጠፈው ሰንደቅዓላማ የኢሉሚናቲ አርማው የሌለው ንፁሁ የኢትዮጵያ የዘመናት መለያ የነፃነት አርማ የአዕላፍ ጀግኖቻችን መታሰቢያ እንቁ ሰንደቅዓላማችን ነው ይህን ገና በተዘጋጀለት ወንበር ላይ እየተቀመጠ እያለ የተመለከተው ሊቀጂኒው ሀሺም ቶፊክ በአንድ እጁ ጠላቱን ዘሎ እንደያዘ ጀግና አፈፍ አድርጎ ከጠረዼዛው ላይ በብሽቀት ጠቅልሎ በማንሳት በንቀትና በከፍተኛ ጥላቻ ከፍዝቅ አድርጎ ሰንደቅዓላማውን እንደሰው ተናገረ ሳይሆን አቀረሸበት ማለቱ ይቀላል!!! ታዲያ በቦታው የነበሩት ዋነኞቹ የሊቀሰይጣን ወያኔ አባላት “ዋይ ይሄ ሰውዬ እኮ ከእኛም ልብለጥ አለ?! ምንድነው እስከዚ ድረስ ጥላቻ? ሰንደቅዓላማው እኮ እውነት እንነጋገር ካልን የእኛም አባቶች እና አያቶች ሞተውለታል ዋይ አሁንስ አበዛው” ማለታቸው አይዘነጋም!!!
ከሊቀሰይጣን ወያኔ ለገሰ ዜናዊ እና ጌታቸው አሰፋ ጋር እስከመጨረሻው ያስተሳሰረው ይኼው ጫፍ የወጣ ብልግና እና እጅግ ዘረኛነቱ ትበር!!!
Filed in: Amharic