>
6:30 am - Tuesday July 5, 2022

ወቅታዊ ሁኔታዎች በሚመለከት ከትግራይ ክልል መንግስት  የተሰጠ መግለጫ!!!

ወቅታዊ ሁኔታዎች በሚመለከት ከትግራይ ክልል መንግስት  የተሰጠ መግለጫ!!!
ትርጉም ኪዳኔ አፈወርቂ
ከሃዋሳው የኢህአዴግ_ጉባኤ ጀምሮ “ህወሓት ውስጥ የእነ ደብረፂዮን ቡድን ተደምሯል! በቀጣይ መቀሌ የመሸጉትን ተጠርጣሪ ወንጀለኞች አሳልፎ ይሰጣል!” ስላችሁ አልሰማ ብላችሁ ይሄው ህወሓት በመግለጫው ሰርፕራይዝ አድርጔቾ እርፍ አለ፡፡ አሁን ያልተደመሩት ዘራፊዎችና ሌቦች፣ እንዲሁም የእነሱ ፍርፋሪ የሚቃርሙት ናቸው!
 
የትግራይ ህዝብና መሪ ድርጅቱ ህዋሓት ለፍትህና ለእኩልነት ሲል ከባድ መስዋትነትና ሁሉ ኣይነት ጉዳት ከፍለዋል።
ይህች አገር ገብታበት ከነበረው የቁልቁለት ጉዞ ለማዳን የተለየ መስዋትነት የከፈለና ለዚች አሁን ላለችው ኣገር ደህንነት ሲል ሰው ሆኖ ከሰው በላይ ደምተዋል፣ ተጎድተዋልም። እንደ ህዝብና እንደ ድርጅት ደግሞ በከፈልነው መስዋትነትና ባስመዘገብናቸው ድሎች እጅግ እንኮራለን።እንደዚህ ያለ መስዋእት የከፈለና የዚህ ከወርቅ በላይ የነጠረ ታሪክ ባለቤት ለሆነው ህዝብ መንግስትና ድርጅት ደግሞ የለውጡና የእድገት ባለቤት እንጂ የሁሉ ኣይነት ጥፋትና ድክመት ባለቤት ሊሆን ኣይችልም።
ከዛው ከመጀመርያው የበኩር ልጆቻችንና ታናናሾቻቸው መስዋእት የከፈልንበት ሚስጢር የተሻለ ሰላም ልማትና ዲሞክራሲ ፍትህ ለማረጋገጥ ኢዚች ሃገር  ብሄር ብሄረሰቦችና ሀዝቦች በእኩልነት የሚኖርባትና የሚከበሩበት ስርኣት ለመትከል ነው። በዚህ ከፍተኛ መስዋትነት የከፈልንበት ደግሞ እጅግ ልንኮራበት ኢንጂ ራሳችን ዝቅ የሚያስደርግ ጉድፍ የለንም። እንደ ህዝብ ማንኛውንም ጭቆና ባርነት እንደማንቀበል ሁሉ ለሌላ ህዝብም አንመኝም። ይሁን ኢንጂ ለውጡን ለማይፈልግ ማንኛውም ሃይል ፍጹም የማንበረከክ መሆናችንን ደግሞ የትናንትና ና የዛሬ የውደፊትም የማይነቃነቅ ቃልኪዳናችን ነው። እንደ ህዝብ የትግራይ መንግስትና ህዝብ ከላይና ከታች ኣንድ ወጥ ሆነን በሰላም በእኩልነትና በመቻቻል ለመኖር ስለምንፈልግ በቀዩ ደማችን በመስዋትነታችን ያረጋገጥንበት ለመሆኑ ዘመን ተሻጋሪ ታሪካችንን የሚመሰክረው ነው።
የተከበርክ የትግራይ ህዝብ
ለፍትህና ለሰላም ስትል ድምህን አፍሰሰሃል፣ ተጉድተሃልም። ዲሞክራሲዊ ስርእት ለመትከል ለፍትህና ለሀግ የበላይነት ከሁሉ በፊት ታግላሃል። ኣሁንም በመታገል ላይ ትገኛለህ ። እነዚህ መሰረታዊ ጉዳዮች ሲጣሱና ሲሸራረፉ ስታይም በፍጥነት ሁኔታዎችን ትገመግማለህ ፣ ታርማለህ። አቅምና ሁኔታዎችም በፈቀዱም ያለማመንታት በሙስና ጸረ ዲሞክራስያውነት ፍትህ ማጉደልና ሌሎችም ችግሮች ሲያጋጥሙህ ወስጥህን ፈትሽህ የማያወላውል ወሳኔ እንደምታሳርፍ በቅርቡ በተደረገው ግምገማ በጥልቀት መታደስ ያደረግሀው ትግል ምሳሌ ነው። ከታሪካችንም እንደዚሁ የመሰሉ ጉድለቶች ከማረም ውጭ ለድርድር አቅርበነው አናውቅም። አሁንም እንደ ህዝብ መንግስትና ድርጅት ከማንም ጊዜ በላይ ለህግ የበላይነትና ፍትህ እየታገልን እንገኛለን። አሁን በሚታዩ ያሉ ሃገራዊ ሁኔታዎችም ቢሆን ሙስናን ፍትህ መጓደል ሰብዓዊ መብትን ጥሰት የአንድ አከባቢ ወይም ብሄር ችግር አይደለም።በዚህ ምክንያት እኩልነት ባለበት አግባብ የህግ የበላይነት የሚረጋገጥበት በመግባባት ላይ የተመሰረተ በተመርጠና ጥቂት ማስተማርያ ሊሆን በሚችል በሁሉም ኣካባቢና በመላ ሃገራችን ለተፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ህገ መንግስታዊ ጥሰትና ሙስና በእኩልነት እንዲታይ በተደረገው  የኢሃደግ መድረኮች ኣጥብቀን ገልጸናል።ሃገራችን በእርቅና በይቅርታ እንደመነሻ ሆኖ ለምትወስዳቸው እርምጃዎች ወደሓላ እንደማይመለስ ሆኖ የህግ የበላይነት ሳይሸራረፍ እንዲፈጸም ጥብቅ ጥንቃቄ የሚጠይቅ መሆኑን በአጽንኦት ያምናል። እንደዚህ ሲታይ ደግሞ በማያወላውል ኣጥብቀን እንደምንታገል እናረጋግጣለን።
የተከበርክ የትግራይ ህዝብ
እስካሁን ያሳየሀው ትእግስት እያደነቅን ኣሁንም ሃገሪትዋ ያለችበትን ኣስከፊና ከባድ ችግር ወስጥ እንዳለች የሚካድ ኣይደለም። ለተጨባጭ ሁኔታዎች የተርዳህውንና የትንታኔህ ብልህነት ተጠቅመህ ኣንድነትህ በበለጠ በማጠንከር ባላማህ ጽና። ኣካባ።ቢህን በጥብቅና በማንኝውም ጠብቅ። የልማትና መልካም ኣስተዳደር ስራዎችህን አጠናክረህ ቀጥል። ለሚመጣው ማንኛውም ችግር እንደወትሮህ ከመንግስትህ ጋር ተሰልፈህ ተከላከል። ይህን እስካደረግህ የከባቢህ ደህንነትና መረጋጋት ክልልህና ኣገርህ ወደነበርበት መመለሱ አይቅሬ ነው።
የትግል ታሪክህ ጉዞ ያደርካቸው ትግሎች እጅግ ኣስከፊ የተወሳሰቡና ብቃል ለመግለጽም ሆነ ለመንገር የከበዱ ይትግል ኣጋጣሚዎች ሲሆኑ ሁሉንም እንደየኣመጣጣቸው በመመከት ሁልጊዜ ኣንጸባራቂና የሚያስመኩ ታሪኮች እንደፈጽምክ ነውና ኣሁንም በሚታዩ ችግሮች ና ሁኔታዎች ሳትንበረከክ መሰረታዊ ኣላማህንና መስመርህን ኣጠንክር። ኣንድነታችን ይበርታ። እንደሁልጊዜው የማንዘልቀው ችግር እንደሌለ ደግመን እናረጋግጥ።
ኣሁን የሚታዩ ያሉ ሁኔታዎች እውነት ቢሆኑም ኣዲስ ስጋትና ጥርጣሬ የሚፈጥር የማንኛውም ብሄር በተለይ የሚጠቃበት ሳይሆን በጣም በከፍተኛ ሃላፊነትና ጥንቃቄ መስመር እንዲያዝ ከማንኛውም በላይ የዲሞክራሲውያን ሃይሎች ብ/ብ/ ህዝቦች ኣገርንና እንደተለመደው የትግል ኣንድነት ኣጠንክረን እንድንታገል ብ/ብ/ መንግስት ትግራይ ጥሪ ያደርጋል።
ዘለኣለማዊ ክብርና ሞገስ ለሰማአታት
ብ/ክልል መንግስቲ ትግራይ
04/03/2011 አም
Filed in: Amharic