>

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 300 ሚሊየን ዶላር ጉድና ሜቴክ!!!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 300 ሚሊየን ዶላር ጉድና ሜቴክ!!!
ሚኪ አምሀራ
 
* ሌላዉን ጉድ ልንገራችሁ ባለፈዉ ተወልደ ፕሌን አለዉ ብያችሁ ነበር፡፡ እሱ ብቻ አይደለም የሜቴክ ሰወች እራሱ አላቸዉ፡፡ አባይ ሊዝንግ ሌላም አንድ ድርጅት አለ በእነዚህ ድርጅቶች ምክንያት የኢትዮጵያን አየር መንገድ ሎጎ አድርገዉ ስራ ሚሰሩ ብዙ አዉሮፕላኖች አሉ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማስፋፊያ አይታቸዉሁት ከሆነ በኢንተርናሽናል ተረሚናል በኩል የተሰራዉ ትንሽየ ማስፋፊያ 300 ሚሊየን ዶላር ነዉ የፈጀዉ ወየም ወደ 10 ቢሊየን ብር፡፡ ይህ ዋጋ አሁን ባለዉ የአለም ገቢያ መሰረት ትንሽየ ማስፋፋት ሳይሆን አንድ ራሱን የቻለ ደረጃዉን የጠበቀ ኤርፖርት ይገነባል::
ጉዳዩ እንዲህ ነዉ፡፡ኪሮስ አብርሃ የሚባል የህወሃት ሰዉ ነበር አሁን ሜቴክ የያዛቸዉን የመከላከያ ኢንደስትሪዎችን ይመራ ነበር፡፡ ከዛም ሰራርቆ ከወጣ በኋላ የራሱን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ አቋቋመ፡፡ ወደ ቻይና ሄደ እና እዛ ለይምሰል አንድ አነስ ያለ ድርጅት ጆይንት ቬንቸር ፈጠርኩ አለ፡፡ ይሄን ያረገበት ዋና አላማዉ የአየር መንገዱን ማስፋፊያ ከኋላ ሁኖ ለመስራት ነዉ፡፡ የጨረታዉን ኮንትራትም ከአቶ ተወልደ ጋር በመሆን እንዲያሸንፍ ሆነ፡፡ ኪሮስ አብርሃ ከጀርባ ሁኖ ትንሽየ ማስፋፊያ በ300 ሚሊየን ዶላር ከቻይና ኩባንያ ጀርባ ሁኖ ዘረፈ ማለት ነዉ፡፡
የኪሮስ አብርሃ ልጅ አብርሃ ኪሮስ ይባላል፡፡ ኖርዌ ይኖራል በኖርወይ አገር ዉስጥ ከ1 እስከ 10 ካሉት ባለሃብቶች ዉስጥ አንዱ ነዉ ይባላል፡፡ ዉሎ እና ኣዳሩ የካረቢያን አገሮች ላይ ነዉ፡፡ ወደ ኢትዮጵያ በየቀኑ ይመላለሳል፡፡ ዋና ስራዉ የህወሃቶችን ዶላር እየተቀበለ የካረቢያን አገሮች ባንክ ዉስጥ ማስቀመጥ ነዉ፡፡ ኖርዌ ዉስጥ ማስቀመጥ እይችልም፡፡ ገንዘቡን የሚያወጣዉ ከአየር መንገዱ በመመሳጠር ነዉ፡፡ እንዲሁም አየር መንገዱ በአዉሮፓ ባሉት የትኬት መሸጫ ጣቢያወች የሚገኘዉን ገንዘብ እዛዉ ያስቀርና አዲስ ላይ በኢትዮጵያ ብር ይከፈላል፡፡
ሌላኛዉ መረጃ ሰሞኑን ግር ግሩን ተጠቅሞ የፍራንክ ፈርት የአየር መንገዱ ጣቢያ ሰራተኛ 1 ሚሊየን ይሮ ይዞ ተሰዉሯል፡፡ ማኔጅመንቱ ተሰብስቦ ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ይልቁን ወሬዉ እንዳይወጣ ተስማምተዋል፡፡
ሌላዉን ጉድ ልንገራችሁ ባለፈዉ ተወልደ ፕሌን አለዉ ብያችሁ ነበር፡፡ እሱ ብቻ አይደለም የሜቴክ ሰወች እራሱ አላቸዉ፡፡ አባይ ሊዝንግ ሌላም አንድ ድርጅት አለ በእነዚህ ድርጅቶች ምክንያት የኢትዮጵያን አየር መንገድ ሎጎ አድርገዉ ስራ ሚሰሩ ብዙ አዉሮፕላኖች አሉ፡፡ ገንዘቡ ግን ገቢ ሚሆነዉ ለሜቴክ ሰወች ነዉ፡፡
Filed in: Amharic