>

በማስፈራራት ፖለቲካ አገርን መግዛት ጊዜው አልፏል!!! (ኤፍሬም ለገሰ)

በማስፈራራት ፖለቲካ አገርን መግዛት ጊዜው አልፏል!!!
ኤፍሬም ለገሰ
 
አገርንና ህዝብን የዘረፉና ያዘረፉ ግፍ የፈፀሙ ለፍርድ ይቀርባሉ ቦታቸው ከህዝብ ጋር ሳይሆን ካሊቲ፡ ቂሊንጦ ወዘተ የመሳሰሉት ማጎሪያ ቦታዎች ነው!
ሰሞኑን አንዳንድ የትግራይ ምሁር ነን ባዮች በአንድ ራስ ሁለት ምላስ ሆኑብኝ በአንደኛው በትንሹ ምላሳቸው በአገራችን እየተከሰተ ያለውን ለውጥና እርምጃ የሚደግፉ ይመስሉና በትልቁ ደግሞ መሰሪና መርዘኛ የሆነውን የህወሃት ቡድንና የትግራይ ህዝብን አንድ አድርጎ በማየት በአንድ ብሄር ላይ ያነጣጠረ አፈሳ እየተደረገ ነው እያሉ ይቃዣሉ።
ይህንንም የሚሉት የቡድኑ ተጠቃሚ በመሆናቸው እንጂ እንኳን ዛሬና ያኔ ወደ ደደቢት ሲገቡም የትግራይ ህዝብ ተቆርቋሪዎች አልነበሩም። እነዚህ ግለሰቦች በ”መምህር”” ገብረኪዳን ደስታ እና ተስፋዬ ገብረአብ የተቀቡ ይመስላሉ የጥላቻና የዘር ፖለቲካ ማስፈራራት ተጨምሮበት የሚነዙት ፕሮፓጋንዳ  ጊዜ ያለፈበት ህዝብ የተፋው ታሪካችንና ባህላችንን የማይመጥን የወደቀ ትረካ ነው። ይህን እውነት ምንም ቢቆይም ጀግናው የትግራይ ህዝብ እንደ ተረዳው የሚያሳየን እየወሰደ ያለው እርምጃና ወደፊትም በሱ ስም የሚነግዱትን አልጠግብ ባዮችና ነብስ ገዳዮችን ለፍርድ አሳልፎ እንደሚሰጥ አንጠራጠርም።
ለዚህም በቅርቡ በኢፈርት፡ ሜድሮክ እና በሌሎች  የዘረፋ መረብ ላይ በሚደረገው ህዝባዊ ዘመቻ እናየዋለን።  እነዚህ ዘራፊዎች በትግራይ ህዝብ ስም የተደራጁ ነገር ግን መጨረሻ የሌለውን የሀብት ማከማቸት  አባዜ የተናወጣቸው የሰው አተላዎች ናቸው።
የማፍያው የህወሃት ቡድኖች ማዕድን ከመዝረፉ አልፎ ወንዞችን ሃይቆችን የከርሰ ምድር ውሃን በመበከል በሰው በእንሰሳና በእፅዋት ላይ ያደረሱት ግፍ ይህ ነው የማይባልና ጠባሳው ለትውልዶችም ይተርፋል ይህን በተመለከተ የሻኪሶ፣ የአፋር፣ የወሎ ህዝብ ይመስክራል። መሬትን ለመቀራመትና እንደ ፋሺስት ግዛቱን ለማስፋት  ያጠፉው የህይወት ብዛት ቤት ይቁጠረው።
መራሹ የህወሃት ቡድን በአገራችንና በህዝባችን ላይ የሰራው ግፍ የትግራይን ህዝብ ስም በመጠቅምና እንደከለላ በመጠቀም  ነው። https://youtu.be/tqjvXNykf34
 http://news.bbc.co.uk/2/hi/africa/8535189.stm ህወሃት የህዝብን ሰቆቃና ሞት  ለፖለቲካ  ፍጆታ ለዘረፋ የተጠቀመ አረመኔ ቡድን ነው።
 ይህ ሁሉ ዛሬ አክትሞ  ህዝባችን የፍቅር የሰላና የአብሮነት ኑሮ እንጂ የጎጥ ፖለቲካ አጀንዳው ሆኖ እንደማያውቅ እያስመሰከረ ነው ለዚህም የትግራይ ህዝብ ከሌላው እህትና ወንድሙ የኢትዮጲያ ህዝብ ጎን በመሰለፍ አካባቢውን ከሌባና ከነብሰ ገዳይ እንደሚያጠራውና የሚመጥኑትን ለህሊናቸው የቆሙትን አመራሮችን ብቅ እንሚያደርግ እውን ነው።
 አገርንና ህዝብን የዘረፉና ያዘረፉ ግፍ የፈፀሙ ለፍርድ ይቀርባሉ ቦታቸው ከህዝብ ጋር ሳይሆን ካሊቲ፡ ቂሊንጦ ወዘተ የመሳሰሉት ማጎሪያ ቦታዎች ነው።
ኢትዮጲያ በልጆቿ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች!!!
አንድነት ሃይል ነው!!
ፍቅር ያሸንፋል!!!
Filed in: Amharic