>

"የሀገርህን ተስፋ እያየህ ብትሞትስ   ምን ችግር አለው?" (ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ)

“የሀገርህን ተስፋ እያየህ ብትሞትስ  ምን ችግር አለው?” – 
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
“… በተለያዩ ክልሎች ገና ይህ ለውጥ በደንብ ስር ያልሰደደባቸው ቦታዎች አሉ:: ብዙ የሚጠብቁን ስራዎች አሉ:: ከተባበርን ግን ይህ ስርዓት እንዲለወጥ የምንፈልግ ሃይሎች በአንድ ላይ ከሰራን … በአንድ ላይ ሆነን ዓይን ለዓይን ተያይተን [ለውጧን] እዛች ጋር እናድርሳት [ብለን ከሰራን]… ማን ስልጣን ያዘ የሚለው [ምንም ማለት አይደለም]:: በእውነቱ [ምንም ማለት አይደለም]:: እኔ ማንም ስልጣን ላይ ወጣ [ያን ያህል ትርጉም የለውም]:: ህዝብ የመረጠው [መንግስት] መፍጠር ከቻልን; ጎማው አንዴ እዚያ መሽከርከሪቱ ውስጥ እንዲገባ ካደረግን…ከዚያ በሗላ የፖለቲካ [ፍላጎት/ጥያቄ] አለኝ የሚል ሁሉ የፖለቲካ ስልጣን የሚገኘው በህዝብ ፍላጎት መሆኑን ተረድቶ በዚያ መሰረት የራሱን አስተሳሰብ ማስተካከል ከጀመረ እንደ ትውልድ ትልቅ ታሪክ የምንሰራበት ነው::
* ከዚህ በላይ ትልቅ ስጦታ …በግልህም እንደ [ስኬት] ከዚህ በላይ ትልቅ ነገር ያለ አይመስለኝም:: በእውነት ነው የምልህ … ሃብት ምን ዋጋ አለው? ሃብት ምንም ማለት አይደለም:: እንዲህ ዓይነት ትልቅ ነገር ሰርተህ ማለፍ …በጋራ..አንድ ሰው ብቻውን የሚሰራው ነገር አይደለም:: እነ [ዶ/ር] ዓቢይ ብቻቸውን አይሰሩትም:: ሁሉም ሰው በጋራ ሆኖ ይሄንን [የለውጥ ሂደት] እዚያ ቦታ ላይ ካደረስን … ከዚያ በሗላ እኮ የምትተኛው እንቅልፍ …ከዚያ በሗላ እኮ የምትኖረው የሰላም ኑሮ …የሀገርህን ተስፋ እያየህ ብትሞትስ ከዚያ በሗላ ምን ችግር አለው?”
* የአክራሪ ዱላ ተፈርቶ የነፃነት ትግል አይቆምም።
የያዝነው የሃገር ጉዳይ ነው የያዝነው ኢትዮጲያ የምትባል ሃገር ትኖራለች ወይስ አትኖረንም የሚል ጥያቄ ነው።
 * ሰዎችን በዘር ሰብስቦ ቁስላቸውን እየነካኩ በስሜት መንዳትና ማስጮህ ቀላል ነገር ነው፣ ነገር ግን የተለያየ ማህበረሰብ እንደ ሃገር አስተባብሮ ታግሎ ነፃነት ( ፍትህ ፣ እኩልነት፣ ዘላቂ ሰላም እና ዲሞክራሲ) ማምጣት ከባድ ስራ ነው።
ምንጭ:- ከ” ኢ. ቢ .ሲ ” ብርቱ ወግ” ላይ የተቀነጨበ 
በስንታየሁ ጫንያለው
Filed in: Amharic