>
6:26 pm - Monday May 16, 2022

ከአይሱዙ ረዳትነት ወደ ቢሊዬነርነት የተቀየሩት አቶ ዓለም ፍፁም ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ!  (በጋዜጠኛ አብዱረሂም አህመድ) 

ከአይሱዙ ረዳትነት ወደ ቢሊዬነርነት የተቀየሩት አቶ ዓለም ፍፁም ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ! 
በጋዜጠኛ አብዱረሂም አህመድ 
* የትላንቱ የአይሱዙ መኪና ረዳት የዛሬው ቢሊየነር ዓለም ፍጹም የሀብት እንቆቅልሽ በመጨረሻም ተፈታ!
 
ከሶስት ዓመታት  በፊት ከልብ ወዳጄ አሊ መኪ ጋር  ደቡብ አፍሪካ በምትገኘው መኖሪያችን  የእለት ዜናዎችን እየተከታተልን ነበር።  ዓሊ መኪ ያየው አንድ ዜና አስደንግጦት ግራ አጋብቷል።  ” 2.5 ቢሊዮን ብር የሚፈጅ ሆቴል በመዲናችን አዲስ አበባ እየተገነባ ነው!  ” ይላል ዜናው  ሆቴል መገንባቱ አልነበረም ወዳጄን ያስደነገጠው ። ያስደነገጠው ሆቴሉን የሚያስነገነባውን ግለሰቡን ያውቀዋል ። አቶ አለም ትላንት የመኪና ረዳት የነበረ ዛሬ ቢሊየነር መሆኑ ነው አስደንጋጭ የሆነበት ። ርግጥ ነው ሰው ከለፋ ከጣረ ባለሀብት መሆኑ የሚገርም አይሆንም። ይሁንና የሰውየው በድንገት ወደ ሀብት መተኮስ ከባለዘመኖቹ ጋር ጥብቅ ቁርኝት በመኖሩ መሆኑን ሚዛናዊ ወዳጄ ለአፍታም አልተጠራጠረም። እናም በሰአቱ ወዳጄ ስለ ሰውየው የሚያውቀውን መረጃ ነገረኝና ወደ ተለያዩ ዌብሳይቶችና አክቲቪስቶች  በመላክ መረጃው ለህዝብ ይፋ እንዲሆን አደርግን ።
እነሆ ዛሬ ሰውየው ከሜቴክ ጋር ሽርክና ፈጥሮ በፈጸመው ምዝበራ በዛሬው እለት ፍርድ ቤት ቀርቧል። የፍርድ ቤቱን ውሎ በጽሁፉ መጨረሻ ላይ የማስገባው ይሆንና በፈረንጆች በ2015 ለተለያዩ ዌብሳይቶች ጽፌ የላኩትን መረጃ በቀጥታ ላካፍላችሁ።
 ኦሮሚያ ክልል በኢሊባቡር ዞን ጉሬ ከተማ ከትግራይ ክልል መጥተው ነዋሪ የነበሩት አቶ ብርሃኔ ወልደጊዪርጊስ ወደ ኦሮሚያ ያቀኑት ከኢህአዴግ በፊት ነበረው ስርአት ነው፡፡ አቶ ብርሃኔም እንደማንኛውም ኢትዪጲያዊ ከኦሮሞ ተወላጆች ጋር እየነገዱ ይኖሩ የነበሩ ግለሰብ ናቸው፡፡ ግለሰቡ አይሱዙ የጭነት መኪና በገዙ ሰአት ንብረታቸውን የሚጠብቅላቸው ገንዘብ የሚቆጣጥርላቸው የቅርብ ሰው በማስፈልጉ የሚስታቸው ወ.ሮ አበባን ወንድም የሆነውን አቶ አለም ፍጹምን ከትግራይ የገጠር ክፍል ወደ ጎሬ ያስመጡታል አቶ አለም ፍጹምም ኢሊባቡር ዞን ጎሬ ከተማ ከመጡ በሁላ በአይሱዚ መኪና ረዳትነት ስራቸውን ቀጠሉ ይህም በ1985 -1989 ባለው ገደማ አካባቢ መሆኑ ነው፡፡ ከዚያ በሁላ አቶ ብርሃነ ወልደጊዪርጊስ ከነ ባለቤታቸው በአሁኔ ጊዜ በህይዎት የሉም:: የትግራይ ተወላጅ የሆኑት ኦቶ አለም ፍጹም ከረዳትነት ወደ ድንገታዊ ባለሃብትነት ያደጉበት ሚስጥር በኢሊባቡር ዞን ጎሬ ለሚያውቋቸው ሰዎች እጅግ አስገራሚ እና አስደናግጭ ሁኗል፡፡ አቶ አለም ፍጹም ከስርአቱ ሰዎች ጋር በፈጠሩት ቁርኝት ድንገታዊ ሀብት መመንደጋቸውን ቀጠሉ፡፡
-አለም ገነት የሚል የቤት ክዳን ቆርቆሮ ፋብሪካ ባለቤት ናቸው
-የብረታብረት ፋብሪካ እና የሶፍት ወረቀት ማምረቻ ለቡ ኢንዱስቱሪ ዞን የሚገኙ ናቸው
የተለያዩ ድርጅቶችም አሏቸው :: በመጨረሻም በቀለበት መንገድ ሃና ማሪያም አደባባይ አካባቢ የሚገኘውን ሪቬራ ሆቴል የተባለውን ገነቡ፡፡ ከዚያ የህወሃት ድርጅር የሆነው መከላከያ ኢንጅነሪንግ እጅግ በጣም በተጋነነ ከመጋነነም በላይ ከፍተኛ በሆነ ዋጋ ሪቨራ ሆቴልን ገዛቸው፡፡ ከዚያም ፊላሚንጎ ቦሌ መንገድ ላይ ለአዲስ ሆቴል ግንባታ የሚሆን ቦታ ተሰጣቸው :: ድሬ ትዩብ ስለ አዲሱ ሆቴል ስለሚሰራው ተከታዩን መረጃ በፎቶ አስደግፎ አውጥዋል ::
2.5 ቢሊዮን ብር የሚፈጅ ሆቴል በመዲናችን አዲስ አበባ እየተገነባ ነው!
ሆቴሉ ከአፍሪካ ቀዳሚው ያደርገዋል! (በተሻገር ጣሰው)
በአለም ገነት ንግድና ኢንዱስትሪ የሚመራው በመዲናችን አዲስ አበባ ፍላሚንጎ አካባቢ ባለ አምስት ሆቴልና ከአፍሪካ ቀዳሚ የሚያደርገው ሆቴል እየተገነባ መሆኑን የሆቴሉ ባለቤትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አለም ፍፁም ለጋዜጠኞች በሸራተን አዲስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ::
ሆቴሉ ባለ 27 ፎቅ ህንፃ ሲሆን 500 ዘመናዊ ክፍሎች 10ሊፍቶች እንደሚኖሩትም የተገለፀ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ሆቴሉ 30 ከመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን በአይነቱ ልዩ የሆነናና ከሁለት አመት በሆላ ስራው ሲጠናቀቅ ለ1ሺህ 500 ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጥር አቶ አለም ተናግረዋል::
——
የሚገርመው እና የሚደንቀው ነገር የትላንቱ የአውሱዙ መኪና ረዳት የዛሬው ቢሊየነር መሆን በቅርበት ለሚያውቋቸው የኢሊባቡር ጎሬ ነዋሪዎች አስደንጋጭ ሁንዋል፡፡ ይህን ጉዳዩ የአካባቢውን ተወላጆች በመጠየቅ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ከአቶ አለም ጀርባ ያለው የህወሃት ባለስልጣን ማነው እንዲሁም ይህን ሁሉ ሀብት እንዲሸከሙስ ማን ሰጣቸው የሚለው ጊዜ የሚፈታው እንቆቁልሽ ነው፡፡
በጣም የሚያስገርመው ነገር ያኔ በረዳትነት ሲሰረባቸው የነበሩት አማቹ አቶ ብርሃነ ከነ ባለቤታቸው ወ.ሮ አበባ ከዚህ አለም ተለይተዋል፡፡ አሳኙ ነገር ከትግራይ ከገጠር አምተውተት በረዳትነት ሲሰራ ቆይቶ አሁን ድንገት ቢሊየነር የሆነው አቶ አለም ፍጹም የአቶ ብርሃነ ልጆችን እንኳን የማይረዳ መሆኑ ነው
በአሁኑ ሰአት ገበሬዎችን በማፈናቀል እየገደለ የሚገኘው ህወሃት ለነደዚህ ያሉ ግለሰቦችን መኪና ረዳትነት ከሚሊየነርም አሻግሮ ወደ ቢሊየነር ወርውሮ ሚሊየን ዜጎችን ችግረኛ ማድረግ ነው
አቶ አለም ፍጹም ማን ነበሩ የሚለው የዚህን መረጃ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የጎሬ ነዋሪዎችን መጠየቅ ይችላል ::
እነሆ ከላይ ያነበባችሁት በ2015 የተጻፈ ነበር። ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ውለው በዛሬው እለት ፍርድ ቤት ቀርበዋል ። የጀርመን ድምጽ ስለሰውየው የፍርድ ቤት ውሎ የጻፈው ዘገባ ነበር እኔን ጋደም ካልኩበት አስፈንጥሮ ይህን መረጃ አስታውሼ እንዳካፍላችሁ ያደረገኝ የጀርመን ድምጽ  የዛሬ ኖቬንበር 21/2018 ዘገባ እንዲህ ይላል
ፖሊስ በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የሚገኙትን አቶ ዓለም ፍጹምን የፕላስቲክ ፋብሪካቸውን እና ሆቴላቸውን በሕገ ወጥ መንገድ ያለጨረታ ለብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን በእንግሊዝኛ ምኅጻሩ ሜቴክ በመሸጥ እንደጠረጠራቸው ዛሬ ለፍርድ ቤት አስታወቀ። አቶ ዓለም ፋብሪካቸውን ለመሸጥ የሰጡት ዋጋ 128 ሚሊዮን ብር ሲሆን፤ ለሜቴክ የሸጡት ግን ከፍ ባለ ዋጋ በ195 ሚሊዮን ብር መኾኑን ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል። ይህን ያደረጉትም ጓደኛቸው ከሆኑት ከሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ጋር ተመሳጥረው ነው ሲል ገልጿል። የአቶ ዓለም ጠበቆች የፖሊስን ክስ ተቃውመዋል። ፍርድ ቤቱ አቶ ዓለም የዋስትና መብት እንዲሰጣቸው የቀረበለትን ጥያቄም ውድቅ ማድረጉን፤ ለምርመራ የተያዘላቸውን ጊዜም ከ14 ቀን ወደ 10 ቀናት ዝቅ ማለቱንም የፍርድ ቤቱን ሒደት የሚከታተለው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከሥፍራው የላከው ዘገባ ይገልጣል።
Filed in: Amharic