>
6:38 am - Wednesday December 7, 2022

ሰበር-ዜና፦ የጠፉት መርከቦች ተገኙ! ሜቴክ (ስዩም ተሾመ)

ሰበር-ዜና፦ የጠፉት መርከቦች ተገኙ! ሜቴክ
ስዩም ተሾመ
1) “አባይ” እና “ህዳሴ” እንደ “Padma” እና “Tika”
በመጀመሪያ እ.አ.አ. በ2016 ዓ.ም ከመላው ከአገልግሎት ውጪ በመሆናቸው ምክንያት ተቆራርጠው ለሌላ ነገር መስሪያ እንዲውሉ የተደረጉ መርከቦችን ዝርዝር (2016-List-of-all-ships-scrapped-all-over-the-world) አገኘን። በዚህ መረጃ መሰረት ተጠቀሰው አመት 862 መርከቦች አካላቸው ተቆራርጦ ለሌላ መርከብ ወይም ዕቃ መስሪያ ውሏል። ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ በተራ-ቁጥር 172 እና 173 ላይ ሁለት የኢትዮጵያ መርከቦች ተዘርዝረዋል። በዝርዝሩ መሰረት አባይ እና ህዳሴ የተባሉት መርከቦች “Padma” እና “Tika” የሚል ስም ተሰጥቷቸው በኮሞሮስ ሀገር ሰንደቅ ዓላማ ሲንቀሳቀሱ እንደነበር መረጃው ይጠቁማል።
በመጨረሻም እ.አ.አ. በ07-01-2016 ዓ.ም “Padma” የተባለችው መርከብ እንድትቆራረጥ በህንድ ሀገር ለሚገኝ “Alang” የተባለ ኩባንያ ተሸጣለች። “Tika” የተባለችው መርከብ ደግሞ በ02-02-2016 ዓ.ም በፓኪስታን ሀገር ለሚገኝ “Gadani” የተባለ ኩባኒያ መሸጧ ተጠቅሷል። ይሁን እንጂ በኮሞሮስ ሰንደቅ ዓላማ የሚንቀሳቀሱት እነዚህ ሁለት መርከቦች እስከተሸጡበት ዕለት ድረስ ባለቤታቸው፣ ለሥራ የሚያንቀሳቅሳቸው እና ተጠቃሚ ተብሎ የተጠቀሰው አካል ሜቴክ ሳይሆን “የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ አገልግሎት ኢንተርፕራይዝ” (Ethiopian Shipping and Logistics Service Enterprise) ነው።
በዚህ መሰረት ሜቴክ የሁለቱን መርከቦች ስምና ሰንደቅ ዓላማ ቀይሮ “የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ አገልግሎት ኢንተርፕራይዝ” ግን የመርከቦቹ ህጋዊ ባለቤት፣ ተጠቃሚና ተጠያቂ አድርጎ በሀገርና ድርጅቱ ስም በህገወጥ ንግድ ተሰማርቶ እንደነበር መገንዘብ ይቻላል። ስለሁለቱ መርከቦች የቀረበውን መረጃ ከታች ካለው ምስል መመልከት ይቻላል። በ2016 ዓ.ም በመላው ዓለም እንዲቆራረጡ የተሸጡት 862 መርከቦች ሙሉ ዝርዝር መረጃን ይህን ሊንክ(Excel) በመጫን ያንብቡ። https://ethiothinkthank.com/2018/11/24/ethiopian-ships-with-comoros-flag-and-ethiopian-ship-with-caribbean-flag/
Filed in: Amharic