>

የባንዳዎች ስርወ መንግስት በኢትዮጵያ!!! (ኤርሚያስ ቶኩማ)

የባንዳዎች ስርወ መንግስት በኢትዮጵያ!!!
ኤርሚያስ ቶኩማ
* አስደማሚው የሸንቁጥ ልጆች የአርበኝነት ጀብድ!
ይህ የሸንቁጥ ቤተሠብ የፈፀመው የአርበኝነት ጀብድ የጣልያንን ጭካኔ በአንፃሩ የኢትዮጵያዊያንን አልሸነፍ ባይነት የሚያሳይ ትልቅ ተውኔት የሚመስል ጀብድ ነው፡፡ ከሸንቁጥ ቤተሰብ የተገኙት አምባሳደር ዓለማየሁ አበበ ሸንቁጥ የወንድማማቾቹ የሸንቁጥ ልጆች የአርበኝነት ታሪክ በሚለው መፅሀፋቸው የወንድማማቾቹን ጀብድ አግኝቼ ሳነብ አፌን ይዤ ተገርሜያለሁ፡፡
አምስቱ ወንድማማቾች የሸንቁጥ ልጆች እነአበበ ሸንቁጥ፣ ተሸመ ሸንቁጥ፣ ሀይሌ ሸንቁጥ፣ ይነሱ ሸንቁጥና ጥላሁን ሸንቁጥ በጀማ ወንዝ፣ በጃማ፣ በሚዳ፣ በአደሬ፣ በወርቅ አምባ እና በእርግብየት የፋሺሽት ጦርን ውሃ ውሃ ያሰኙ የአንድ ቤተሰብ ጀግኖች ናቸው፡፡ የሸንቁጥ ልጆች የሆኑት ተሸመ፣ አበበና ሀይሌ ሸንቁጥ ኢትዮጵያ በጣልያን መወረሯን በመቃወም የፋሺሽትን ጦር እንዴት ከኢትዮጵያ ማስወገድ እንደሚቻል ምክር ለማግኘት ወደሰላሌ እና ጅሩ በመሄድ ከራስ አበበ አረጋይና ከደጃዝማች አበራ ካሳ ጋር ምክክር አድርገዋል፤ በነገራችን ላይ የደጃዝማች አበራ ካሳ ጀግናውን አርበኛ አቢቹን የያዘ ትልቅ ጦር ነው፡፡ የሸንቁጥ ልጆች ከእነራስ አበበ አረጋይ ጋር ከተወያዩ በኋላ ጦር አደራጅተው ጣልያንን ለመፋለም መርሃቤቴ በማቅናት ጣልያንን ማብረክረክ ጀመሩ፤ ከዚህም በኋላ የሸንቁጥ ልጆች ሃይላቸው እየተጠናከረ በሄደበት ወቅት ለሶስት በመከፈል በግራዝማች ተሸመ ሸንቁጥ፣ በልጅ ሐይሌ ሸንቁጥና በልጅ አበበ ሸንቁጥ የሚመራ ጦር በማደራጀት የጠላት ጦር ከካምፕ እንዳይወጣ በማድረግ ባለበት ከፍተኛ እርምጃ ወሰዱ በዚህም ከፍተኛ ንዴት ውስጥ የገቡት የጣልያን ወታደራዊ ሃለፊዎች በአውሮፕላን ጭምር ኬሚካል በመጠቀም የአካባቢውን ህዝብ ጨፈጨፉ የተረፈውም ለአካል ጉዳት ተዳረገ፡፡ በዚህም ከሸንቁጥ ልጆች መካከል ሶስቱ በግፍ እንዲገደሉ ምክንያት ሆኗል፡፡
ጣልያን የሸንቁጥ 3 ልጆችን በጦርነቱ ላይ ከገደለ በኋላ ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ቆዳቸውን በመግፈፍ አስነዋሪ ተግባር ፈፅመዋል፡፡ የወንድሞቻቸው ሞት ከጦር አውድማ ያላፈገፈጋቸው ጅግኖቹ የሸንቁጥ ልጆች ግራዝማች ተሾመ ሸንቁጥና አበበ ሸንቁጥ ቀን ከሌት ዘመናዊ መሳሪያ ከታጠቀው የጣልያን ጦር ጋር በመዋጋት ጀማ ወንዝ፣ በጃማ፣ በሚዳ፣ በአደሬ፣ በወርቅ አምባ፣ በእርግብየት እና ሌሎችንም አካባቢዎች ከጣልያን እጅ ነፃ ያወጡ የኢትዮጵያ ጀግኖች ናቸው፡፡ ይህ የሸንቁጥ ቤተሰብ በአጠቃላይ 6 የቤተሠቡ አባላትን ማለትም እናት፣ አባት፣ እህታቸውን ወይዘሮ ፋንታዬን፣ ሀይሌ ሸንቁጥ፣ ይነሱ ሸንቁጥና ጥላሁን ሸንቁጥን ለኢትዮጵያ ነፃነት ሲል ያጣ ታላቅ የኢትዮጵያ ባለውለተኛ ቤተሰብ ነው፡፡ የእነርሱን ብርታት ለሁላችንም ይስጠን፡፡ ስለሸንቁጥ ቤተሰብ በሰፊው ለማንበብ በአምባሳደር ዓለማየሁ አበበ ሸንቁጥ ተፅፎ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ የታተመውን የወንድማማቾቹ የሸንቁጥ ልጆች የአርበኝነት ታሪክ የሚለውን መፅሀፍ አንብቡት፡፡
የሸንቁጥ ልጆችን የሚያሳየው ምስል የተገኘው ከአመታት በፊት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ተቋም ሙዚየም ውስጥ በሄድኩበት ወቅት ነው፤ አሁንም ያለ ይመስለኛል ወደሙዚየሙ በመሄድ መጎብኘት ትችላላቹህ፡፡
ሌላኛው ባንዳ የአጤ ዮሐንስ ልጅ የሆነው የትግሬው ገዢ ራስ መንገሻ ነው
ራስ መንገሻ የአድዋ ጦርነት ሊካሄዱ ወራቶች ሲቀሩት ከጣልያኖች ጋር በመስማማት የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ጦር በተቃራኒ እንዲቆምና ለጣልያን እንዲያድር ጣልያንን የጠላ ጠላቴ በማለት የፋሺሽት ጣልያን ወታደሮች ከበሮ እየተደለቀላቸው ወደኢትዮጵያ ድንበር እንዲገቡ ምክንያት የነበረ ሰው ነው፡፡ ይህ ታሪኩ ግን ብዙም አይወራም የማይወራበት ምክንያት ሃሰቡን ቀይሮ የፈፀመው መልካም ተግባር ስላለ ሳይሆን ቢወራ እና እውነታው ቢታወቅ ህዝቦችን ከማራራቅ በተለየ ሊፈጠር የሚችል ነገር ስለማይኖር እውነታው እንዲደበቅ ተደርጓል፡፡
ሶስተኛው ባንዳ የተንቤን ተወላጁን ጀግናውን የእንግዳ እቁበን ልጅ የራስ አሉላን ህይወት የነጠቀው የተምቤን ገዢ የነበረው ራስ ሐጎስ ነው፡፡ ይህ ግለሰብ ከጣልያኖች ብዙ ድጋፍና እርዳታ ይደረግለት የነበረ እና ራስ አሉላን እንዲበቀል ከፋሽሽት ኢጣልያ ትዕዛዝ የተሠጠው ህሊናው በገንዘብና በጥቅም የታወረ ግለሠብ ነበረ፡፡ ራስ አሉላ ከአድዋ ድል በኋላ ሐገር ሰላም ብለው በተቀመጡበት ወቅት ይህ ባንዳ ራስ ሐጎስ የሚባል የጣልያን ተላላኪ ወታደሮችን አዘጋጅቶ የራስ አሉላ ጦር ባልተዘጋጀበት ሁኔታ ጦርነት በመክፈት የራስ አሉላን እግር በጥይት በመምታት ጀግናው የኢትዮጵያ ባለውለታ ራስ አሉላ አባነጋ እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር የካቲት 15 1897 ህይወታቸው እንዲያልፉ ያደረገ ታሪክ ሊረሳው የማይገባው የጣልያን ተላላኪ ነበረ፡፡
አራተኛው ባንዳ ብዙዎቻችን የምናውቀው ኃይለስላሴ ጉግሳ ነው፡፡ ኃይለስላሴ ጉግሳ የአጤ ዮሐንስ የልጅ ልጅ ነው፡፡ ይህ ባንዳ ከራስ ስዩም ጋር በመሆን ትግራይን ለሁለት ከፍሎ ሲመራ የነበረ ግለሠብ ሲሆን በወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉስ የነበሩት አጤ ኃይለስላሴ ልጃቸውን ዘነበወርቅን ገና በ13 ዓመት እድሜዋ የዳሩለት ግለሰብ ነው፡፡ ይህ እንሰሳ የ13 ዓመት ልጅ የነበረችውን ዘነበወርቅ በማስረገዝ በወሊድ ምክንያት ህይወቷ እንዲያልፍ ያደረገ ነውረኛ ግለሠብ ነው፡፡ ባንዳው ኃይለስላሴ ጉግሳ እንደቀደምቶቹ ኢትዮጵያን ለመካድ ከነበረው ፍላጎት የተነሳ አጤ ኃይለስላሴን የምገዛው መሬት ስላነሰኝ ግዛት ይጨመርልኝ በማለት ቁርሾውን ከጀመረ በኋላ የ2ኛው የጣልያን ወረራ ሊነሳ አቅራቢያ መስከረም 28 ቀን ከአዲስ አበባ ጋር የሚገናኘውን የስልክ መስመር በሙሉ በጣጥሶ በወታደሮቹ ታጅቦ አስመራ በመግባት ለጣልያን ለማደር የተስማማ ነው፡፡ እዚህ ጋር እጅግ ልብ የሚነካው ተግባር የእርሱ ወታደሮች የፈፀሙት ተግባር ነው፡፡ ኃይለስላሴ ጉግሳ 12000 ወታደሮች የነበሩት ሲሆን ባንዳ ለመሆን መስማማቱን ሲያውቁ አስመራ ድረስ አብረውት ለመሄድ የተስማሙት አንድ ሺህ ብቻ መሆናቸውን ደቦና በመፅሃፉ ገልጧል፡፡ ኃይለስላሴ ጉግሳ ከባንዳነቱ በተጨማሪ አንዳንድ የትግራይ ሹማምንት ለኢጣልያ እንዲያድሩ በማድረግ ጣልያኖች በነፃነት የትግራይ ምድር ላይ እንዲጨፍሩና የትግራይ ህዝብ ላይ እንደፈለጋቸው እንዲፈነጩ ያደረገ ባንዳ ነበረ፡፡
እኔ ግን እናገራለሁ ደንቆሮን ደንቆሮ ካላልከው ደንቆሮነቱን ሊረዳ አይችልም ይላሉ አባቶቻችን እውነት ነው ደንቆሮን ደንቆሮ ልንለው ይገባል ችግሩ የዘንድሮዎቹ ደንቆሮዎች ህወሃትና አረና ደንቆሮ ብንላቸውም ሊሠሙን አልቻሉም ምክንያቱም ደንቆሮ መስማት አይችልምና ሆኖም እውነታውን አሁንም ቢጠቅምም ባይጠቅምም ከዚህ በኋላም መፃፋችንን እንቀጥላለን፡፡
Filed in: Amharic