ብርሀን መስቀል አበበ
በዚህ ሳምንት ብቅ ያለችው በጠቅላይ ሚንስትር አብይ የሚመራው ኢህዴግ የሚቀጥለውን ምርጫ አያሸንፍም የምትለው የተቀዋሚዎች ትርክት እንድምታ ለኢትዮጵያ ህዝብ በደንብ ሊትገባ ይገባል።
አሁን በኢትዮጵያ ያለው የተደረጀ የፖላቲካ ኃይል አሰላለፍ ሁለት ብቻ ነው። አንደኛው የተደራጀ የፖላቲካ ኃይል በጠቅላይ ሚንስትር አብይ የሚመራው የለውጥ ኃይሎች ኢህዴግ ነው። ሁለተኛው የተደራጀ የፖላቲካ ኃይል በህወሃት የተደራጁ ሌቦች የሚመራው እና በነዶ/ር አብይ ከስልጣን የተባረረው እና አድፍጦ ለውጡን ለመቀልበስ ቀን እና ምቹ አጋጣሚ የሚጠብቀው በህወሃት ሌቦች የሚመራው የሌቦች ኢህዴግ ነው።
አሁን በኢትዮጵያ ባለው የፖላቲካ ኃይል አሰላለፍ ተቃዋሚ ቡድኖች እና እዚህና እዚያ ውርውር የሚሉ ግለሰቦች የነዚህ ሁለት የኢህዴግ ቡድኖች አጫፋሪ እንጂ እነርሱ በራሳቸው ከግለሰብ ስብስብነት ያለፉ የፖላቲካ ኃይል አይደሉም።
ታዲያ እነዚህ የአጫፈሪነት ሚና ያላቸው የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ቡድኖች እና ውርውር የሚሉ ግለሰቦች ሁለት ታሪካዊ ምርጫ አላቸው። አንደኛው ምርጫ የጠቅላይ ሚንስትር አብይን የለውጥ መንግስት መደገፍ እና ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ቆሞ የተጀመረውን ለውጥ ማስቀጠል ነው።
ሁለተኛው የተቃዋሚ ቡድኖች ምርጫ መቀሌ ከመሸገው የህወሃት የተደራጁት ሌቦች ጎን መሰለፍ እና ለውጡን በምርጫ ግርግር ሰም ለመቀልበስ መስራት እና በመላው ኢትዮጵያ ግንባር ፈጥረው አድፍጠው የእነ አብይን መሰናከል የሚጠብቁ የተደራጁ የህወሃት ተባባሪ ሌቦች አገር እንዲያፈርሱ ማድረግ ነው።
ከትርክታቸው እንደምናየው የአጫፋሪ ተቃዋሚዎቻችን ምርጫ “የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው” በሚል መሪሆዎቸው በጠቅላይ ሚንስትር አብይ የሚመራውን የተራማጅ ኢህዲጎች መንግስት በመቃወም እና እነርሱን ለማዳከም በህወሃት ሌቦች የሚመራውን ኢህዴግ ወደ መደገፍ የተሸጋገሩ ይመስላል።
በጠቅላይ ሚንስትር አብይ የሚመራውን የተራማጅ ኢህዴግ ቡድን ለ27 አመት በህወሃት ሲመራ ከነበረው የተደራጁ ሌቦች ኢህዴግ ጋር አንድ አድርጎ እና አመሳስሎ ለህዝብ መግለፅ እና በጠቅላይ ሚንስትር አብይ የሚመራው ኢህዴግ የሚቀጥለውን ምርጫ አያሸንፍም ማለት በህወሃት ሌቦች የሚመራው ኢህዴግ ወደ ስልጣን ተመልሶ አገር እንዲያፈርስ እንረዳለን ከማለት ውጭ ሌላ ምንም ትርጉም የለውም።
ይህ የአሁኑ የተቀዋሚ ቡድኖች አሰላለፍ በኢትዮ ሱማሌ ጦርነት ጊዜ የደርግን መንግስት ለመጣል ብቻ ብለው “የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው” በሚለው መርዘኛ ፖሊሲያቸው ኢትዮጵያን ሊያፈርስ ከመጣው ከወራሪው የሱማሌ መንግስት ጋር ከተሰለፉት ከህወሃት እና ኢህፖ የአገር ክህደት ወንጀል በፍፁም የከፋ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለ ከፍተኛ ክህደት ነው። ልብ ያለው ልብ ይበል!