>

ጌታቸው አሰፋን ለማደን አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ተባበረች - አፍሪካን ዴይሊ ቮይስ

ጌታቸው አሰፋን ለማደን አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ተባበረች”
አፍሪካን ዴይሊ ቮይስ የተሰኘ ዜና አውታር።
ኖቬምበር 30/ 2018 ፤
ትርጉም ሉሉ ከበደ
ጌታቸው አሰፋ ፤ የቀድሞው ወታደራዊ ስለላ ሀላፊ ትግራይ ገጠር ውስጥ ተሸሽጎ ያለ፤  “ይፈለጋል” በሚል አዋጅ በአሜሪካ  የአስር ዋራንት ወቷል ። የኤርትራው መራሄ ዜና አገልግሎት ተስፋ ዜና  አንደሚለው ስዩሙ የኢትዮጵያ መንግስት ተስፋዬን ለበርካታ ክሶች በማደኑ ተግባር ላይ በመሰማራቱ የአሜሪካ መንግስት  የበኩሉን እገዛ ያደርጋል።
አዲስ አበባ ላይ ዶክተር አብይ አህመድን ለመግደል ለተቀነባበረው ሴራ ፤ በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ ስውር እስር ቤቶች ታስረው በነበሩ መቶሺዎች  ላይ ለተፈጸሙ ኢሰብአዊ ግፎች ፤ ግብረሶዶም መፈጸም፤ ሴቶችን አስገድዶ በጅምላ መድፈር ፤ በግርፋት ቁምስቅል ማሳየት ፤ስቃይ የሞላባቸው  ግድያዎች ፤ ልዩልዩ ዘዴዎችን በመጠቀም በኢትዮጵያውያን ላይ ለፈጸመው ሰቆቃ  እንዲሁም ደግሞ ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ከሜቴክ በመስረቅ ወንጀል ይፈለጋል።እንደ ADV ዜና ዘገባ።
በቅርቡ የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል አቃቢ ህግ መስሪያ ቤት በጌታቸው አሰፋ ሀላፊነትና ቁጥጥር ስር የነበሩ  ዜጎችን ቁምስቅል የሚያሳዩ ፤  ፤ በርካታ ማሰቃያ ስውር እስርቤቶች በኢትዮጵያ መገኘታቸውን አስታውቆ ነበር።  ከነዚህም ሰባቱ አዲስ አበባ ውስጥ እንዳሉ ጠቁሟል።
እናም አሜሪካ ጌታቸው አሰፋን በማደኑ ተግባር ከወሰደቻቸው እርምጃዎች በሱላይ የጉዞ ማእቀብ መጣልና የባንክ ሂሳቡን ማገድን ይጨምራል።
አሜሪካ ይህን እርምጃ እውን ያደረገችው በኢትዮጵያ የወያኔ ባለስልጣናት ለፈጸሙት ኢሰበዊ ወንጀል ተጠያቂ የሚያደርገው  HR 128 የተሰኘው ሰነድ በዩኤስ ኮንግረስ ማለፉን ተከትሎ መሆኑን የዜናው ምንጭ አክሎ ገልጿል።
Filed in: Amharic