>
5:01 pm - Sunday December 2, 2953

በዐማራው ላይ ግድያው ማፈናቀሉ ወደ ኩላሊት ዝርፊያ አድጓል ይሉልሃል የመከራው ገፈት ቀማሾቹ!!!  (ዘመድኩን በቀለ)

በዐማራው ላይ ግድያው ማፈናቀሉ ወደ ኩላሊት ዝርፊያ አድጓል ይሉልሃል የመከራው ገፈት ቀማሾቹ!!!
ዘመድኩን በቀለ 
በመርፌ፣ በኪኒን፣ በጦር፣ በቀስት፣ በእስር፣ በስደት፣ በማፈናቀል፣ በህክምና እጦት፣ በግብር፣ በታክስ ከላይ ከታች አካልበውት፣ ረሽነውት፣ አቃጥለው ፈጅተውት አላልቅ፣ አልጠፋ ያለ ጉደኛ ብሔር ቢኖር ዐማራው ብቻ ነው!!!
~ አፄ ዮሐንስ ወሎና ጎጃምን፣ መለስ ዜናዊ መላውን ዐማራ ባለ በሌለ ኃይላቸው ቢፈጁትም ንጉሡም ጠቅላይ ሚንስትሩም አፈር ሆነዋል። ዐማራው ግን ይኸው ዓለም እያየ እየተመለከተም እንኳ የማይረዳውን መከራ ተሸክሞ ህይወቱን ይገፋል።
 የዛሬዋ ኢትዮጵያ ማለት ዐማራን እየበላች የማትወፍር፣ በልታ ግጣውም የማትጠግብና ቅምም የማይላት በሹካም፣ በማንኪያም፣ በቀስትም በጥይትም፣ በገጀራም በካራም ብትለው ብትለው የማትጨርሰውም አላልቅ ብሎም ያሰቸገራት ሀገር ማለት ናት።
የዚህ መከረኛ ህዝብ ወኪል ነኝ ባዩ ደግሞ የቀድሞው በድኑ ብአዴን፣ የአሁኑ አሽቋላጩ አዴፓ የተባለ ታጥቦ አይጠሬ ፓርቲ ነው።
አዴፓ/ብአዴን ፦ 
በአሁኑ ወቅት በሀገረ አሜሪካ በሽርሽር ላይ ነው። አዴፓ ለምን በዚህ ቀውጢ ሰዓት ወደ አሜሪካ እንደሄደ የሚያውቀው ቸሩ መድኃኔዓለምና ራሱ አዴፓ ብቻ ናቸው። የአዴፓን የአሁኑን የአማሪካ ጉዞ ሰይጣን ራሱ የሚያውቀው አይመስለኝም። ሀገር እሳት እየነደደበት እሱ እንደ ደላው ሁሉ እንደሞላለት ሰው አስረሽ ምቺው ይጨፍራል። ሰው ሲሞት ቴሌቭዥን ራዲዮ ከሚዘጋ ማኅበረሰብ የወጣም አይመስልም። ነገዱ እየታረደ የሚጨፍር ፓርቲ አዴፓ ብቻ ነው።
አዴፓ
በዚህ በአሁኑ የአማሪካ ጉዞው ባልተሰጠው ውክልና ገብቶ ሊፈተፍት ሲጥርም ታይቷል። የዐማራ ህዝብ ወኪል የሆንኩ ዐማራዊ ፓርቲ ነኝ ባዩ አጅሬ አዴፓ አሜሪካ ሲደርስ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ጥብቅና ለመቆምና ወኪል ለመሆን የሚዳክር ሳይጠራ አቤት ባይ አቅሙን አያውቅ ፓርቲም ሆኖ ታይቷል። ቢያንስ በአሁን ሰዓት የትግሬዎቹ ህወሓት አዴፓን እንኳን ሊያነጋግረው ይቅርና በላይ በታች እሳት ለኩሶበት ዶግዐመድ ሊያደርገው ባለ በሌለ ኃይሉ ይደክማል። ህውሓት የአዴፓን ዐይኑን ማየት እንኳ አይፈልግም። ቢጠቅምም ባይጠቅምም ሁሉም ነገዱን ለማዳን እንቅልፍ ሲያጣእና ሲደክም አዴፓ ባልተጠራበት፣ ባልተወከለበትም የምን ጭራ መቁላት ነው። መጀመሪያ ራስህን ሁን በሉት። ከዚያ ለኢትዮጵያዊነቱ ትደርስበታለህ። ኢትዮጵያዊነትህን የሚቀማህ የለም። መጀመሪያ በሀገሪቱ ህግ መሠረት ለወከልከህ ነገድህ ጥብቅና ቁም በሉት።
አዴፓ
በአሜሪካ የማይመልሰውን ጥያቄ ሲጠየቅ ይታያል። በሀገር ቤት በህዝቡ የተጠየቀውን ጥያቄ ሳይመልስ አሜሪካ ድረስ ሄዶ ጥያቄ ለመቀበል ተኮፍሶ መቀመጡ በራሱ አስቂኝ ነው። ኢህአዲግ መናገር እንጂ መስማት የማይችል ጆሮው የደንቆሮ መሆኑን የማይረዳው ህዝብ ደግሞ ዝንተ ዓለሙን ሰው አገኘሁ ብሎ ኢህአዴጋውያንን ባገኘ ቁጥር እጁን እየቀሰረ የማይመለስ ጥያቄ ሲጠይቅ ውሎ ያድራል። በዚህ የአዴፓ ሽርሽር ውስጥ የማከብረውን ዶር አምባቸውን ማየቴም ይቆጨኛል። የዶክተሩ ቦታ ከምር አዴፓ አልነበረም።
አዴፓ
በአሜሪካ ለኦሮሞ ያለውን ፍቅር ለማሳየት ሲል ሱሪውን ጥሎ ላብ በላብ እስኪሆን ድረስ በጭፈራ ልቡ እስኪጠፋ ሲውነጠነጥ ታይቷል። ይሄ ለባለ ጊዜ ማሽቋለጥ ደግሞ ለአዴፓ አዲሱ አይደለም። የቆየና አብሮት ያደገም፣ ለገዢ ማሽቋለጥና ማሽካካት መገለጫ ባህሪው የሆነ ፓርቲ ነው። አዴፓ ቀደም ሲል ጠፍጥፎ ለፈጠረው ህወሓት ዕድሜ ዘመኑን እንዲሁ አሁን ለአዴፓ እንደሚሆነው ሲያሽቋልጥ የኖረ ፓርቲ ነው። በዘመነ ህወሓት፤ አጅሪት ስሙን እንኳ ሳይቀር ከኢህዴን ወደ በድኑ ብአዴን የቀየረችለት፣ የባንዲራውን ከለሩን ሳይቀር አሰፍታ በመስጠት ማንነቱን ሰልባ አሽከር አድርጋው የኖረች ናት።
ህወሓት የድፍረቷ ድፍረት፣ የንቀቷም ንቀት ዐማራን እንዲመሩ ከኤርትራና ከትግራይ ድረስ አማርኛ ተናጋሪ ትግሬዎችን በዚሁ በድን ድርጅት ውስጥ ሰግስጋ ባለሥልጣናትም አድርጋ የሾመችለት በድን ድርጅት ነው። እኒህ ዐማራውን እንዲመሩ የሾመቻቸው ዐማርኛ ተናጋሪ ትግሬዎች ዐማራውን ” ለሃጫም፣ ትምክህተኛ፣ ልጋጋም” እያሉ እየሰደቡት እንዲገዙት ሁላ ነው ያደረገችው። እነዚህ ተሳዳቢዎች አሁንም ስልጣን ላይ ተቀምጠዋል። የሰደቡትን ዐማራ ምን ታመጣለህ ብለውም ያላግጡበታል።
 ዛሬ ህውሓት ስትሞት ደግሞ ህውሓት ከእሱ በኋላ በሰሜን ሸዋ ደራ ላይ ከደርግ ምርኮኞች ሰብስባ የፈጠረችው ጩጬው ኦህዴድ ሥልጣን ሲይዝ አዴፓ አሁንም የኦዴፓ አሽከር ሆኖ ማሽቋለጥ የባህሪ መገለጫው ነውና ለኦህዴድ እያጎነበሰ ጫማም እየላሰ ይብረከረካል። ጎበዝ [ ፍቅርና አሽከርነት ፈጽሞ ይለያያሉ ]።
አዴፓን
ይኸው ኦህዴድ እንኳ በአቅሙ ስሙን አስቀየረው። ያውም እኔ ኦዴፓ ሆኛለሁና አንተም አዴፓ በል ብሎ ስሙንም፣ ጾታውንም አስለወጠው። ኦዴፓ የአዴፓን አርማውንም አስለውጦታል። ኤርትራዊው በረከት ስምኦን ከሥልጣን ቢለቅም የአዴፓዎቹ የአርሲ ልጆች የባህርዳሩን የአዴፓ ቢሮ ተቆጣጥረው አዴፓን ኦሮምኛ ያስጨፍሩታል።
አዴፓ
በህወሓት አብዮታዊ ዲሞክራሲ ተጠምቀው ያረጁና የጃጁ የሽማግሌዎች ጥርቅም የሞላበት ፓርቲ ስለሆነ የዐማራ ህዝብ ከላይ በትግራይ የህውሓት ጦር፣ ከታች በትግራዩ ህወሓት በሪሞት ኮንትሮል በሚታዘዘው የቤኒሻንጉል ቀስተኛ የዘላን ጦር እንደቅጠል ይረግፋል። ገበሬው ዐማራ እርሻውን ትቶ የህውሓት ቅጥረኞችና የሱዳን ወራሪዎችን አፈር ከድሜ ሲያበላ ገለልተኛ ተብዬው የመከላከያ ሠራዊቱ ደግሞ ለአጥቂው የህውሓት ጦር ተደርቦ የዐማራውን ገበሬ ለመውጋት ሲላላጥ ይታያል።
አዴፓ
እነ ጃዋር በአንድ እጃቸው #ኦሮማራ የሚል የማደንዘዣ መርፌ ወግተው በሌላኛው እጃቸው ደግሞ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ከፍተው፣ መጽሔትም አሳትመው፣ ወዳጄ የሚሉትን ዐማራውን ቅማንት አገው እያሉ የሌለ አጀንዳ ፈጥረው ሊያፈራርሱት ሲጥሩ እያየ ለምን እንኳን ብሎ አይጠይቅም። ኦሮሞዎቹ የራሳቸውን የወለጋ፣ የአሩሲ፣ የሐረርጌ፣ የባሌ፣ የሸዋና የጂማ ኦሮሞ ማስማማት አቅቷቸው፣ ጴንጤ ኦሮሞና፣ እስላም ኦሮሞ ከኦርቶዶክሱ ኦሮሞ ጋር ተፋጦ መጨረሻውን እየተጠባበቀ እያዩ፣ የራሳቸውን ያረረ ድስት እንደማማሰል፣ ከትግሬው ህውሓት ጀሌዎች ጋር አንድ ላይ #አብረው፣ ዕድሜ ዘመናቸውን ዐይተውት የማያውቁትን ኢትዮጵያን የመምራት ሥልጣን ቁልፉን ያስጨበጣቸውንና ለዙፋኑ ያበቃቸውን ዐማራውን ለማፈራረስ እንቅልፍ አጥተው ያድራሉ። አዴፓ ይሄንንም አይቃወምም። ለምን ብሎም አይጠይቅም። የአፀፋ ምላሽም አይሰጥም። አዴፓ ሲፈጥረው አቃጣሪ፣ አሸርጓጅ አድርጎ ፈጥሮታልና ምን ይደረግ። መቼም በግድ ከዝንብ ማር አይጠበቅ።
አዴፓ
ለነገዱ፣ ለብሔሩ ፍቅር የለውም። ሲፈልግ የአባቶቹን ርስት ከነ ህዝቡ ቆርሶ ይሸጣል። ጎጃምን በቁሙ ቆርሶ ከነ ህዝቡ የሸጠ፣ ጎንደርን ወሎንና ሸዋን በነፃ ከነ ህዝቡ አሳልፎ የሸጠ የህዝብ ነጋዴ የሆነ ፓርቲ ነው። ፓርቲው ከጥቂቶች በቀር “በሆዳም ዐማራዎች” የተሞላ ፓርቲ ነው። ገንዘብ ካገኙ፣ ካድሬ ከሆኑ ወላጅ እናታቸውን እንኳ አሳልፈው ቢሸጡ ቅሽሽ በማይላቸው አእምሮ በተነሱ ድንዙዛን የተሞላ ነው።  ለምሳሌ እስራኤል አንድ እስራኤላዊ ዜጋዋ ከሀማስ በተተኮሰ ጥይት ቢሞትባት መሪዋ የውጭ ጉዞ አቋርጦ ወደ ሀገሩ ይመለሳል። ወታደሩ ስለ አንዱ ፈንታ የሚወስደው እርምጃ በሁሉ ዘንድ ይታወቃል። አዴፓ ግን በከባድ መሣሪያ የታገዘ የጅምላ ጭፍጨፋ በሚመራው የዐማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ እያየ፣ እየሰማም እሱ ግን ደንታ የለውም። ጭራሽ ጎንደር እየነደደች እሱ ባህር ተሻግሮ አሜሪካ ለአሜሪካ በዚህ በበረዶ ያውም እልም ባለ ድቅድቅ ክረምት በቆፈናም ወራት ሀኒ ሙኑ አይሉት ምን መላቅጡ የጠፋ ዙረት ይዞራል። እንዲያው ግን እነ አቢቹ ምን ቢያስቡ ነው በዚህ ሰዓት አዴፓን ወደ አሜሪካ ንካው ያሉት። መልሱን የሚያውቁት እነሱ ቢሆኑም ቢያንስ ለማስመሰል ያህል እንኳ አጅሬ አዴፓ የአሜሪካ ጉዞውን አቋርጦ ባይመለስም በለበት ሆኖ በርገሩን እየበላ እንዴት በአሁን ሰዓት በዐማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግልፅ ጦርነት ካለበት በመቃወም ስለ ሁኔታው ጥቂት እንኳ ትንፍሽ አይልም?
አዴፓ
አዲሱ አሳዳሪውና አዲሱ ጌታው አጅሬ ኦህዴድ/ኦዴፓ ከቤኒሻንጉል ተነሱ የተባሉ ታጣቂዎች አምስት የኦሮሞ ነገድ አባላት ገደሉ ተብሎ በተቀናጀ ሁኔታ በመላዋ የኦሮምያ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጡ አስደርጎ ህዝቡ መንግሥት ኦሮሞ ሲገደል እያየ ለምን ዝም ይላል? በአስቸኳይ እርምጃ ይውሰድ እንዲሉም አስደርጎ፤ በነገደ ኦሮሞ የተጥለቀለቀው የኢትዮጵያ መንግሥትም የኦሮሞ ሰልፈኞቹን ጥያቄ ተቀብሎ የሀገሪቱን መከላከያ ሠራዊት ወደ ቤኒሻንጉል ክልል ልኮ ተደፈረ የተባለውን የኦሮሞን መብት ለማስከበረ የሄደበትን ርቀት በዐይናችን እያየን፣ በጆሮአችንም እየሰማን ያለንበት ሁኔታ ነው ያለው። እንዲያውም ከዚያም አልፎ የአብቹ መንግሥት የቤኒሻንጉል ባለሥልጣናትን ሰብስቦ ከርቸሌም ዶሏቸዋል። ለነገዱ መቆርቆር ማለት ይሄ ነው።
አዴፓ
በድኑ ግን በሺ የሚቆጠሩ ዐማሮች ከቤኒሻንጉል እየታረዱ ኩላሊታቸው ሲበላ፣ የማንም ዘላን ቀስት መለማመጃ ሲሆኑ፤ የተገደሉትን፣ የታረዱትን ዐማሮች አስከሬን አትቀብሩም ተብለው የዐማሮችን ሬሳ የጫካ አውሬ እንኳ ለመብላት ሲጠየፈው፣ ዐማራው ከቀዬው እየተፈናቀለ በህርዳርን ሲያጨናንቃት እያየ፣ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ራያ በዐማራነቱ ምክንያት ብቻ ፍዳውን ሲያይ እሱ እቴ እንኳን ለምን ብሎ ሊጠይቅ ማላገጫ የሆነውን የተለመደውን አንጀት አቁስል መግለጫ እንኳ ሲያወጣ አይታይም።
እሱ ብቻ እሺ እዚያጋ አንተኛው ባለ ዜብራ ሸሚዝ ያደረከው ተራ ቁጥር 5 ነህ፣ እርሶ እዚያ ጋ የሉት ባለ ባርኔጣው ደግሞ ተራ ቁጥር 9 ነዎት፣ እርሶ ባለ ሹሩባዋ፣ አይደለም እርሶ ቀይዋ ሴትዮ እ አዎ እርስዎ ደግሞ ቁጥር አንድ ነዎት። በሉ ጠይቁ እያለ መሬት ላይ የማያርፍና አየር ላይ ተበትኖ የሚቀር ምላሽ የሌለው ጥያቄ ሲጠየቅ ይውል ያድርልኛል። አስተዳድራታለሁ የሚለው ህዝብ እሳት ተለኩሶበት እየነደደ ለዘር የቀረውን ዐማራ ናና ሀገር ቤት ገብተህ አልማ ይለዋል። ሀገር ቤት ያለው ዐማራ በቁሙ እየተዘረፈ ያልደረሰለት ብአዴን ከባህር ማዶ ያሉትን ለአዲስ ዘረፋ ይውሰውሳቸዋል።
አዴፓ
ማለት ልክ እንደ ሽንፍላ ያለ ታጥቦ የማይጠራ ባለ ብዙ ክፍል ቤት ቆሻሻ የሞላበት ፓርቲ ማለት ነው። በቃ ያው በድኑ ብአዴን አሁንም ጃኬት ቀይሮ እንደማለት ማለት ነው። ተለወጠ የተባለው ስሙ ብቻ ነው። ለወገኑ፣ ለባህሉ፣ ለቅርሱ፣ ደንታ የሌለው አቁስል ፓርቲ። ዘላለሙን የአሸናፊዎችን ጫማ ሲልስ የሚኖር፣ እንደ ወንድ የማይገዳደር፣ የማይደራደር፣ አሽቃባጭ፣ ደንታቢስና ያለ ወበቶ ሱሪ የሚታጠቅ ፓርቲ ነው። እኔ በህይወቴ እንዲህ እንደ አዴፓ ዓይነት እያቃጠለ፣ እየለበለበ፣ ጨጓራም እየላጠ ህዝቡን የሚገዛ #ሚጥሚጣ የሆነ ፓርቲ ዓይቼም፣ ሰምቼም አላውቅ።
እኔ ግን እላለሁ። በመጨረሻ የሆነው ሁሉ ሆኖ ነገር ሁሉ ሲያበቃ ተወደደም ተጠላም ኢትዮጵያና ዐማራ ግን አይጠፉም። ዐማራን እናጠፋዋለን፣ ኢትዮጵያንም እናፈርሳታለን ባዮች ግን ከኢትዮጵያም፣ ከዐማራም በፊት ዓይናቸው እያየ ራሳቸው ድራሽ አባታቸው ከምድረገጽ ይጠፋል። ይሄ የማይቀር ሃቅ ነው። ንግርቱም እንዲሁ ነው የሚለው። ይሄው ነው። አከተመ ።
ይሄን ዘግናኝ የካህን ምስክርነት እየሰማም “ሆዳም ዐማራው” ግን አሁንም የዐማራው ቁስል ሲሰማው አይታይም። ያልበላውን ያካል። የሰው ድግሥ ያሟሙቃል። የማያገባውን፣ የማይመለከተውንም አጀንዳ ተሸክሞ ይዞራል። እባክህ አትጃጃል ወደ ቀልብህ ተመለስ። ለወገንህም ድረስለት። 
 https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=741293026235592&id=176519726046261
Filed in: Amharic