>
6:41 am - Tuesday July 5, 2022

ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ፀፀት ተክለን እንዳናልፍ!!! (ቹቹ አለባቸው)

ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ፀፀት ተክለን እንዳናልፍ!!!
ቹቹ አለባቸው
ሰሞኑን በጭልጋ አካባቢ የተከሰተውና አሁንም በደንቢያ አካባቢ እንደቀተለ የምሰማው ነገር እጅግ ያሳዝናል፤ያማል፡፡ ይሄ ሁኔታ እንዳይደርስ ካሁን በፊት ከማውቀውና ከልምዴ ተነስቸ ያልኩትን ብየ ነበር፤ነገር ግን አንዳንድ ገወኖች ሃሳቤን ሰምተው መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ፤በኔ ሃሳብ ሲያኮርፉ ታዘብኳቸው፤እኔም ካጠፋሁ እሽ ብየ ዝም አልኩ፤እኔ ግን እውነቴን ነው፤ የሁለቱን ህዝቦች እውነተኛ ስሜት አውቀዋለሁ፡፡ ሁለቱ ህዝቦች ተማምነውና ተግባብተው፤አንዱን አንዱ ችሎ ለመኖር ካልሞከሩ በቀር፤ገናም  ከዚህም በላይ ከባድና አስፈሪ ሁኔታ ሊገጥመን ይችላል፡፡ ምክንያቱም ነገሮች ከመቸውም ጊዜ በላይ ተበላሽተዋልና፡፡
———-////——
በአንድ ነገር ግን እንስማማ፤ አማራ ራሱን ከማናቸውም ጥቃት የመከላከል፤ህጋዊና ተፈጥሯዊ መብት አለው፡፡ የቅማንት ህዝብም እንዲሁ፡፡ ይሄንን መብትህን ለማስጠበቅ ደግሞ ቅድምያ፤ መብትህን የነካብህን/ አጥቂህን ለይተህ ማወቅ ቀዳሚው ስራ ነው፡፡ አሁን እየተካሄደ ያለው ግጭት፤በምንም ታአምር የቅማንትን ህዝብ በተለይም አ/አደሩን እንደማይወክል አምናለሁ፡፡ ከሱ የተገኙ ጥቂት ህገ-ወጦች በፈጠሩት ችግር በቅማንት ህዝብ ላይ እንደ አጠቃላይ እጣታችንን ልንቀስር አይገባም፡፡ ነገር ግን ይሄንን ድርጊት በመሩትና ባስተባበሩት፤እንዲሁም በድርጊቱ በቀጥታ ተሳታፊ በሆኑ እኩይ አካላት ላይ የአማራ ህዝብና መንግስት ከመችውም ጊዜ በላይ አስተማሪና ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ በርትተው መስራት አለባቸው፡፡ለዚህ ደግሞ የቅማንት ወንድሞቻችንም መተባበር አለባቸው፤አንድ ሰው አማራ ስለሆነ ወይም ቅማንት ስለሆነ ብቻ ወንጀል እየሰራ ልንሸፍነው አይገባም፤ እኛ አማራዎችና ቅማንቶች ህወሀታዊያን አይደለንም፤ እንደሂህ አይነት ግለሰቦች ለሁለቱም ህዝቦች አይጠቅሙምና፡፡
——///——-
በአርማጭሆ፤መተማና ደንቢያ፤በለሳ አካባቢ አንዳንድ ነገሮችን እሰማሁ ስለሆነ ማስተዋል አለብን፡፡ የተጋጩት ሁለት ወንድማማቾች ናቸው፤ያጋጫቸውንም እናውቀዋለን፡፡ ይልቁንስ አሁን ላይ ማትኮር ያለብን ድርጊቱን የመሩትና ያስፈጸሙትን ከገቡበት ገብቶ ለህግ ማቅረብ ነው፡ ጎንደር፤ደንቢያ ፤በለሳ፤ ታች አርማጭሆና መተማ ከቅማነት ወንድሞቻችሁ ጋር በመተባበር እነዚህን አጥፊዎች ለህግ ማቅረብ አለባችሁ፤ሌላ እላፊ አያስፈልግም፡፡
——–////———–
ለአማራ ወንድም/አህቶቸ- ይገባኛል፤የገጠመን ችግር እጅግ አስቸጋሪ ነው፡፡ ሰው ከወንድሙ አንጻር እንዲህ ፈተና ሲገጥመው እጅግ ከባድ ነው፡፡ ግን ምርቱን ከጥሬው መለየት ያስፈልጋል፤ ህዝብ በጅምላ እንዳይጠቃ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፤አጥፊውን ግን ከመቸውም ጊዜ በላይ መረር ብላችሁ ለህግ አቅርቡ፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ” ባንተ ላይ እንዲደረግ የማትፈልገውን ነገር በሌሎች ላይ እንዲሆን አትፈልግ/ አታድርግ” የሚለውን አባበል እንዳትዘነጉ፡፡ ስለሆነም፤ይህን ክፉ ቀን የሚከፈለውን ዋጋ ሁሉ ከፍለንም ቢሆን ማለፋችን አይርቀርም፡፡ ምን ለማለት ፈልጌ ነው፤ነገ ጸጸት የምንገባበት ስራ እንዳይሰራ ለማለት ነው፡፡ ጥቃት ያደረሱብንን ሰዎች ግን ከመቸውም ጊዜ በላይ ምርር ብለን እንታገላቸው፤ይሄንን በማድረጋችን ደግሞ በነገሩ የሌለበት አብዛኛው የቅማነት ማህበረሰብ የሚደግፈን ይመስለኛል፡፡ ብቻ በኛ በኩልም አላስፈላጊ ድርጊቶች እንዳይከሰቱ አደራ ለማለት ነው፡፡
——–///———–
ሌላም አንድ ነገር እየታዘብኩ ነው፡፡ ጎንደር ዩኒቭርስቲ ውስጥ የዚህ ብጥብጥ መሪዎች አሉ፤እርምጃ ይወሰድ ምናምን የሚል፤እኔ ደግሞ እናስተውል እላለሁ፡፡ ችግር ያለባቸው ግለሰቦች ይኖሩ ይሆናል፤ ግን ግን- አንዳንዶቹ ደግሞ በቅርብም የማውቃቸው አሉና ጥንቃቄ ብናደርግ፡፡ ጎንደር ዩኒቭርስቲ ስማር ሁሉን ነገር አውቀዋለሁ፤ ሆኖም ዛሬ ከምሰማቸው ስሞች ጋር የማይሄዱ ሰዎችን እያነሳችሁ ስለሆነ ትንሽ ጥንቃቄ ቢደረግ ለማለት ነው፡፡ በማያውቁት ቅሬታ የሚገቡ ሰዎችን ማባዛት እንዳይሆን ብየ ነው፡፡ በዚህ በኩል እንዲህ ለመናገር፤የማያወላዳ  መረጃ ስለመያዛችሁ እርግጠኛ ሁኑ፡፡
————////———
ሌሎች ጉዳዮች፡
1.አቶ ገዱ ጉብኝቱን አቋርጦ ወደ አገር ቤት ቢመለስ ጥሩ ነው፡፡ በእንዲህ አይነት ወቅት የሱ መኖር እጅግ አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም ስልጣን በሱ እጅ ናት፤አንዳንዱ ስልጣን በውክልና አይሆንም፡፡ ቀሪውን ስብሰባ አብሮ የሄደው አንድ መንጋ ሰው ይከውነው፡፡
2.አዴፓ ሰሞኑን ሦሰት ወጣቶቹን መሾሙን ሰምቻለሁ፡፡ አማራ አካዳሚ ውስጥ የገባው ሸጋ ነው፡፡ የሁለቱ ልጆች ግን ምክነት ነው፡፡ መልካሙ ለትምህርት ጥራት? ወይ ዘንድሮ? የአማራ ፍትህ ጉዳይ በጤና ከርሟል ማለት ነው? ስለ በህግ ተምሮ የትምህርት ጥራት ኋላፊ? ገጣሚው ወጣት ስምሪቱ ጥሩ ቢሆንም…..ብቻ አልጣመኝም፡፡ ለነገሩ በዚህ ጉዳይ መተቸት ትቸ ነበር እንዴው ከገባሁ አይቀር ብየ ነው፡፡ ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት አዴፓ ምደባን በተመለከተ እንደስትራቴጅ የሚከተለው፤ እኛ በምናቀርበው ትችት የተገላቢጦሹን ስለሆነ ፡፡
Filed in: Amharic