>

ትግራይን ለመገንጠል መሞከር አጉል መንፈራገጥ ነው!!! (ስዩም ተሾመ)

ትግራይን ለመገንጠል መሞከር አጉል መንፈራገጥ ነው!!!
ስዩም ተሾመ
ለማንኛውም ወ/ሪት ግደይ ትባሓል ውሂጥ ሴትዮ #የትግራይ_ነፃነት ነገ ሊታወጅ እንደሆነ፣ ድል በእጃቸው እንደሆነ በመግለፅ #ሞት_ለኢትዮጵያ በማለት ቅዠቷን ገልፃለች፡፡
አደዋ ላይ የፈሰሰው ደማችን፣ ባድመ ላይ የተከሰከሰው አጥንታችንን ይዞ ልክ እንደ ተከራይ ውልቅ ብሎ መሄድ የለም፣ አይቻልም፡፡ እንደ ተከራይ ውልቅ ከማለታችሁ በፊት ነገሮችን ውልቅልቅ አድርጎ ማየት ያስፈልጋል፡፡
በመጀመሪያ:-
* ወልቃይት ፀገዴ፣ ሁመራ እና ራያን በፀባይ እንደወሰዳችሁ በክብር ትመልሳላችሁ፡፡
*  በመቀጠል በትግራይ ከሚኖሩት የአንድርታ፣ ተንቤን፣ አጋመ፣ ኩናማ፣ አፋር፣ ኢሮብ፣…ወዘተ ጎሳዎች ቁጭ ብለን እንመክራለን፡፡ መገንጠል ፍቃዳቸው ከሆነ የእነሱን ምርጫ እናከብራለን!! ነገር ግን በቅድሚያ ሌቦችና ወንጀለኞች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው፡፡
ይህ ካልሆነ ግን ዝም ብለን ትግራይን ለሌቦች አሳልፈን አንሰጥም!! ምክንያቱም ከሌቦች ጋር የሚወራረድ ብዙ ቀሪ ሂሳብ አለን፡፡
ሌላው ቢቀር ለምሳሌ #ጌታቸው_አሰፋ እና #አባይ_ፀሓዬን የመሰሉ ሰዎች ይዞ መገንጠል አይቻልም፡፡ የኢትዮጵያዊያን ደምና ብር በእነዚህ ሰዎች እጅ አለና፡፡ ይህን ሳይመልሱ ንቅንቅ የለም፡፡ ይህ ከዚህ ትውልድ የተወሰደ ነው፡፡ የዚህን ትውልድ ደምና ብር ከፍለው ቢጨርሱ እንኳን የቀድሞ አባቶቻችን ደምና አጥንት ከፍለው የሚጨርሱ አይመስለኝም፡፡
እሱን ከማስከበር በቀር ሌላ ምርጫ የለንም፡፡ የአሉላን አባ ነጋን ርስት አሳልፋችሁ በመስጠታችሁ እስካሁን ቁጭቱ አልወጣንም፡፡ የአደዋ ጀግኖችን፣ ባድመ ላይ የተሰውትን አሳልፈን አንሰጥም፡፡ በመሆኑም ከመገንጠላችሁ በፊት በደማች የወዙትን የአደዋን ተራራዎች፣ በአጥንታችን የተከሰከሰበትን #ባድመ መረከቦ አለብኖ፡፡ ከዚያ በመቀጠል #በአክሱም_ፂዮን ያለው የሙሴ ፅላት የህዝበ ክርስቲያኑ ነው፣ የአልነጋሺ መስኪድ ደግሞ የእስልምና እትብት ነው፡፡ ማንም በይገባኛል የማይወስደው፣ የማይሰጠው የእኛነታችን ማህተብ ነው፡፡ በዚህ ላይ ከተስማማን ምርጫው የእናንተ ነው፡፡ ምክንያቱም መቀመጫችሁ የሚሆነው፤ ወይ !ሱዳን አሊያም #ደደቢት ነው፡፡ ያው ደደቢት ደግሞ የሚገኘው ወልቃይት ነው! አሁን የቀራችሁ ያው ሱዳን ብቻ ነው!! አዎ ሰሞነኛ ፍቅራችሁ ከእነሱ ጋር ነው፡፡ ወደ ሱዳን መሄድ ለሚሻ መንገዱን ጨርቅ ያድርግለት!! ትግራይ መገንጠል መሞከር ግን አጉል መንፈራገጥ ነው! ውጤቱም አጉል መላላጥ ነው!!
ውድ የትግራይ ህዝብ ሆይ… ሀገር እና ህዝብ ከህወሀት በፊት ነበሩ ወደፊትም ይኖራሉ!
የህወሓት አመራሮችና አፈ-ቀላጤዎች በነገው ዕለት “መሬት አንቀጥቅጥ” የሆነ የድጋፍ ሰልፍ በመቀሌ ከተማ እንደሚካሄድ እየገለፁ ይገኛል። እነዚህ የህወሓት ካድሬዎች በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለማመን የሚከብድ በደልና ስቃይ ሲፈፅሙ የነበሩ ሌቦችና ጨካኞች አሊያም ለዚህ እኩይ ምግባራቸው ጥብቅና የቆሙ ህሊና-ቢስ የሆኑ ሆድ አደሮች ናቸው። ላለፉት 27 አመታት በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ቅጥ-ያጣ ዘረፋና ጭካኔ የተሞላው ተግባር በመፈፀማቸው ለውርደትና ውድቀት የተዳረጉ፤ የተቀረው ዓለም በገዛ ሀገራቸው ላይ በፈፀሙት ግፍና በደል አንቅሮ የተፋቸው፣ ከኢትዮጵያ ውጪ መሸሸጊያ ጥጋት የሌላቸው፣ ከህግና የህሊና ፍርድ ለማምለጥ ወደ ትግራይ በመሸሽ በመካከላችሁ የተደበቁ ጉዶች ናቸው።
በተመሳሳይ ባለፈው ሳምንት በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል እነሱ በቀሰቀሱት ግጭት ብዛት ያላቸው የአማራና ኦሮሞ ተወላጆች በተገደሉበት ሳምንት “በትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ የብሔር ጥቃት ይቁም” በሚል ሰላማዊ ሰልፍ መጥራታቸው ይታወሳል። ወጣቶችን የጦር መሳሪያ አስይዘው አደባባይ እንዲወጡ ካደረጉ በኋላ በተለያዩ የክልሉ ከተሞች “ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ“ የሚል ዲስኩር አሰሙ። አዛውንት እናቶችን በትልቅ ጎራዴ ላይ የትግራይን ባንዲራ እያውለበለቡ እንዲወጡ አድርገው አረንጓዴ፥ ቢጫ፥ ቀይ ባንዲራ አክሱም ጹዮን ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ እንዳይውለበለብ ከልክለዋል። እናቶችን በአደባባይ ጦርነት እንዲቀሰቅሱ የሚያደርጉ፣ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ስለ ሰላም እንዳይፀልዩ የሚያውኩ፣… ፈሪሃ-እግዚያብሔር የሌለባቸው፣ የሰይጣን መንፈስ የተጫናቸው ክፉዎች ናቸው።
የትግራይ ህዝብ ሆይ…. የህወሓት ካድሬዎችና የእነሱ ድቀመዛሙርት፤ ከኢትዮጵያ ህዝብ የዘረፉት ሃብት መላ ያሳጣቸው፣ የንፁሃን ደምና እምባ ያሰከራቸው፣ ህሊናቸው ታውሮ ማስተዋልና ማመዛዘን የተሳናቸው፤ ጥሩና መጥፎ፣ ትክክልና ስህተት፣ ሥራና ወንጀል፣ ሰላምና ጦርነት የተምታታባቸው ድኩማኖች ናቸው። ባለፉት ወራት በተግባር እንደታዘብነው፤ እነዚህ ሰዎች “የድጋፍ ሰልፍ” የሚጠሩት ሽንፈትና ውርደታቸውን ለመሸፋፈን፣ “የተቃውሞ ሰልፍ” ሲጠሩ ደግሞ ለትግራይ ህዝብ መልካም የሆነን ነገር ለማስተጓጎል እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል።
Filed in: Amharic