>

ወለጋን የኢትዮጵያ ዳርፉር ለማድረግ እየተሰራ ነው!!! (ብርሀነ መስቀል አበበ (ዶ/ር))

ወለጋን የኢትዮጵያ ዳርፉር ለማድረግ እየተሰራ ነው!!!
ብርሀነ መስቀል አበበ  (ዶ/ር)
ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ የነዚህን ሰዎች መሰሪ ሴራ ማፍረስ አለበት። የኦሮሞ ህዝብ ለዚህ ግንባር ቀደም ኃላፊነት አለበት። ምክንያቱ ኦሮሚያ የዚህ ጦርነት መዕከል እንድትሆን ጠላቶቻችን መርጠዋል!!!
በውጭም ሆነ በአገር ውስጥ ያላችሁ የኦሮሞ አክቲቭስቶች በፕሬዝደንት ለማና ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ላይ የህወሃት ካድሬዎች በተደራጀ መልኩ እያደረጉ ያሉትን ዘመቻ በሚገባ መረዳት አለባቸሁ።
ትናንት የኦሮሞን ህዝብ ሲገሉና ሲያስገድሉ የነበሩት የህወሃት ካድሬዎች ዛሬ ከኦሮሞ በላይ ኦሮሞ ለመሆን ይጥራሉ። ለማና አብይ ላይ ኦሮሞን መቀስቀስ ቁርስ፣ምሳ እና እራታቸው ነው።
ለማና አብይ ኦህዲድን ከቀሟቸው ወዲህ ሌላ የኦሮሞ ድርጅት በጉዲፈቻ ለማሳደግ በብዙ  ሚልዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ኦሮሚያ ውስጥ እያፈሰሱ ነው። ለኦሮሞ ድርጅት ለመገንባት አይደለም። ኦሮሞን ለመበታተን እና ለማባላት ነው።
 በተመድ ሰላም መስከበር ስራ ተሰማርተው አገር እንዴት እንደሚፈርስ ያዩት የህወሃት ታጣቂዎች ያንን እውቀታቸውን ኢትዮጵያን፣ በተለይም ኦሮሚያን ልያፈርሱ ሌት ተቀን እየሰሩ ነው።
 ወለጋን የኢትዮጵያ ዳርፉር ለማድረግ እየተሰራ ነው። ይህ አደጋ የኦሮሞ ህዝብን ሁሉ ልያሳስብ ይገባል። ይህ የፖላቲካ ቁማር አይደለም። መፍረስን እያለማመዱን ነው። ወለጋ የጀመሩት ነገ ጠዋት ሸዋ፣ በሚቀጥለው ቀን ሃረር ከዚያ ወሎና ጎንደር የማይደርስበት ምክንያት የለም።
 በጥናት እና የአገር ማፍርስ አቅም ባላቸው ባለሙያዎች ታግዞ እየተደረገብን ያለ ዘመቻ መሆኑ ምልክቶቹን ለሚያይ ሁሉ ግልፅ ነው። ሌላው ቀርቶ የህወሃት ካዲሬዎች ህዝብ ግብር እንዳይገብር እያደረጉ ነው።
 ህዝባችን ያልገባው አንድ ነገር ያለ ይመስለኛል፡የህወሓት ድርጅት በ27 ዓመታት ውስጥ መፍጠር የፈለጉት ህብረተሰብ ፈጥረው እንደሄዱ የተረዳን አልመሰለኝም፡ ቢያንስ አንድ አይነት የሆነን ህብረተሰብ እንኳን እንዳይደማመጥ፡እንዳይሰማማ፡ ማድረግ  መቻላቸውን አሁንም መባነን አልቻልንም፡፡
    በ27 ዓመታት ውስጥ ለመጥፎም ስራ ቢሆን እንደ ህወሓት አይነት ታች ድረስ የሚደርስ መዋቅር እና አደረጃጀት በሁሉም ክልሎች ያደራጀ ድርጅት አለ ብዬ አላምንም፡ ይህን እኛ አሁንም አላጤንም፡ ድሮ የጎረቤት አባቶችን ከምንሰራው ነውር የምንደበቅ ልጆች፡ ዛሬ በህወሓት መዋቅር አደረጃጀት፡ የአባ ገዳ ሽማግሌዎችን፡የሀይማኖት አባቶችን፡ ቤተሰቦቻችንን አለመስማት ደረጃ አድርሶናል፡፡አሁንም በክልል መንግስት ደረጃ የነ ኦቦ ለማን ንግግር ከልመና ያክል በመቁጠር ለመታበይ የምንፈልግ አለን፡፡ይህ ነገር ከወዲሁ ነቅተን በጊዜ ማረም ባለመቻላችን፡ በህዝባችን ላይ የሚፈጥረው የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ተፅዕኖ ቀላል ነው የሚባል አይደለም፡፡
 ይህ አደጋ በነዝላልነት መታየት የለበትም። መንግስት ግልፅ ህጋዊ እርምጃዎችን መውሰድ አለበት።
ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ የነዚህን ሰዎች መሰሪ ሴራ ማፍረስ አለበት። የኦሮሞ ህዝብ ለዚህ ግንባር ቀደም ኃላፊነት አለበት። ምክንያቱ ኦሮሚያ የዚህ ጦርነት መዕከል እንድትሆን ጠላቶቻችን መርጠዋል።
Filed in: Amharic