>

የመቀሌው ሰልፍና የአቢቹ መንግሥት ፈጣን ምላሽ!!!

የመቀሌው ሰልፍና የአቢቹ መንግሥት ፈጣን ምላሽ!!!
ዘመድኩን በቀለ
★ መገለልና መድሎ ይቁም ! 
~ የዐቢቹ መንግሥት አሁንም ለትግሬው ህወሓት ያዳላል። ይፈራዋልም። ፈጣን የሆነ ምላሽ የሚሰጠውም ከመቀሌ ለሚነሳ ጥያቄ ብቻ ነው እየተባለም ይታማል።
~ ትናንት ሕዳር 29/2011 ዓም በትግራይ ክፍለ ሀገር በመቐለ ከተማ ” ሕገ መንግሥቱ ይከበር ” በሚል መሪ ቃል መቀሌ አንቀጥቅጥ ሰልፍ ተደርጎ ነበር። የዚህን ሰልፍ ፕሮቫ  ሰልፉ ከመደረጉ በፊት በዋዜማው በመቀሌ ጎዳናዎች ላይ የፌደራል መንግሥቱን ሽብር ውስጥ የሚከት ” ሰሜን ኮሪያዊ ” ትዕይንት ተደርጎ ስለነበር የዐቢቹ መንግሥት መሸበሩ አልቀረም። በተለይ በማግሥቱ ሰልፉ ላይ የሚንፀባረቁ መፈክሮች ቀደም ብለው ለመንግሥት በመድረሳቸው መንግሥት ከወደ መቀሌ የሚመጣው ጥያቄ ስላስፈራው ፈጣን ምላሽ ለመስጠት መወሰኑም ነው የተነገረው።
መንግሥት በውሳኔውም መሠረት መቀሌ ሰልፍ እየተደረገ፣ ገና ሰልፉ ሳያልቅ፣ ደብረ ፅዮን ሳይናገር፣ ጌታቸው ረዳ ሳይፎክር፣ ቲም ስብሃትም ሳይጨፍር፣ አክቲቪስቱ ሁላ ሳይወጥር፣ ሳይደሰኩር ለመቀሌው “የሕገ መንግሥቱ ይከበር” ጥያቄና ሰልፈኞቹም ያሰሙት ድምጽ ሳይውል ሳያድር፣ እናስብበት፣ ቆይ እስቲ እንምከርበት፣ ነገሩንም ጊዜ ወስደን በጥሞና እንየው ሳይል በፍጥነት አዲስ አበባና ቤኒሻንጉል ላይ ምላሽ በመስጠት መቀሌን በደስታ ማዕበል አጥለቅልቋታል።
በዚህ የአብቹ መንግሥት ፈጣን ምላሽ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በብስጭት ሲስቅ ውሎም አድሯል። ስንትና ስንት ዓይነት ሰልፍ በኢትዮጵያ ምድር ተደርጓል። ለእዚያ ሁሉ ሰልፍ ምላሽ ያልሰጠው መንግሥት እንዴት ገና ለገና ነገ ሰልፍ እንወጣለን ብለው ማስታወቂያ ብቻ ለሰሩ የመቀሌ ነዋሪዎች ምላሽ ይሰጣል በማለት ህዝቡ በደስታ አኩርፏል ነው እየተባለ ያለው።
ለማንኛውም በመቀሌው ሰልፈኞች ጥያቄ መሠረት የዐቢቹ መንግሥት መኖሪያቸውን በአዲስ አበባ ከተማ ያደረጉትንና መቀለ በሚገኘው የህዝብ ጫካ ውስጥ ገብተው ያልተደበቁትን የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከፍተኛ አመራር የነበሩትን አቶ #መዓሾ_ኪዳኔ_ዓለሙ እና አቶ #ሓዱሽ_ካሳ_ደስታ የተባሉትን የአቶ ጌታቸው አሰፋን ረዳቶች በቁጥጥር ስር አውሎላቸዋል።
መንግሥት በዚህ ብቻ ሳያበቃ በመቐሌው ” ሕገ መንግሥቱ ይከበር ” ድምጽ ከመበርገጉ የተነሳ በኋላ እነዚህ ሰዎች ፊታቸውን ወደ እኔ ሳያዞሩ በፊት ጥያቄያቸውን ልመልስ በማለት በአሶሳ ከተማ 5 ቀንደኛ የህወሓት ደኅንነቶችና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግጭቶችን ሲያደራጁ ሰያስተባብሩ፤ ዐማራና ኦሮሞውንም እሳትና ጭድ ለማድረግ ሲያስተባብሩ የነበሩት የተባሉ አምስት ግለሰቦችን ምሽቱን በፌድራል ፓሊስ ቁጥጥር ስር በማዋል በድጋሚ ለትግራይ ህዝብ ወገናዊነቱን አሳይቷል ተብሎም እየተወቀሰ ነው።
እኒህ ሰላዮች ቀደም ሲል በካማሽ ዞን ያሶ ወረዳ ነዋሪ የነበሩ ዐማራዎች እና ኦሮሞዎችን ሲያጋጩ እና ሲያፈናቅሉ ቆይተው በፓሊስ እንደሚፈለጉ ሲያውቁ ጫካ ተደብቀው ከከረሙ በሃላ አሁን ወደ ትግራይ ሊያመልጡ ሲሉ በአሶሳ ከተማ በቁጥጥር ስር ውለው ገቢ መደረጋቸው ነው የተነገረው።
እነዚህ ገቢ የተደረጉትም
 ኢንጅነር ጌታቸው ገብረፃዲቅ ፤  
አቶ አረጋዊ ገብረፃዲቅ ፤ 
አቶ ክብሮም ታመነ፤ 
አቶ ገብረሥላሴ ገብረማርያምእና ወሮ ሙሉ ብርሃን በርኻ ናቸውም ተብሏል።
የዐቢቹ መንግሥት በዚህ ዓይነት ዐይን ያወጣ መድሎና አድሎ ወደፊትም የትግራይን ህዝብ ድምፅ ብቻ የሚሰማና በዚህ አካሄዱ ከቀጠለ፤ እነ አባይ ፀሐዬን፣ እነ ጌታቸው አሰፋንና ሌሎችንም ሕገ መንግሥቱን አስገድደው የደፈሩ ግለሰቦችን በቶሎ በቁጥጥር ስር የማያውል ከሆነ የትግራይ ህዝብ ትእግስቱ አልቆ በዓለም ላይ ታይቶ የማይታወቅ ጥፋት በጎረቤት ሀገር ኢትዮጵያ ላይ ያደርሳልም ተብሎም እየታለመ ነው። ህልም ነው።
ለማንኛውም መንግሥት የትግሬን ድምጽ ብቻ አይስማ። የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ድምፅ በእኩልነት ያዳምጥ። ለአንዱ አባት ለሌላው የእንጀራ አባት መሆኑን ያቁም። ገና ለገና ህውሓት ደርግ በተመሰረተ በ6 ወሩ ጫካ ገብታና ታግላ ደርግን ጥላለችና እኔም ገና ሥልጣን በያዝኩ በ6 ወሬ 3 ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው አስፈራርተውኛል፣ እናም ምን አልባት እንደ ደርጉ ጊዜ አሁንም ጫካ ገብተው ሥልጣኔን ሊገዳደሩ ይችላሉ ብሎ በመንቦቅቦቅ ብቻ እነሱ ሰልፍ በወጡና ተቃውሞ ባቀረቡ ቁጥር ፈጣን የሆነ ምላሽ የመስጠቱን ነገር የአቢቹ መንግሥት ቢያሰብበትና ልክ ማስገባቱን ተጠናክሮና አጠናግሮ ቢቀጥልበት መልካም ነው የሚሉም አሉ።
የሚገርመው ነገር በኋላ እንደተሰማው ከሆነ ከጥቂት ተከፋይና ቀለብተኛ ካድሬዎች በስተቀር አብዛኛው የመቀሌ ነዋሪ በተለይ ምስኪኑ የመቀሌና የአካባቢው ህዝብ ስለ ሰልፉ የተነገረውና የሚያውቀው ” የብሔር ብሔረሰቦች ” በዓል በመቀሌ እንደሚከበርና ለዚህም በዓል ሲባል የሱዳንና የሰሜን ኮሪያ ፕሬዝዳንቶች እንደሚመጡ ነበር ተብሏ። ህዝቡ ላይ ቀላል ነገዱቡት እንዴ እነዚህ ሜቴካሞች።
በመጨረሻም በመቀሌው ሰልፍ ላይ የተያዙትን ታሪካዊ መፈክሮች ታዩ ትመለከቱ ዘንድ በሰነድም መልክ ለትውልድ ይቀመጡ ዘንድ ተያይዞላችኋል።
ማስታወሻ | ~ እስከዛሬ ድረስ በተደጋጋሚ ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት ከአቢቹ መንግሥት ምላሽ ያለገኘው መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከክልል ትግራይ ጋር በመነጋገር ሰላማዊ ሰልፎችን በመቀሌ ቢያደርግ ፈጣን ምላሽ እንደሚያገኝ ታዋቂው የፖለቲካ ሳይንቲስ አቶ አየለ ጫሜሶ መናገራቸው ተሰምቷል። ህዝቡ ምናልባትም መቀሌ መሄድ ሳያስፈልገው ዋ መቀሌ ሄጄ ልሰለፍ ነው ብሎ ካስወራም የአቢቹ መንግሥት ድንብርብሩ እንደሚወጣና ጥያቄዎችን ያለ ቢጫዋ ኢሊኮፍተር እንደሚመልስም ታውቋል ነው የሚባለው። ከምር እስቲ ሌሎቻችሁም ሰላማዊ ሰልፍ መቀሌ ላይ ሞክሩ። የሆቴልና የትራንስፖርት ብቻ ብታወጡ ነው።
ሻሎም !  ሰላም !
Filed in: Amharic