>
5:14 pm - Thursday April 20, 6884

ህውሀት ሁሉ ታሟል ሁሉም ራሱን የሚያጠፋና የሚጠፋፋ ይሆናል !!! (ሉሉ ከበደ)

ህውሀት ሁሉ ታሟል ሁሉም ራሱን የሚያጠፋና የሚጠፋፋ ይሆናል !!!
ሉሉ ከበደ
ህገመንግስቱ የሚከበርበት ሰዎች እጅ ሲገባ “ህገ-መንግስቱ ይከበር”  አሉ የወያኔ ሰልፈኞች። ይኸው ህገ-መንግስት ጠረጴዛቸው ላይ እያለ ነበር ሀያሰባት አመታት የኢትዮጵያን ህዝብ ያረዱት ያስተራረዱት። ሀያ ሰባት አመታት የኢትዮጵያ ህዝብ ልጆቹ በያደባባዩ ሲጨፈጨፉበት፤ በያደባባዩ ሲያለቅስ፤ ሲጮህ ፤ ትግራይ ውስጥ ዘፈን ፤ዳንኪራ ፤ፌሽታ፤  ነበር በየቀኑ።
ጊዜ ተገለበጠና አሁን ደሞ “ያጊዜ ይመለስልን” እያሉ በተራቸው አደባባይ እየወጡ መጮህ ጀመሩ። ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ የሰቆቃ ጊዜ የነበረው ለነሱ የፍሰሀ ዘመን ነበር። ሁላችንም እኩል ተደስተን እንኑርባት ይችን ሀገር ወይስ እኛ ወደ ሰቆቃችን ተመልሰን የነሱ የፍሰሃ ኑሮ እንዲቀጥል እንፍቀድላቸው?
“የገነባናት ሀገር ካላከበረችን የምታከብረንን ሀገር ለመገንባት እንገደዳለን ” ብለዋል ንኮች። ሰዎቹ ታመዋል ያልኩት እዚህ ላይ ነው። ያደረጉትን ነገር አያውቁም ? ኢትዮጵያን ማፍረሳቸውን አልተረዱም? የትኛዋን ሀገር ነው የገነቡት? ትግራይን? ያን አድርገዋል። አንከራከራቸውም።
እዚህ በስደት በምኖርበት ሀገር ነርሶች ኮሌጅ ገብቼ ነበር። አንድ ቀን አስተማሪዋ ያስተማረችኝን የበሽታ አይነት በእውን ለማየት አስብ ነበር። ይህ ነው ተብሎ በማይታወቅ ሰበብ ያንድ አካባቢ ሰው በጅምላ አእምሮው የሚታመምበት የበሽታ አይነት ነው። “Mass Psychogenic illness ”  እንደዋዛ አስተማሪዋ የነገረችኝን እና መጽሀፉ ላይ ያለውን ተረድቼ አለፍኩት እንጂ በሽታውን በተግባር የትም አላየሁትም  ።  የትግራዩን ሰልፍ ሳጤን  ግን  የበሽታውን ምልክት አየሁት መሰለኝ ።
በጅምላ የመሳከር፤ አቅል የመሳት፥ ከቁጥጥር ውጭ የወጣ ስሜታዊነት፤  መሰረት የሌለው መበርገግ፤ መርበትበት ፤ መደናገጥ፤  የሆነ ያልሆነውን በመለፍለፍ ታማሚዎች ፈውስ ያገኙ ይመስላቸዋል። ሰልፈኞቹ የሱዳንን ሀገርና መንግስት ያመሰግናሉ ።ያስመሰገናቸው ነገር ምንድነው? ሀገራቸው ኢትዮጵያ እንጂ ሱዳን አይደለችም።መንግስታቸው የኢትዮጵያ መንግስት እንጂ የሱዳን መንግስት አይደለም። እንዳለፉት አስራ ሰባት አመታት ሱዳን አዝሎ እንደገና ኢትዮጵያን ያስወጋናል ብለው አስበው ይሆን? ወይስ መቀበሪያችን እዚያው ይሆናል ብለው? ሰዎቹ ታመዋል አልኳችሁ።  የሆነ ያልሆነውን በመለፍለፍ በመሳደብ ፈውስ  የሚያገኙ ይመስላቸዋል። ከጭንቀታቸው የሚገላገሉ ይመስላቸዋል። በሽታው ምንጩ አይታወቅም ባንድ ጊዜ ያንድን አካባቢ ህዝብ ይወራል። ለምሳሌ ህዝቡ በሙሉ የሌለ ነገር ሊሆን እንደቀረበ ያምናል።  ጠላት ሊወረን ብሎ ያምናል። እዚያ  ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ያሉ ስዎች አማራ ሊወረን ነው ወይም ኢትዮጵያ ልትወረን ነው ብለው ያመኑ ይመስላል። መታመም ነው.። “ወጣቶች ለክፉም ለደጉም ተዘጋጁ” ብሏል ደብረጽዮን ። እብደትነው። ማንን ለመውጋት ነው የሚዘጋጁት? እርግጥ በስልጣን ላይ የነበሩ ሁሉ ከባድ ጭንቀት ውስጥ ወድቀዋል።   የማያመልጡት ሁለት ከባድ አደጋ  ተጋርጦባቸዋል። ከስልጣን ተወገዱ። የሚዘረፈው የሀገር ሀብት ባንድ ጊዜ ቆመ። ሀያ ሰባይ አመት ያዘረፉትን የማስመለስ ስራ ተጀመረ። ያፈሰሱት ደም የሚያስጠይቅበት ቀን መጣ። እዚህ ላይ እነዚ ሰዎች የማይችሉትን የማይቋቋሙትንም ሀገር ተነስተው ሊያስወርሩ  ይችላሉ። እንደዝንብ ከረገፉ በኋላ ይሆናል ያደረጉትን ነገር የሚያውቁት።
የሩዋንዳው ፍጅት ጊዜ ገዢው ፓርቲ ኢንተርሃምዌ የሚል መጠሪያ የሰጣቸው በወጣቶች የተገነባ ልዩ ሀይል ነበረው ። በሱማሌ ክልል “ዩጎ” ብለው  አብዲ ኢሌና ህውሀት አደራጅተው ብዙ ጥፋት ያደረሰውን ወጣት ታጣቂ ያስያውሷል።በትግራይ ልዩ ሀይል ተብሎ  ሀሪቱን በተለይ አማራውን በመበጠበጥ ላይ እንዳሉት አይነት።  ህውሀት ሀያሰባቱንም አመታት የትግራይን ወጣቶች በውትድርና ሲያሰለጥን ነው የኖረው ። የአስራ ሁለት አመት ህጻን ሳይቀር የጦር መሳሪያ አጠቃቀምና ውጊያ ሲያሰለጥኑ እንደነበረ በተለያየ ጊዜ መረጃ ተመልክተናል። በትግራይ ውስጥ አይደለም ከትግራይ ውጭ ያለ የትግራይ ተወላጅ ሁሉ እስከሚበቃው የጦር መሳሪያ የታጠቀ ነው። እርግጥ ለራሳቸው መጥፊያ ነው የሚሆነው። በትግራይ ስላለው የመሳሪያ ክምችት ከሚገባው በላይ መረጃ ሲደርሰን ኖረናል። አንድ ኮንቴይነር ሙሉ ገጀራ ወደ ትግታይ ያመራበትም ወቅት እንደነበረ ሁሉም የሚዘነጋው አይደለም።
 የሩዋንዳ ሁቱዎች ኢንተርሀምዌ ብለው ፈተው የለቀቋቸው ህጻናት ታጣቂዎች ነበሩ በቱትሲዎች ጭፍጨፋ ላይ ዋና ተዋናይ የነበሩት። ወያኔም ፈቶ ሊለቅብን ነው ህጻናቶቹን “ተዘጋጁ ” የሚለው? ይህን ያህል ሀላፊነት የማይሰማቸው ከሰው አይደለም ከንሰሳ የወረደ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች በመሪነት ደረጃ የሚገኙባት ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት። ኢትዮጵያን ወረን ዳግም እናንበረክካለን ብሎ ከማሰብ ወዲያ መታመም ምን አለ? ትግራይ ውስጥ ህውሀት ሁሉ ታሟል። ሁሉም ራሱን የሚያጠፋና የሚጠፋፋ ይሆናል በቅርቡ። ነፍስ ይማር። ዶክተር አብይ ቆራጥ እርምጃ መውሰድ ያስፈልገዋል። የህዝብ አንድ መሆን ከምንጊዜውም በላይ ይጠበቃል። የትግራይ ህዝብ ወንድምህ ከሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ተባበር። የኦነግ በሽተኞች አደብ ግዙ ወይ ተጠቃላችሁ ወያኔ ካምፕ ግቡ።የኢትዮጵያ ህዝብ የለውጥ ሀይሉን በመደገፍ በማጠናከር ወደፊት ገስግስ።
Filed in: Amharic