>

ከምሥራቅ ሸዋ ኦሮሚያ ዐማሮችን  በይፋ ማስወጣት ተጀመረ!!! (ዘመድኩን በቀለ)

ከምሥራቅ ሸዋ ኦሮሚያ ዐማሮችን  በይፋ ማስወጣት ተጀመረ!!!
ዘመድኩን በቀለ
ምሥራቅ ሸዋ ማለት አዲስ አበባ አፍንጫዋ ስር ማለት ነው!
~ ድርጊቱ ህወሓት ስልጣን በያዘች ጊዜ በወልቃይትና በራያ ህዝብ ላይ የፈፀመችውን የዐማራውን ዘር የማጽዳትና ከርስቱም የማፈናቀል ተግባር ጋር ተመሳሳይ ነውም የሚሉም አሉ።
~ ለሆዳም ዐማራው፣ ለአንድነት ኃይሉ እና ሰፈር እንጂ ብሔር የለኝም ለሚለው አዲስ አበቤ ይህ “የውጣልኝ፣ ልቀቅልኝ፣ ጥፋ ከዚህ ” መፈክር ለሁሉም የመጥሪያ ደወል ይመስለኛል።
~በቀበሌና በወረዳ አማራሮች የሚመራው የአፈናቃዮቹ ቡድን ድርጊቱን ህጋዊ አስመስሎ እንዲመሠራ ነው እየተነገረ ያለው።
~ ቄሮ የተባሉት ወጣቶች በወረዳ አመራሮች ይሁንታ በዐማሮቹ የመኖሪያ ቤቶች በር ላይ ስማቸውን በመጻፍ የዐማሮቹን መኖሪያ ቤቶች ለመከፋፈል በዝግጅት ለይ መሆናቸው ተነግሯል።
~ ምንድነው ነገሩ? ብለው ጥያቄ ለማቅረብ የሞከሩ ዐማሮችንም በአደባባይ በቤተሰብ ፊት መረሸንም ተጀምሯል። ህፃናት ትምህርት አቋርጠዋል። አቅመ ደካሞች ያለ ጧሪ ቀበሪ ቀርተዋል። ገበያ ወጥቶ እህል መሸመት የማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል። አቅም ያላቸው ደግሞ ህፃናት ልጆቻቸውን ተሸከምው ሰሚ ብናገኝ ብለው ለአቤቱታ ወደ ክልል መጥተዋል።
~ አደንዛዥ ዕጿ #ኦሮማራ መፈክርም በድኑን ብአዴንንና የአንድነት ኃይል ነኝ ባዩን ሁሉ ለጉማ እና ጠርንፋ ዲዳም አድርጋ ማስቀመጧን ቀጥላለች። መቼም እሷ ነገር ማለትም ይቺ #ኦሮማራ ተብዬዋ መፈክር ለአቢቹ መንግሥት ፍቱን  የማደንዘዣ መድኃኒት ሆና እንደተገኘች ለማንም አልተገኘች። ስንቱን ጀግና እንቅልፋም አደረገችው። ስንቱን ልባም አጃጃለችውም። ለጥ ለሽም አድርጋ እንደ እከ  አስተኛችው። አይ ኦሮማራዬ ! በነገራችን ላይ ታማኝ በየነ ጠፋብኝሳ?
~ ይህን ዜና ኢሳት በመዘገቡ አድናቆቴ ከፍ ያለ ነው። ኢሳት ባደንቀውም ፤ ተፈናቃዮቹን ያፈናቀላቸው ዐማራነታቸው መሆኑን ከመናገር ሲቆጠብ ታይቷል። ኢቲቬ፣ ፋናና ኦኤምኤን ደግሞ ይዘግቡታል ተብሎ አይጠበቅም።
~ ብአዴን በአሜሪካ ሽርሽር ላይ ነው። አቶ ንጉሡ ከእነ ጃዋር ጋር አዲስ ፍቅር ላይ ነው። አቶ ደመቀ መኮንን የአብቹ ጋርድ ሆኖ በየቦታው ጋቢ መሸለም ላይ ነው። ጎንደር ጦርነት ተከፍቶበታል። በቤኒሻንጉል ዐማራው ውጣ ተብሎ ይፈናቀላል። አዲስ አበባ ጫፍ ካራ ቆሬ በሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች እየተፈናቀሉ ነው።
~ አሁን ነገሩ ጫፍ ደርሷል። ያበጠው መፈንዳቱ አይቀሬ እየሆነም ነው። አሁን ኢትዮጵያዊ ነኝ ማለት ማንንም እንደማያድን ለመናገር ነቢይ መሆን አይጠበቅም። ኦሮሙማና እስልምና ከፕሮቴስታንትነት ጋር ሰልቅጦ ሊበላን ከደጃችን ቆሟል። አዲስ አበባ ሰምተሃል።
★ ህወሓት ሆይ እግዚአብሔር ይይልሽ። ታቦተ ጽዮን ትፍረድብሽ። በቁምሽ በሰቀቀን ኑሪ። የወላድ መካን ሁኚ። ተቅበዝብዘሽ ባክነሽ ኑሪ። ሰላም ያሳጣሽ። የህጻናት፣ የአረጋውያን እንባ ጉርፍ ሆኖ ይጥረግሽ። እሳት ሆኖ ይፍጅሽ። ብድራቱን በምድርም በሰማይም እግዚአብሔር ይክፈልሽ። አሜን።
Filed in: Amharic