>

በረከት ዛሬም ኢትዮጵያን እንደፌደራል አገር እንደማያያት ይልቁንም እንደ ኮንፌደሬሽን እንደሚያያት በግልፅ አስቀምጧል!!! (ግዛው ለገሰ) 

በረከት ዛሬም ኢትዮጵያን እንደፌደራል አገር እንደማያያት ይልቁንም እንደ ኮንፌደሬሽን እንደሚያያት በግልፅ አስቀምጧል!!!
ግዛው ለገሰ 
በረከት ዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት፣ አብዮታዊ ዴሞክራሲና የወያኔ በላይነት መናፈቁ ሊገርመን አይገባም።
የበረከት ስምዖንን የመቀሌ ንግግር ሰማሁት።
የስብስባው ይዘት፣ ተጋባዦች፣ ቦታው ሲትይ ንግግሩ ነገን ሳይሆን ነገን መናፍቅ እንደሚሆን መገመት አያዳግትም። የበረከት ንግግር ውጥኑ ይህ ከሆነ ስኬታማ ነው፡፡ ከዚያ ያለፈ ትርጉም ግን ያለው አይመስለኝም።
ባጭሩ ሲጠቃለል ወደ ቀድሞው ስርዓት – ዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት፣ አብዮታዊ ዴሞክራሲና የወያኔ በላይነት – እንመለስ ነው።
ሲጀመር ብሄሮች እግዜአብሄር የፈጠራቸው ናቸው በስምምነት እናጥፋቸው ብንል እንኳን አይጠፉም በማለት መሰርት የሌለው የውሽት የክርክር ነጥብ ያስቀምጣና ህወህት ለሃያ ሰባት አመት የተከተለው የማንነት ፖለቲካ ምርጫ የሌለው ብቸኛ መንገድ ነው ይላል።
ይህ የመከራከሪያ ነጥብ የእምቧይ ካብ ነው። ሲጀመር ብሄሮች ተፈጥሮዋዊ አይደሉም፣ ብሄሮች ይጥፉ የሚለ ማንም ዜግም ይሁን ድርጅት የለም። በረከት በህወሃት የፕሮፓጋንዳ ጥበብ የተካነ ስለሆን ውሽት ሲደጋገም እውነት “ይሆናል” የሚለው ፅኑ እምነት አለው። የመፈክሮች መደጋገም በዜጎች ውሳኔ ላይ የሚኖርው ተፅእኖ ከፈተኛ መሆኑ በሰለጠኑ አገሮችም በተግባር የተፈተሸ ስልት ነው። በረከትና ጓዶቹም ሃያ ሰባት አመት የገዙት በፕሮፓጋንዳቸው ስኬት ይገነዘባሉ።
ችግሩ በረከትና ጓዶቹ ዛሬ በድግግም ውሸት የተገነባው የህዝብ ንቃት ተገርስሷል። ዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት አማራን/ትምክህትና ኦሮሞ/ጠባብን ከግራና ከቀኝ ጫፍ ፈርጆ ህወሃትን ዴሞክራሲያዊና የበላይ ለማድረግ የተቀየሰ ወጥመድ መሆኑ ተጋልጧል።
አብዮታዊ ዴሞክራሲ የዜጎችን ራስ በራስ መግዛት የማይፈቅድ የፓርቲ ሹመኞችን ለዘላለም በስልጣን የሚያቆይ ፌዝ መሆኑ ሁሉም አውቆታል። ከሁሉ በላይ የአብዮታዊ ዴሞክራሲንና የዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነትን ምንነት ዜጎች አይተውታል፣ ኖረውበታል። ውጤት አልባ፣ ሰላም የለሽ፣ ከፋፋይ፣ አሳሪ፣ ገራፊ፣ … መሆኑ ተረጋግጧል!!
በረከት ከዛሬ ሁለት አመቶች በፊት ኢትዮጵያዊ የሚባል ዜጋ የለም ሁሉም በክልሉ ነው ማለት የሚዘነጋ አይደልም፡፡ ዛሬም አቀራረቡ ሁሉም ክሎሎች ችግሮቻቸውን በየክልሎቻችው ይፍቱ አባባሉ ኢትዮጵያን እንደፌደራል አገር እንደማያያት (ፌደራሊዝም ከገባው) ምናልባትም አንድ ኮንፌደሬሽን እንደሚያያት ግልፅ ነው።
የበረከት አለመለውጥ ባይገርመኝም የየክልሉን ፅንፈኛ ብሄተኝነት ሲገልጥ የሄደበት መንገድ ነው። ሁሉም ክልሎች ፅንፈኝነት መኖሩን ለመግለጥ የየክልሉን ብሄርተኝነት አጀማመር ይገልጣል። የትግራይ ብሄርተኝነት የተጀመረው ብሄራው ጭቆናን ለመቃውም ነው የተጀመረው ይልና፣ የኦሮሞም፣ የደቡብም፣ የአዳጊ ክልሎችም እንደዚሁ ናቸው ይላል። የአማራ ብሄርተኝነትን አጀማመር ሲገልጥ ግን የተለይ ነገር ነገርን – እንደማንኛውም ብሄረ ብሄረሰብ እኩልነቱ ተከብሮ .. እንዲኖረ ነው አለ፡፡ በሌላ አነጋገር ሌሎች ብሄረዊ ጭቆናን ለመታገል ከተቋቋሙ፣ አማራው ብሄራዊ ጭቆና ከሌለበት ጨቋኝ ነበር ማለቱ ነው፡፡
በረከት ዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት፣ አብዮታዊ ዴሞክራሲና የወያኔ በላይነት መናፈቁ ሊገርመን አይገባም። ሊያጠያይቀን የሚገባው ይህና አይነት መድረክ ለምን ተፈለገ፣ ማንስ ፋይናንስ አደረገው የሚለው ነው።
Filed in: Amharic