>
9:16 am - Saturday December 10, 2022

የትግሬ ነጻ አውጭ ሰዎች ትውልድን በመግደል የተሳካ ስራ የሰሩ ጀግኖች ናቸው!!! (ሉሉ ከበደ)

የትግሬ ነጻ አውጭ ሰዎች ትውልድን በመግደል የተሳካ ስራ የሰሩ ጀግኖች ናቸው!!!
ሉሉ ከበደ
ሀገሩን ታሪን የማያውቅ፤ አንድ የጋራ ቋንቋ የማይናገር፤ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር  ሀገሩ እንደሆነች የማያምን፤ ከታጠረበት የዘር ክልል ውጪ ያለውን ወገኑን ሁሉ የሚጠራጠር የሚፈራ።  ከህግ ጋር የማይተዋወቅ፤ ከሞራል ከባህልና ከመንፈሳዊ በጎነት የወጣ ትውልድ እጃች ላይ ተገኘ!!
እምዬን፥ታላቁን ያፍሪካ ጸሀይ፥ ታላቁን የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች መቅሰፍት፤ ታላቁን አባት፤ የመተሳሰሪያ እትብታችንን ገመድ ጎንጉኑኖ፤ አንድ አድትጎን ፤ ያስራ ስምንተኛውን ዘመን ፈተና አሻግሮን ያለፈውን ንጉስ ሚኒሊክን ዛሬ ላይ የተፈጠረው ያልታደለ ኢትዮጵያዊ ትውልድ ፤ እንደቆሎ ባልንጀራው እሱ እያለ ሲሳደብ ስሰማ ልቤ በሀዘን ይደማል። አዝናለሁ ። የማዝነውም እኛ የወለድነውን ትውልድ ሌሎች ተቆጣጠሩት።ከጃችን ፈልቅቀው አወጡት።የባንዳ ልጆች በጠላት መንፈስና አስተሳሰብ ተኮትኩተው ያደጉ የኢትዮጵያ ጠላቶች አይናችን እያየ ትውልዱን በምርኮ እግራቸው ስር አሳደሩት። እነዚህ አራሙቻ ሰዎች ከምንም ተነስተው ነፍሳችንና ሀገራችንን መቆጣጠር የሚችሉበት ደረጃ እስኪደርሱ አምርረን ሳንዋጋቸው ቀርተን ድል አድርገውን ሀገራችንን ተቆጣጠሩ፤ ተወላጁን እነሱ በሚፈልጉት መንገድ ቀረጹት። ከዱር አራዊት የማይተናነሱት የትግሬው ነጻ አውጭ ነን የሚሉ ሌቦች።
የሀገሩን ታሪን የማያውቅ፤ አንድ የጋራ ቋንቋ የማይናገር፤ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር  ሀገሩ እንደሆነች የማያምን፤ ከታጠረበት የዘር ክልል ውጪ ያለውን ወገኑን ሁሉ የሚጠራጠር የሚፈራ።  ከህግ ጋር የማይተዋወቅ፤ ከሞራል ከባህልና ከመንፈሳዊ በጎነት የወጣ ትውልድ እጃች ላይ ተገኘ።
 አሁን ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ በጠላት ዘመን የተፈጠረ ህዝብ ነው። ይህንን ያልኩበት ምክንያት  ባሁኑ ሰአት የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት ከመቶ ሚሊዮን እንደሚበልጥ ሲገመት ሰባ በመቶ የሚሆነው ከሰላሳ አመት  እድሜ በታች ነው።  ወያኔ ኢትዮጵያን ሲቆጣጠራት የሶስት አመት እድሜ የነበረው ልጅ ዛሬ ሰላሳ አመቱ ነው። ሰባ በመቶውን የህዝብ ቁጥር የሚሸፍነው ይህ ነው። ወያኔ ሲገባ አምስት አመት፤ አስር አመት የነበራቸውን ብንደምራቸው አሁን ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ ሰማንያ በመቶው ከአርባ አመት በታች መሆኑ ነው። ይህ ማለት ባለፉት ሀያሰባት  አመታት የተፈጠረው ኢትዮጵያዊ ትውልድ በህይወት ልምድም በትምህርትም ያልበለጸገ በመሆኑ ሀገራችን እንደ ሀገር አደገኛ ሁኔታ ውስጥ መኖሯን የሚያሳይ ነው።
የሀሰት ታሪኮች በመጽሀፍ ተጽፈውለት ሲማር አደገ። ራስ ዳሽን ተራራ ትግራይ ውስጥ እንዳለ ተደርጎ መጽሀፍ ተጽፎለት ትምህርት ቤት ሄዶ ተማረው። በሂሳብ ትምህርቱ መደመርና መቀነስ ሲማር ይህን ያህል ቁጥር ያለው ነገር አለህ ። ከዚያ ላይ ጨቋኟ አማራ ይህን ያህል ወሰደችብህ  ስንት ይቀርሀል ?  የሚል ትምህርትም ተቀርጾለት ተማረ። ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ከመቶ አመት በፊት የሌለች፤ ህዝቧ አንዱ ያንዱ ጠላት እንጂ ከዚያ ያለፈ ግንኙነት እንደሌለው፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ዘሮች ሁሉ ለድህነታቸው ተጠያቂ አማራ የሚባል ዘር እንደሆነና ቋንቋውም ባህሉም ዘሩም እንዲጠፋ መሰራት እንዳለበት ሲማር አደገ። እኛማ ፈርተን በየቤታችን ተሸሽገን ልጆቻችንን ለአደጋ አሳልፈን ሰጠን።
ካለፉት ሰባት ወራት ወዲህም እነዚያው ጠላቶቻችን በየአካባቢው ግጭቶችን መፍጠር የቻሉት፤ የፈጠሩት አቅመ ደካማ ትውልድ በትንንሽ ነገር እየተሸጠም፤ እየተለወጠም ፤ እየተታለለም ፤የጥፋት ተልኮ ፈጻሚ መሆን ስለቀለለው ነው። ባግባቡ ማሰብ የሚችል ቢሆን ኖሮ ፤ ትክክል የሆነና ትክክል ያልሆነን ነገር መለየት የሚችል ቢሆን ኖሮ ፥ በትንሽ ነገር እየተደለለ ህይወቱንም አያጣም ።ህይወትም አያጠፋም። የራሱንም መኖሪያ ሰፈር በእሳት አያጋይም። የሀያሰባት አመታት የትግሬ ነጻ አውጭ መተት ውጤት።
የዚህ ስርአት ልጆች ዛሬ ዩኒቨርስቲ ገብተው በሰላም የትምህርት ገበታ ላይ ተቀምጠው  መማር ቢያቅታቸው ምን ይደንቃል? እንዲጠላሉ እንዲፈራሩ እጅግ ብዙ ተሰርቶ አድገው? የሁለት ልጆች ተራ ጠብ በአፍታ ተለውጦ ፤የሁለት ጎሳ ጦርነት ሆኖ ፤የትምህርት ብርሃን አለበት በተባለ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ህጻናት በድንጋይና በዱላ ተቀጣቅጠው የሚሞቱበት ዘመን ላይ ብንገኝ ምን ይደንቃል? ሀያ ሰባት አመታት ጠላቶቻችን ምን ሲሰሩ እንደነበር እያወቅን በፍርሀት ተሸብበን ኖረን ልጆቻችን ቢያፍሩብን እውነት የላቸውም እንላለን? ይቅር በሉን ልንላቸው ይገባል። እራሳቸው በስርአቱ ውስጥ ተወልደው አድገው እንደገና ሞተው እኛን ወላጆቻቸውን ነጻ ስላወጡን። ምንም እንኳን አንድ ራእይ አንድ ህልም ይዘው አልነበረም የተሰዉት ብንልም። እናም አሁንም ጉዟቸው አንድ ኢትዮጵያን ብለው ባንድ አቅጣጫ ነው ባንልም።  ከፊሉ ከደማቸው ጨርሶ እንዲወጣ ብዙ መዳኒት የተሰራለት ኢትዮጵያዊነት ከውስጣቸው አልወጣም ብሎ ስለቀረ አልተበታተንም። በእግዜብሄር ሀይል ኢትዮጵያን ያሉ ወጣቶች ለምልመዋል ።በዝተዋል።አቅጣጫ ማስያዙ ላይ መረባረብ ግዴታችን ነው። የለውጥ ሀይሉን ጠንክሮ ማጠናከር መደገፍ የህውሀትን ግብአተ መሬት ማፋጠን ብቸኛ አማራጭና ግዴታ ነው።
የትግሬ ነጻ አውጭ ሰዎች ኢትዮጵያዊ ትውልድን በመግደል የተሳካ ስራ የሰሩ ጀግኖች ናቸው። የኢትዮጵያ ወጣቶች ሰውን በድንጋይ እየወገሩ የገደሉበት ዘመን ነበረ? ወጣቶች ሆ ብለው በጅምላ ወተው  ሰብ አዊ ፍጡርን በሽመል ቀጥቅጠው መግደልን ስራ ያደረጉበት ዘመን ነበረ?  የእድሜ እኩያቸውን ባደባባይ ገለው ዘቅዝቀው የሰቀሉበት ዘመን ነበረ? ያንድ ከተማ ህዝብ ውሀ እንዳይጠጣ ያደረጉበት ዘመን ነበረ? ጀግናው ወያኔ ሀርነት ትግራይ ግን ይህን አይነት ትውልድ መፍጠር ችሏል።
ትውልዱን  እንዴት እናድነው? 
የወያኔን ግብ አተ መሬት ማፋጠን፤ የሀገር ፍቅር ትምህርት ዘመቻ ማካሄድ፤ ዛሬ ነገ ሳይባል ማንበብ መጻፍ የሚችል ዜጋ ሁሉ ትክክለኛውን የኢትዮጵያ ታሪክ እያነበበ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን ማስተማር፤ የሀይማኖት ተቋማት ወጣቶችን እያደራጁ ስለ አንድነት ስለፍቅር ስለ ይቅርታ ስለ መደረዳዳት ማስተማር፤ ዘፋኙ፤ ኮሜዲያኑ ፤ልክ እንደ እንዳልክ ፤ ተዋናዩ እስፖተኛው ሁሉም በየመስኩ ስለወንድማማችነታችን ፤ ስለ አንድነታችን መስበክ ።ማስተማር። የዘር ፖለቲካ ልክፍተኞችን ማግለል ፤ ማስወገድ፤ ወጣቱን የሚበክሉበትን መገናኛ መንገዳቸውን መዝጋት። እኔ ይህን ያህል ብያለሁ የቀረውን እናንተ ሙሉበት።
እምዬ ኢትዮጵያ በክብር ለዘለአለም ትኑር።
Filed in: Amharic