>

ቡራዩ አለ የተባለው የሜድሮክ ቴክኖሎጅ ግሩፕ ድብቅ እስር ቤት ጉዳይ እየተጣራ መሆኑ ተሰማ

  • ንብረቶቹ የተገኙት የከተማዋ መስተዳድር ከህዝቡ ባገኘው ጥቆማ መሠረት ባደረገው ፍተሻ እና ምርመራ ነው፡፡

በቡራዩ ከተማ የሜድሮክ ቴክኖሎጅ ግሩፕ አባል በሆነው ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ገፈርሳ ካምፓስ ሁለት ትንንሽ ማለትም አንድ የኬሚካል መርጫ አውሮፕላን እና ሌላ ትንሽ ሄሊኮፕተር መገኘታቸው ተሰማ። ንብረቶቹ የተገኙት የከተማዋ መስተዳድር ከህዝቡ ባገኘው ጥቆማ መሠረት ባደረገው ፍተሻ እና ምርመራ ነው፡፡

መስተዳድሩ ፍተሸውን ያደረገው በከተማዋ ውስጥ ምንነታቸው ያልታወቁ ለኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚውሉ በሚል የተለያዩ ቁሳቁሶች እንዳሉ ህዝቡ ጥርጣሬ ውስጥ በመግባቱ እና ድብቅ እስር ቤት አለ የሚል ተደገጋሚ ጥቆማ መምጣቱን ተከትሎ ነው፡፡ የተባሉትን አውሮፕላንና ሄሊኮፍተር በዩኒቨርሲቲው እንዳገኘ ያረጋገጠው የከተማው መስተዳድር ስለ ኢንዱስትሪ ቅሳቁሶቹም ይሁን ስለ ድብቅ እስር ቤቱ እንዲህ ነው እንዲያም ነው ባይልም ሁሉንም በማጣራትና በመመርመር ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡ 6 አውሮፕላን እና አንድ ትንሽ ሄሊኮተር ያለው ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ የተባለ የአየር መንገድ ድርጅት እንዳለውና ለስ ማመላለሻ እና ለኬሚካል መርጫ እንደሚጠቀምባቸው የገለጸው ሜድሮክ ቴክኖሎጅ ግሩፕ ቡራዩ ላይ የተገኙት ሁለቱ አውሮፕላንና ሄሊኮፍተሮች የድርጅቱ ንብረቶች መሆናቸውንና ለማስተማሪያነት በግቢው ውስጥ እንደተቀመጡ ተናግሯል፡፡

Filed in: Amharic