>

ሚሊዮኖች እንዳይፈናቀሉ፣ደርዘኖቹ ለቁም-እስር የሚያስከፍላቸው መረጃዎች አሉን፤ (ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ

ሚሊዮኖች እንዳይፈናቀሉ፣ ደርዘኖቹ ለቁም-እስር የሚያስከፍላቸው መረጃዎች አሉን፤

(ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ)

  
ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ 
            ዕብራውያን ፲፥፳፪               
 ለስምንተኛ ወራት ጊዜ መሆኑ ነው፤ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቀላል እና ግልፅ በሆነ ቀጥተኛ አነጋገር፤”ከበቀል ነፃ በሆነ መንገድ ያለፉት ሰቆቃዎች አብቅተው፣ ኢትዮጵያን ከመፈራረስ እናድናት ዘንድ በሰላማዊ መንገድ በጋራ እንገንባት”በማለት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሪ ማቅረባቸው።”ጥሪው ሕግን መከተል አለበት ብዬ አላምንም፤ወይም በማያሻማ ቃላት አልቀረበም የሚሉ ሰዎችን አይጋብዝም፤አሊያም ጥሪው ሕገ-ወጥ ነው፣የሚያስብለው መንገድም የለውም፤ እንዳይገርማችሁ!ጥሪው በሕገ-ልቡና የቀረበ የሰብዓዊ መብት ጥሪ ሲሆን፤መንፈሳዊም ነው።
         ይህንን ጥሪ ተቀብለው በቅንነት የተደመሩ አሉ፤የተደመሩ የሚመስሉም(ምሁራንን ጨምሮ)ሆነ በግልፅ የሚቃወሙም ሞልተዋል፤ቁም-ነገሩ “በዜግነት ኢትዮጵያዊነታቸው እነማን ናቸው በሠላም ለትግል የሚንቀሳቀሱት?”የሚለው ነው።በዚህም መሠረት በተጠርጣሪነት ከሰላማዊ ትግል ውጭ የሆነ ግለሠብ፣በምንም ዓይነት ተግባር እንዲሳተፍ አይደረግም፤አይታሰርም ዳሩ ግን በተለየ ሥፍራ አሳርፎ(በቁም እስር)ማየት ግን ይቻላል።
     ለዚህም ነው ሕውሃት የሚ-ጠላው፣በደም ስለተጨማለቀ፣ የግብረ-ሰዶም ሰዎችን መሰባሰቢያ ስለሆነ፣የግፍ-ፈፃሚ አምራችነቱ ገዳይ-ኩባንያነቱ ስለተረጋገጠ እና የተንኮለኛ ሰው-እባቦችን መፈለፊያ ፓርቲ ነኝ ብሎ፣ኢትዮጵያን ለማጥፋት ሃያ ሰባት ዓመታት በደም እየዳከረ የሚገኝ ስለሆነ ነው፤ከዚህ አትለፍ መባል ያለበት።ፈቃደኛ ሆነው በይቅርታ ንስሓ ከታጠቡ ማንም አያሸሻቸውም።እነዚህን ሃቆች የሚክዱ ግን ትውልድ ይተፋባቸዋል፣አሁን በሥልጣን በክተው እንዳየናቸውና ሕዝብ አንድ ቀን እንደሚተፋባቸው ሰዎች ማለት ነው።
          እኛ የሐበሻ ነገዶች፣ተወላጆች እና የዮቅጣን ዘሮች፤ሌሎችም በአበሻ ያሉ ልዩ ልዩ ኢትዮጵያውያን ወገኖች ፣ በደም እና በአጥንታችን ኢትዮጵያን  እየጠበቅን ከጠላቶቻችን አፍ እንዳትገባ በነፃነት እንድትቆይ ያደረግነው በእግዚአብሔር ቸርነትና በአርበኞቻችን መስዋዕትነት ነው ።ይህን የሐቅ ታሪክ ያልተቀበሉ ግለ-ሰቦች ሁሉ፣ የኢትዮጵያን የሕላዌ ምንጭ አይረዱምና ይህን ጦማር በደመ-ነብስ ከማንበብ ሌላ በቀላሉ አይገነዘቡትም።
   ስለሆነም ለዘመናት የተከፈሉት መስዋዕትነት በአርበኞቻችን እንጂ፣ነብሳቸውን በሕይወት ለማትረፍ ሲሉ በፍርሃት ደብቀው፤ሕዝብን ለግድያ አጋልጠው፤የጀግንነት ካባ እንደተከናነቡት የውሸት ጀግኖች አይደለም።እናም አፈር እስከሚሆኑ ድረስ የደም-ፍትፍት የበሉትን የምንትፍ  ጀግኖች ባለታሪኮችን ገድል(ገድለ መዊዕ ይመለከቷል)ሥም ለማግኘት  አይደለም።እነሱንማ ማን እንደሆኑ በጊዜ መስተዋቱ አየናቸው፤ቁልጭ፣ቅልብጭ አድርጎ ጊዜ ደጉ ባደባባይ፣ወርቅ ሳይሆኑ ጭቃ እና አመድ መሆናቸውን በዚሁ ከመቶ ዓመት የተንኮል ዕቅድ ሴራቸው፣ሃያ ሰባት ፐርሰንቱን እንኳ ሳያልፉ በገሃድ አሳየን።
   ኢትዮጵያ የተሻለች አገር እንዳትሆን እና ሕዝቦቿም በድህነት እንዲማቅቁ የሚፈልጉት ከጥንት ጀምሮ የሥጋ ትል ሆነው ያስገደሉን፣የሦስተኛው እጅ አባላት(ሕውሃቶች)ናቸው። ሁሌም ሕውሃቶች የሚ-ፈ-ጠሩት ሁለት የተለያዩ አዳዲስ ሃሳብ ያላቸው ወገኖች በውይይት ለመስማማት ጥረት በሚያደርጉበት ወቅት ሲሆን፣በሦስተኛ አካልነት ራሳቸውን በሠላም ሥም ጠፍጥፈው በድብቅ ጣልቃ እየገቡ የሚያጋጩ ናቸው።በኢትዮጵያ ጣልቃ ጉዳይ በግለሰብ በምሳሌነት አቶ ስብሃት ነጋን ማየት ይቻላል፤እስከዛሬም ድረስ በሌለው ሥልጣን፣ በማያገባው ጉዳይ ሁሉ፤እንዴት የእርጎ-ዝምብ እንደሆነ ተመልከቱ፤ምንም ሥልጣን የለውም፤ ዳሩ-ግን ድሮ አያስፈልግም ተብሎ በቀረው የሰላም-ኮሚቴ ሥም ጭምብል አድርጎ”አይነ-ደረቅ ሌባ ቃጭል ይዞ እንደሚገባ”ጥሩ ማጅራት መቺ መሆኑን እናረጋግጣለን።በረከት ሰምዖን ደግሞ አማራ ነኝ ሲል የነበረው ከቀን-ጅቦች ጋር ተደምሮ ጅብነቱን ሳያውቀው ለማስመስከር ቁርበት አንጥፉልኝ ሲል”በአደባባይ የተዋረደበትን የትግራይ ዩነቨርስቲ ስብሰባ” https://www.youtube.com/watch?v=JK7ccUK1ARU ማየት ብቻ ይበቃል።የሚያሳዝነው እነርሱ ባጠመዱት የአርባ አራት(ታቦታችንን ልብ ይሏል)ዓመታት ተንኮላቸው ዜጎች ሲገደሉ እና ሲጋደሉ አስታራቂ እና ድረሱላቸው ባዮች ሆነው ተመልሰው በመግባት፤ቁስሉን እያባባሱት ዑዑታ ማሰማታቸውን የማያውቅ ኢትዮጵያዊ እንደሌለ አለማወቃቸው ነው።
      በሌላ በኩል ደግሞ በኢትዮጵያ ላይ ያልተፈፀሙ የጥፋት ፈጠራዎች እና አፈ-ታሪኮች አሰራጭተው፤አንዴ በጡት-ቆረጣ፣ሌላ ጊዜ በዘር-ግልበጣ፤ኢትዮጵያን ለማጥፋት፣ደጋግሞ የወረራትን፣ፋሺሽት ጣሊያንን”የምዬ ምንሊክ”ወዳጅ አድርገው ያቀርባሉ።ፈጠራው በትግሬው ምሁር ነኝ ባይ እና በዘመነ-ግልምቢጥ ምሁራን ተብዬዎች በሕዝብ መገናኛ መተረኩ ሳያንስ ሕውሃት የትግራይ ሕዝብ በደህንነት መዋቅር ታፍኖ ዕውነቱን እንዳያውቅ መደረጉ ተጨምሮበት፤አስለቃሹ ነገር የትውልድ በደልና እንደገና ወጣት ትግሬዎችን ለጦርነት ለመማገድ የ”ውጫሌ ውል”ዓይነት በተንኮል ቦይ ለመቅደድ መዘጋጀቱ ነው።እምዬ ምኒሊክ ለዲፕሎማሲ ነበሩ ብለን ብንቀበል እንኳ፣ ከእርሳቸው ሥርዓተ-መንግሥት በፊትስ በትግሬ በር በኩል ሮማውያን ፋሺሽት ጠላቶች፣አርባ ዓመታት አስቆጥረው በመዘጋጀት፣በዘመናችን ደግሞ፣በእጅ አዙር የባንዳዎች የልጅ ልጆችን መልምለው እንደሥጋ-ትል በኮንስትራክሽን ሰበብ፤ፖለቲካዊ ወረራ ሳይሆን፣ኢኮኖሚያዊ ምዝበራ በማድረግ እየገቡ፣ኢትዮጵያን ሲወጓት የነበሩትስ፤በቀዳማዊ ሚኒልክም ነበር ብለን እንቀበል?በተለይም ምንሊክ ወደ አድዋ ከመዝመታቸው በፊትስ አምስት ጊዜ በጣሊያን በድብቅ የተሸነፉትስ የትግሬ ንጉሥ ምን ሊባሉ ይችላል?ዳግማዊ ምኒሊክ “እኔ ሳልመጣ ጦርነት እንዳትገጥም፤አምስት ጊዜ መሸነፍህን ሰምቻለው፤”ብለው ነው፣ከአድዋ ጦርነት በፊት ባሉት ጥቂት ወራትና ሣምንታት መቀሌና አምባላጌ ላይ የተደረጉ ጦርነቶች እንደነበሩ በማውሳት የዘመቱት፡፡ የመቀሌን ከተማ በኢጣሊያዊው ኮሎኔል ጋሊያኖ ከሚመራው አውሮጳዊ ሠራዊት ለማስለቀቅ መስዋዕትነቱ የበዛ በመሆኑ፡-መቀሌ የተለቀቀችው በፈረንጆች ሚሊኒየም BBC (British Broadcasting Corporation)የሚሊኒየሙ ምርጥ ሠብዕና ብሎ ከአህጉር አፍሪቃ ባጫቸው ከጐንደር ኦሮሞ ቤተሠብ በሚወለዱት እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሥልጡን ወታደራዊ መላ ነው፤ታሪኩን ማረጋገጥ ይጠቅማል።
         ዝርዝሩን እዚህ አላወሣውም እንጂ መቀሌ በጣይቱ ልዩ ወታደራዊ ብቃት መያዝዋን መግለፅ ይጠቅማል፡፡ በኋላ ላይ ኮሎኔል ጋሊያኖ በአድዋ ጦርነት ተማርኮ፡- የምንሊክን ፊት ከማይ ግደሉኝ ብሎአል፡፡ለማንኛውም ሰሞኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ የአድዋ ድል የሚከበርበት ሰሞን በመሆኑ ወድተነሳሁበት ርዕስ ልመለስ።እናም ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ፊት ለፊት ሄደው የሮም ገዥውን እና የዘመናት ባለድል ተብሎ ሲፈራ የነበረውን በመግጠም ነበር ፋሺሽት(ድሮም ይባል የነበረው፣በመጥረቢያ ስለሚጠቀም)ጣሊያንን አዋርደው ያሸነፉት።ለማንኛውም ታሪክን በመሰረዝ እና በመደለዝ የአገውን ታሪክ”ኣኮ ሱም’ን፣”አክሱም”ብሎ በመጥራት እንደ ተሰረቀው እና የትግሬ ነው እንደማለት፤ወይም ተራራን የሚያህል የጎንደር ሕዝብን ይዞታ ለመዝረፍ አሥር ዓመታት ሰርቆ እጅ ከፍንጅ ሲያዙ አሳስተውን ነው በማለት መለወጥ ኣይቻልም፤ ሕዝብ እያንዳንዷን ነገር በሚገባ ያውቀዋልና።
     ወደ ተነሳሁበት ርዕሰ ጉዳይ ልመለስና፣ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቀላል እና ግልፅ በሆነ ቀጥተኛ አነጋገር፣ኢትዮጵያ የጦርነት ልሳን ከእንግዲህ አያስፈልጋትም ተብሎ በተነገረባት የሥልጣኔ ጉዞ ምሥረታ ላይ”ያለሕዝብ ውክልና” ጦርነት ለመጫር ለምን አስፈለገ?ያውም በራሳችን ዜጎች ላይ።ላለፉት አርባ አራት ዓመታትም ያለአግባብ እንዴት ጦርነቶች በሕዝቦች መካከል እንደተደረጉ የሚ/በረበሩ/ጣሩ ይሆናሉ፤በአሁኑ ጊዜ ማድረግ ያለብን ግን መቅደም ያለበትን በቅደም ተከተል መፈፀም ብቻ ነው።ስለዚህም የኢትዮጵያን ችግሮች ለመፍታት በእግዚአብሔር በኩል በመንፈሳዊ መንገድ”ኢዮብ ፴፫፥፲፬ እግዚአብሔር በአንድ መንገድ በሌላም ይናገራል፤ሰው ግን አያስተውለውም።”አንዱ ሲሆን፤ዶክተር ዐቢይ አህመድን ሰጥቶናል ብዬ አምናለሁ።በሥጋዊ የትግል ጉዞአችን ደግሞ ጦርነትን ጠልተን ሠላምን መምረጣችን፤መለያየትን አርቀን መወያየትን አቅርበን መፈላለጋችን፤በፆም እና በፀሎት እየታገዘ እግዚአብሔርን በመለመን ክፉ ነገሮችን ሁሉ በማስወገድ በሕሊና ዳኝነት ለመገዛት በዲሞክራሲ ሥም በቅን ልብ ልንቀርብ ልቦናችንን ከፍተን ጥረት በማድረግ ላይ እንገኛለን፤ዕብራውያን ፲፥፳፪ ‘ን  ይመልከቱ።
            በአንፃሩ ደግሞ እጃቸው የግፍ ደም ያጨማለቃቸው ንስሃ ከመግባትና በአደባባይ የሕዝብ ይቅርታን ከመሻት ይልቅ፤በበደል ላይ ሌላ የግፍ በደል ለመጨመር፤ሲመቻቸው በግልፅ ሲብስ ደግሞ በሕቡዕ መራራ ሴራዎችን ሲፈፅሙ በትክክል የሚታዩ አሉ።በእርግጥ እንዲህ ዓይነቱን ፈተና ለመወጣት በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ የምናውቃቸውን ተመክሮ፣ከባለሙያም ሆነ ከዕድሜ ጠገብ መልካም አዛውንቶች ምክር መካፈሉ ብልህ ትውልድ ያሰኛል።እኔም የመፅሃፍ ቅዱሱን ሙሴ ታሪክ በአራያነት፤”መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ ፩፥፯ ነገር ግን ጽና፥ እጅግ በርታ፤ ባሪያዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ ሁሉ ጠብቅ፥ አድርገውም፤ በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል።”የሚለውን መንፈሳዊ ምክር ብመርጠውም በቀጥታ ድንጋዩን፣ድንጋይ፤ሌባውን ሌባ አለማለታችንና፤”ማንቆላጰላጠሳችንን” ለዘረፈን ሰው ክብር መስጠታችንን የምናውቅ ጥቂቶች ብቻ መሆናችንን በሚገባ በተለያዩ መንገዶች ተረድቻለሁ።
        ለምን?ቢባል፤ ከክፉ ሕሊና ለመንጻት እና ልባችንን ተረጭተን ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልቦና ለመቅረብ ስንል።አሁንም እንዴት ቢባል?በተስፋችን ውስጥ የቀረችን”አንድ የህሊና ዳኝነት”ብቻ ስለሆነ።ይሁንና ሚሊዮኖች እንዳይፈናቀሉ፣ደርዘኖቹ ለቁም-እስር የሚያስከፍላቸው መረጃዎች አሉን፤በሐይማኖት እስላም ወይም ክርስቲያን፤አሊያም የዚያ ወይም የዚህ ስለሆንን ሳይሆን በሰብዓዊነት ብቻ፤እያንዳንዳችን በዜግነታችን ዝም ማለት ሳይሆን ግዴታችንን የመወጣት ወሳኝ ወቅቱ፥አሁን ነው፤እናም ይህቺንስ ለማስፈፀምም ሰበቦች ያስፈልጉናል?
        ያለ-ይሉኝታ ከራሳችን ጀምሮ ለትውልድ ስንል በኢትዮጵያ ጉዳይ ባይተዋር አንሁን፤እኛ ካልቀረብን ግን ርኩሶቹ እና የሠይጣን ዓላማዎች(ፍናፍንት፣ማጋደል፣ክህደት…)ያሏቸው ያረክሱናል፥ወደአልተፈለገ አቅጣጫ፤እንጦርጦስ ሊወስዱን መሆኑን ማወቁ አይደለም ቁም-ነገሩ ቀድሞ መፍትሄ ማግኘቱ ላይ ነው።ከደርዘኖቹም ሌጌዎኖች፣አባይ ፀሐዬ፣ስብሃት ነጋ እና በረከት ስምዖን (የማርቆስ ወንጌል ፭፥፱ ስምህ ማን ነው? ብሎ ጠየቀው።ብዙዎች ነንና ስሜ ሌጌዎን ነው አለው፥)ቀንደኛዎቹ ጉልቻዎቹ ናቸውና እንዳይቀደሙ።
     ጠቅላይ ሚኒስቴራችን ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያን ቀንደኛ ጠላቶች ለማስወገድ ሌላ ምን ቀረን?እባክዎት የሚሰዉ ሰዎች የሉንምና ወንጀለኞች ያልሆኑትን ተጠርጣሪዎች”ሆድ ሲያውቅ፣ዶሮማታ ነውና”በቅን ልብ እንቅረብ እና እስከሚጣራ”በቁም እስር”ማቆየት ሕጋዊነት ስለአለው፦ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማ እንደመከሩት  በመንግሥት አርቆ አሳቢነት ለሕዝብ አለመፈናቀል ሲባል፣እንደ እርስዎ የጥበቃ ዝግጅት የማንንም መብት አይነኩምና፣ለሁሉም ማዕበሉን ቢያንስ ፀጥ ማድረጉ “በቅን ልብ” ይመረጣል።እናም”የቁም-እስር”ሕዝቡን እንዳይፈናቀል ከረዳ ለምን በሥልጣንዎ ከሦስቱ ተጠርጣሪዎች ጋር በቁም እስር ቤት ውስጥ አይወያዩም? ? ?….አራታችሁም ኢህአድግ መሆናችሁን እናውቃለንና።
Filed in: Amharic