ወዲ ሻምበል ዘ ብሔረ ኢትዮጵያ
* የትግራይ ህዝብ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ “መንጋ ተብሎ ተሰድቧል” እያሉ ለሚያለቃቅሱ የተፃፈ :-
“መንጋ የተባለው ለህዝብ ሳይሆን በመንጋ ፍትህ ጥየቃ ለሰው ህይወት አደጋ ለሆኑ ብዱኖች ሌቦች አንሰጥም የሚሉ መንጋዎችም ይመለከታል እንጂ ለአንድ ብሄር አልያም ለአንድ ህዝብ መንጋ አልተባለም”
“የቀን ጅብ የተባለውም ለህዝብ ሳይሆን በቀን የሃገርን ሀብት የዘረፈ ያዘረፈ የሰውልጅ ሂወት ያመሳቀለ የገረፈ ለአሸባሪዎች ካንሰሮችን ተባለ እንጂ ለህዝብ አልያም ለአንድ ብሄር አልተባለም”
“ይሰማል ማነህ ጠማማ ለራስህ ህልውና ብለህ ነገሮች አታጣምም ጠማማ”ይህንን ያልክበትም ምክንያትም አውቀዋለሁኝ” የቀንጅ ጅብ ማለት ለትግራይ ህዝብ ነው ብለህ ማላከክህም ትክክል ነህ” ምክንያቱም ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድነው ብለሃል”
ህወሓት የቀን ጅብ ነው ባይባልም አባባሉ ለእኔ ነው ስላለች” የአዋሳው ንግግር ወደ መቐለ አምጥታ የራሴ ነው ብላዋለች” እንደ አባባሉ ህወሓት የቀን ጅብ ነችና የትግራይ ህዝብም የቀን ጅብ ነው” ስለዚህ አንተ ልክ ነህ አልተሳሳትክም”እኔ ግን አይደለም ቀድመን የተለየን አለን ህወሓትና የትግራይ ህዝብ የተለያዩ ናቸው ብለን ቀድመን ህዝብና ፓርት ይለዩ ወንጀል ነው ብለን በመቐለ አደባባይ ሮማናት ሰልፍ ወጥተናል” ባአንተ አባባል ግን ልክ ነህ ህወሓት ሲሰደብ የትግራይ ህዝብ ተሰደበ ብለህ እሪ ስትል ትክክል ነህ” ምክንያቱም የቀን ጅቦች ማህበርተኛ እንደሆንክ ያሳውቅባሃል” እናማ ሰደበኝ በል እንጂ ለትግራይ ህዝብ ተሳደበ አትበል እላሃለሁኝ” አንድ አይደለንሟ” ባንተ ተንኮል ክፋት አባባል መጣፈጫ ደግሞ መንጋ ይቁም ለተባለው ለህዝብ ተሳደበ አልክ ይህንንም አንተ መደበቅያ ስታፈላልግ እችን አገኘህ እንጂ መንጋ ተብሎ የተሰደበ ህዝብ ብሄር የለም።
በመንጋ ፍትህ ፍለጋ አደገኛ ነው ይቁም ነው የተባለው። የብዙሃን መብት ለማግኘት የጥቂቶች መብት አደጋ ላይ መጣል የለብንም ስርአት ይደረግበት ነው የተባለው። ይህንንም ለአማራ ለኦሮሞ ህዝብ እንደ ስድብ አድርገህ የትግራይ ህዝብ የቀን ጅብ ተብያለሁኝ ብሎ በ አብይ አሕመድ እንዲያምፅ። የኦሮሞ እና የአማራ ህዝብ መንጋ ተብያለሁኝ ብሎ በ አብይ አሕመድ እንድያምፅ ማድረግ ነው። ይህንን ደግሞ የትግራይ የአማራ የኦሮሞ ህዝብ ። የቀን ጅቦች ካንሰሮች የመደበቅያ ዋሻ ለማድረግ የሚደረግ የክፋት ሴራ ሃሳብ ስለ ሆነ። አይሳካም እንዳህ እናከሽፈዋለን!! አብይ አሕመድ ያደረገልን ህወሓት በ27 አመት አላደረገልንም። ተወደደም ተጠላም የትግራይ ህዝብ በአብይ ስልጣን ተጠቃሚ እንጂ ተጎጂ አይደለም። በትንሹ የመቐለ ዋሃ በህወሓት ዘመን በሃይለማርያም ዘመን በመለስ ዘመን ያልተሰራ አሁን እያለቀ ነው በስምንት ወሩ ነው። የትግራይ ህዝብ ከአብይ አሕመድ በላይ መሪ አላገኘም በህወሓት ኢህወዴግ ዘመን። ይህንን መካድ አይቻልም በጥቃቅን ንግግር የአብይ አሕመድ ስራዎች አፈር ማብላት ማድረግ አይቻልም። የህወሓት ፕሮቦጋንዳ ቀነስ አድርገን የህወሓት ውድቀት ለህወሓት አሸክመን የሃይለማርያም ውድቀት ለሃይለማርያም አሸክመን ዶ/ር አብይ አሕመድ ነፃ እናውጣው ለሰራው ስራ ምስጋና ይገበዋል”