>
9:37 pm - Tuesday July 5, 2022

ኤርትራ፤ ህወሃት እና ምስራቅ አፍሪቃ (ሚኪ አምሀራ)

ኤርትራ፤ ህወሃት እና ምስራቅ አፍሪቃ
ሚኪ አምሀራ
ሰሞኑን ኢሳያስ አፈወርቂ በድንገት እና ባልታሰበ ሁኔታ የተወሰኑ መንገዶችን እንዲዘጉ ወይም ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ማዘዙ ምናልባትም ህወሃት ያረገዉ ነገር ያለ ይመስላል፡፡ ህወሃት ህልሙ ኤርትራን እሱ የሚያዛት ፑፔት ሀገር ማድረግ ነዉ፡፡ ነገር ግን ኢሳያስ በህይወት እያ ይሄን ማድረግ እንደማይችሉ ያዉቃሉ፡፡ ከኢትዮጵያ የመሃል ሀገር ፖለቲካ መገለል እንዲሁም በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ጥላቻ በነሱላይ ማሳደር ህወሃት ጭንቅ ላይ እንዲወድቅ አድርጎታል፡፡ ቀስ በቀስ ከራሱ ከትግራይ የሚያገኘዉን ድጋፍ (declining legitimacy) ሊሸረሸርበት እንደሚችልም ገብቶታል፡፡ በመሆኑም ህወሃት ለትግራይ ህዝብ አሳማኝ የሚያደርግለት external ጠላት መፍጠር አለበት፡፡ ለዚህም አማራጩ ሁለት ነዉ አንድ ከአማራ ጋር ጦርነት ላይ ነን ማለት፡፡ ወይም ደግሞ ኢሳያስ ትግራይን ሊያጠፋ ነዉ እና እናስወግደዋለን የሚል ጀብደኝነት ትርክት መፍጠር ነዉ፡፡
ከኤርትራ የሚወጡት መረጃወች እንደሚያሳዩት ሰሞኑን ኢሳያስ አፈወርቂ ሶማሌን እየጎበኘ በነበረበት ወቅት የተወሰኑ የኤርትራ የጦር መኮነኖች የኢሳያስን አገዛዝ ለማስወገድ ሲዶልቱ ተደርሶባቸዉ በብዛት ተይዘዋል፡፡ ይሄን መረጃ ያጋለጠዉ የቀድሞዉ የኤርትራ መካላከያ ሚኒስቴር የአሁኑ የማእድን ሚኒስቴር ጄኔራል ስብሃት ኤፍሬም የአቦይ ስብሃት አማች  ነዉ፡፡ ኢሳያስ ጄኔራሉን ገለል አድርገዋቸዉ ነበር፡፡ ጄኔራሉም በፍራቻ ሊሆን ያችላል ታማኝነታቸዉን ለፕሬዝደንቱ ለማሳየት ከአንዳንድ የህወሃት ሰወች ጋር የሚለዋወጡትን መረጃ ለፕሬዝደንቱ ያቀርቡ ነበር ይባላል፡፡ ምናልባትም የመኮነኖች ሙከራ የታወቀዉ ሰዉየዉ ከህወሃቶች ጋር ባለዉ ሊንክ ነዉ ይባላል፡፡ጄኔራሉንም የመግደል ሙከራ ያደረገበት ግለሰብ የእነዚህን መኮነኖች መታሰር ለመበቀል ነዉ ተብሏል፡፡ ነገር ግን ለመግደል ሙከራ አድርጓል የተባለዉ ግለሰብ ኢትዮጵ ዉስጥ ለተወሰነ ጊዜ የቆየ መሆኑን መረጃወች ያሳያሉ፡፡ ለማንኛዉም ህወሃት የኢትዮጵያን ፖለቲካ እንደገና influence ለማድረግ ከሚፈልጋቸዉ መስመሮች አንዷ ኤርትራ ናት፡፡ መጀመሪያ ኢሳያስ ቂሙን አንዲተዉ እና ከትግራይ ብሎም ከህወሃት ጋር እንዲታረቅ ቢጀበጅቡም አልተሳካም፡፡ አሁን የያዙት አካሄድ እሱን አስወግዶ የራሳቸዉን ፑፔት መንግስት ተክሎ ከዚህ መንግስት ጋር በመተባበር የንግድ መስመሩን እና ወደቦችን በመቆጣጠር የነበረኝ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖ ይመለሳል ብሎ ያስባል፡፡
በነገራችን ላይ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ ከፍተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ወደ ሌሎች ሀገሮች የመዛመቱ ጉዳይ አይቀሬ ነዉ፡፡ የዶ/ር አብይ መንግስት በተለይም ለኤርትራ ጥሩም መጥፎም ነገር ነዉ ይዞ የመጣዉ፡፡ ጥሩዉ ነገር ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም እንድትፈጥር ማድረጉ እና በከፍተኛ ሁኔታ እየተሸረሸረ የነበረዉን የኢሳያስን authoritarian government legitimacy ጠግኖለታል፡፡ መጥፎዉ ነገር ግን Huntington የተባለዉ ጸሃፊ The third wave በሚለዉ መጽሃፉ እንዳሰፈረዉ፡፡ የአንድ ሀገር የመንግስት ለዉጥ ባካባቢዉ ላሉ ሀገሮች እንደሞዴል ሊያገለግል ይችላል ይላል፡፡ ወይም snowballing or demonstration effect የሚለዉ ነዉ፡፡ ኤርትራዉያን ከኢትዮጵያ በኩል በሚያዩት እና በሚሰሙት ነገር ተበረታተዉ መንግስት ለመቀየር መጣራቸዉ አይቀርም፡፡ በዚህ demonstration effect ምክንያት ሱዳን (already ህዝቡ በመንግስት ማመጽ ጀምሯል)፤ ጅቡቲ ፤ ኡጋንዳ እና ሩዋንዳ የሚያሰጋቸዉ አገሮች ናቸዉ፡፡ ጅቡቲ፤ ሱዳን እና ኤርትሪያ ጎረቤት አገር በመሆናቸዉ በኢትዮጵያ ያለዉ የፖለቲካ ለዉጥ ወላፈኑ በቀላሉ ይደርሳል፡፡ ሩዋንዳ ደግሞ ወያኔ እንደ መጽሃፍ ቅዱስ የሚደጋግመዉን የ developmental state model አራማጅ መሆኗ እና ይህ ሞዴል በኢትዮጵያ ዉስጥ ችግር ዉስጥ መግባቱ በሩዋንዳ ህዝብም ዘንድ ተመሳሳይ ጥያቄ ሊያስነሳ ይችላል፡፡
Filed in: Amharic