>

ደረጀ ደምሤ ቡልቶ.... (ከሻለቃ ላቀው መንግስቴ)

ደረጀ ደምሤ ቡልቶ….

ከሻለቃ ላቀው መንግስቴ
 የጀነራል ደምሤ ቡልቶ ልጅ በ1981 ሥለነበረው የጀነራሎቹ አብዮት ክሽፈትና ሥለነበረው የኤርትራ ውጊያ ውድቀት የሚሠማቸውን በቃለ መጠይቁ ዘርዘር ያለ መልሥ ሠጥተዋል፡፡በእርግጥ የማይካደው ሐቅ በወታደራዊ ሣይንሥ እጅግ የበሠሉ ፡በውጭ የወታደራዊ ሥልጠና ዶክትሪን ላይ በውጤታቸው አንቱ የተባሉ ጀነራሎቻችንን ያጣንበት ከነበረው መንግሥት ጋር የቡድን ፀብ የመሠለ፡ድርጅታዊና የፖለቲካ ተቋም ያልነበረው በራሥ ከረባት አንገትን አንቆ የመሞት ያህል ህልፈትን የማፋጠንና፡መንግሥቱ ኃይለማርያምን ምነው ዝም አልከን አይነት የቀልድ አቢዮት የተሞከረበት ነው፡፡ሌላው ቀርቶ በራሣቸው በጀነራሎቹ መካከል በአቋም የመዋሀድ፡ሚሥጥርን አሣልፎ ላለመሥጠት እንኳን በቃል ኪዳን ያልተሣሠረ፡አንዳንዶቹ ሚሥቶቻቸው ጭምር ከነ ተሥፋዬ ወ/ሥላሤ ደህንነቱና ከሻእቢያ ጋር በግልፅ ግንኙነት የነበራቸው /ቂጥ ገልቦ ራሥ ክንብንብ/አይነት ከእብደት ያልተናነሠ እነኛን ከመሠሉ ሙያ ጠገብ ጀነራሎች የማይጠገብ ውሎ ያላመሸ አብዮት ተፈፅሟል፡፡ባይሣካ እንኳን ቀጣዪ ሥራ ምን መሆን አለበት የሚል ሥንገባ ከውጭ ዝጉብን አይነት ትግል ከነኝህ ትላልቅ ጀነራሎች ጭንቅላት መታቀዱ ያሣዝናል፡፡
መንግሥትን ለመገልበጥ ሢታሠብ በሚያመጡት ለውጥ ላይ ሊኖር የሚገባውን የትግል ሥልት የነደፈ ታክቲክና ሥትራቴጂ፡የአደረጃጀት ሕግ ፡ከጎናቸው ሊያሠልፍ የሚችል ከሠራዊቱ የተለያየ እርከን ከሢቢሉም በተመሣሣይ የተዋቀረ ድርጅት ሣይፈጠር በደመ ነፍሥ መፈንቅለ መንግሥት መሞከራቸው አሣዛኝ ነበር፡፡
ከሠራዊቱም ጋር የነበራቸው ቅርርብ ጥሩ ያልነበረና እንደውም በተገላቢጦሽ መንግሥቱ ውጊያውን ቶሎ ለማጠናቀቅ ሢጥር ውጊያው ቶሎ እንዳይፈፀም ከሻቢያና ከህወሐት ውሥጥ ዉሥጡን እየተገናኙ የሚያሥመቱን እነሡ ናቸው የሚል አቋም ነበረው፡፡ምክንያቱም ለሠራዊቱ እንደ ቅርብ አዛዥ ሆነው ችግሩን የማይፈቱ፡ጥፋት እንኳን ሢታይ እንደ ጥፋቱ ደረጃ ሕጋዊ ምዘና ሠጥቶ ከመዳኘት ይልቅ ፍለጠው ቁረጠው አይነት እርምጃ ሢወሠድ የነበረው መንግሥቱ እታች ወርዶ የሚፈፅመው አልነበረም፡፡
ከኢሠፓ ማእከላዊ ኮሚቴ ጀምሮ እጅግ የገዘፈ ሥልጣን ነበራቸው፡፡ይመረጥ የነበረው መንገድ በወታደራዊ ከፍተኛ ሥታፍ ኤታማዦሩንና ከፍተኛ የጦር መሪዎችን በመያዝ መንግሥቱ ሀ/ማሪያምን ተሠብሥቦ ሥራን እሥከማቆም አሥገዳጅ ሁኔታ ፈጥሮ እጅ ጥምዘዛ ማካሄድ ይቻል ነበር፡፡የመንግሥቱ ኃ/ማሪያምን ሥልጣን ለማዳከም ጦርነቱን አበላሹ እንጂ አልመሩትም፡፡ሠውየው እርምጃ ከወሠዱ በሁዋላ እንዳለው የተመደቡት ጀነራል መኮንኖች በተበላሽ ውጊያ ውሥጥ ተዘፍቀው የቻሉትን ጥረው ለሐገር መሥዋእትነት ከፍለዋል፡፡ሌላውን በመናቅ ያውቃሉ ከተባሉ ጀነራሎቻችን የተፈፀመው ድርጊት ያሣፍር እንደሆን እንጂ የሚያኮራ አይመሥለኝም፡፡የአዲሥ አበባውማ እዚያው እርሥ በርሥ በመገዳደል የተጀመረ ሢሆን ቅድሚያ ከደህንነት ሚኒሥትሩ ጀምሮ የልዩ ጥበቃ ብርጌድ አዛዡን፡የማእከላዊ እዝ አዛዥን የተለያዩ ሢቢል ሚንሥትሮችን፡የብዙሀን መገናኛ አውታሮችን ሣይያዝ የአመፁ መሪዎች የሥራ ክፍፍል እንኳን ሣይኖር ልናጣቸው የማይገባን እንኳን ለኢትዮጵያ ለአፍሪካና ለአለም እጅግ የሚጠቅሙ የጦር መሪዎቻችንን አሣጥቶናል፡፡የሚደረጉ ሚሥጥራዊ ሥብሠባዎች ሁሉ ለደህንነት ሚኒሥትሩ ከሥብሠባ በሁዋላ በአንዳንዶቹ ጀነራል የትዳር አጋሮች ይደርሡ እንደነበር በሁዋላ ተደርሦበታል፡፡የጓደኝነት ሥራ ሊሆን አይሞከርም መንግሥት ግልበጣ፡፡፡፡፡፡
Filed in: Amharic