>

አና ጎሜዝ እንኳ ስለጆሴፍ ጎብልስነቱ የመሰከሩለትን ሰው በሀብት ብክነት መክሰስ መራር ቀልድ ነው!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

አና ጎሜዝ እንኳ ስለጆሴፍ ጎብልስነቱ የመሰከሩለትን ሰው በሀብት ብክነት መክሰስ መራር ቀልድ ነው!!!
አቻምየለህ ታምሩ
አና ጎሜዝ ከብአዴኖች በላይ በረከት ሰምዖን  ስለፈጸመው  የዘር ማጥፋትና በሰብዓዊ ፍጡር ላይ ክብረ ወሰን ስለተቀዳጀበት ወንጀል ትቆረቆራለች። ብአዴኖች የራሳቸውም መገለጫ በሆነው  የሀብት ብክነት ተጠያቂ ልናደርገው ነው ያሉትን በረከተ ስምዖንን  ቢያንስ እሷ በጆሴፍ ጎብልስነቱ ባካሄደው የዘር ማጥፋትና በሰብዓዊ ፍጡር ላይ  በፈጸመው ወንጀል  የተሰቃዩ ሰለባዎች በመያዙ  ሀሴት እንደሚያደርጉ ተናግራለች።
የጌቶቹ ጉዳይ አስመጻሚ እንጂ የአማራ ባለጉዳይ ያልሆነው ብአዴን ግን ለ27 የፋሽስት ወያኔ የአፓርታይድ አገዛዝ ዓመታት ሙሉ  በአማራ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፍት በዋና አዛዥነት ሲመራ የኖረውንና ለሚሊዮን አማሮች መከራና ስቃይ፤ ለበርካታ ሺህ የአማራ ተስፋዎች  ደብዛቸው መጥፋት፣ ባጠቃላይ ተነግረው   በማያልቁ  በአማራ ላይ በተፈጸሙ ግፎችና በሰው ዘር ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች ክብረ ወሰን የተቀዳጀውን አለማቀፍ ወንጀለኛ  ጥፋት አቃሎ  የብክነት ማዕከል በሆነችዋ ኢትዮጵያ ከወንጀል በማይቆጠርና እሱንም እጅግ ደስተኛ በሚያደርግ የሀብት ብክነት ወንጀል  እንደጠረጠረው ነግሮናል። ይህ በንጹሀን ደም ላይ የተቀለደ ምርር ቀልድ ነው
Filed in: Amharic