>

ስማኝማ አዴፓ.....!!!!!!!!! ሌላም ነገር አለ! (ቹቹ አለባቸው)

ስማኝማ አዴፓ…..!!!!!!!!! ሌላም ነገር አለ!
ቹቹ አለባቸው
በረከት ሥምኦንን  በተመለከተ  መጣራት ያለበት ተጨማሪ የሙስና ጉዳይ –
* ጎንደርን ስጋዋን ጨርሶ አይንህን የጋጣት ማን ሆነና በረከት አይደለምን!!

 

ውድ አዴፓ እንደጉርና ተገፍተህ ተገፍተህ፤ ዛሬ ጥሩ ጅምር ሊባል የሚችል እርምጃ ወስደሀል፡፡ በርግጥ እርምጃውን ከብአዴን-አዴፓ ቤት አንጻር ስናየው እንጅ፤ያን ያክል የሚያስፎክር አይደለም፡፡ ስለሆነም  ለምን ዘገየ ልንል ካልሆነ በስተቀር ብዙም የሚጋነን ነገር አይደለም፡፡ ቢሆንም ግን በግሌ ጅምሩን አደንቃለሁ፡፡
ነገሩ ወዲህ ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ሰዎች የሚከሰሱት እንዴትና በምን ወንጀል ነው? በተራ ገንዘብ ማባከን? ከጥረት ኮርፖሬት ጋር በተያያዘ ጉዳይ ብቻ? ነው ወይስ ሌላም ነገር ይኖር ይሆን? ግለሰቦቹ  ከጥረት ኮርፖሬት ጋር በተያያዘ በሚጠረጠሩበት የገንዘብ ብክነት መከሰሳቸውን እደግፋለሁ፡፡ ውጤቱን ደግሞ አብረን እናየዋለን፡፡
ነገር ግን አዴፓ ዛሬም ጀሮ ካገኘህ፤የነዚህ ግለሰቦች ክስ ፤አሁን የተጀመረው የገንዘብ ብክነት እንዳለ ሁኖ፤ሌላ አንድ መሰረታዊ ክስም ሊጨመርላቸው ይገባል፡፡ ይሄውም የ”ፖለቲካዊ ሙስና” (Political Corruption).  ለመሆኑ “ፖለቲካዊ ሙስና” (Political Corruption) ማለት ምን ማለት ነው? WIKIPEDEA”ፖለቲካዊ ሙስና”ን (Political Corruption)  እንዲህ ተርጉሞታል፡
Political corruption is the use of powers by government officials or their network contacts for illegitimate private gain. An illegal act by an officeholder constitutes political corruption only if the act is directly related to their official duties, is done under color of law or involves trading in influence.
ስለዚህ የዛሬዎቹ ሰዎችም ሆነ፤ለወደፊቱ የሚጠየቁ አንዳንድ የአዴፓ ወፍራራም ባለስልጣናት ካሉ፤በገንዘብ ማባከን መጠየቁ እንዳለ ሁኖ ይህ አይነት ወንጀልም አብሮ መደረብ አለበት፡፡ ይሄንን የምለው ድርጅቱ ውስጥ የሚታየው ዋነኛው የሙስና መገለጫ፤ይሄው ፖለቲካዊ ሙስና ነው ብየ ስለማምን ነው፡፡ ተመልከቱ ከላይ የተጠቀሰውን ትርጉም በደንብ አጢኑና፤ከዚህ አይነት ወንጀል ነጻ ነው የምትሉትን የአዴፓ ነባር አመራር ለዩልኝ፡፡ ይሄ ማለት ሁሉም የዚህ ችግር ሰለባ ነው ለማለት አይደለም፤ግን- ግን አብዛኛው በዚህ ችግር የተለከፈ መሆኑን ለመግለጽ እንጅ፡፡
አሁን ጥያቄው እነዚህን ሰዎች በዚህ ወንጀል ለመጠየቅ የሚያስችል፤ህጋዊ ማቅቀፍ አለን ወይ? የሚለው ጥያቄ ነው፡፡ እኔ አይጠፋም ባይ ነኝ፡፡ የህግ ባለሙያዎች ህጎቹን ፈልጉ፤ በተለይም  ከጉዳዩ ጋር ተቀራራቢነት ያላቸውንና አገራችን የፈረመቻቸውን አለማቀፍ ህጎች/ስምመነቶች ፈላልጓቸው፡፡ ህጎቹ አይጠፉም፤ችግሩ አዴፓ ለዚህ ዝግጁ ነው ወይ? የሚለው ጉዳይ ነው፡፡
ለሁሉም ባለፉት 27/28 አመታ፤አማራን መቀመቅ እንዲለብስና፤አመራር እንዳያወጣ፤አንገቱን ደፍቶ እንዲኖር፤ ርስቱን እንዲነጠቅ ፤ወዘተ… በማድረግ በኩል፤ ብአዴን- አዴፓ ውስጥ የበረከትን ያክል ወንጀለኛ ሌላ  ተጠያቂ ስለመኖሩ እጅጉን እጠራጠራለሁ፡፡ በርግጥ አንድ ሰውም አለ፡፡ የታደሰ ነገርም ያው ታደሰ ነው፡፡ ይሄን ግለሰብ ካወቅኩበት ጊዜ ጀምሮ(1983/84) ትምክህትና የአማራ ብሄር ጨቋኝነትን በማቀንቀን የሚስተካከለው አልነበረም፡፡ እንዴውም በ2008 ዓ.ም፤ የአማራ ብሄር እንደብሄር” ጨቋኝ” ነው የሚል ሃሳብ አንስቶ ፤በብአዴን ጽ/ቤት አዳራሽ ውስጥ ከዶ/ር አምባቸው ጋር የነበረውን መፋጠጥ እናስተውሳለን፡፡ በዚህ ወቅት አለምነው መኮንንም የአምባቸውን ሃሳብ ደግፎት ነበር፡፡ ታደሰ ግን አይሰማም፤ ይሄን አማራን እንደ ብሄር  “ጨቋኝ” ነው የሚል አጀንዳ፤በድርጅት ደረጃ ለወደፊቱ ፕሮግራም ተይዞለት በስፋት ልንወያይበትና አቋም ልንወስድበት እንደሚገባ ፤ለጊዜው ግን እንዳይነሳ የሚል ስምመነት ተደርሶ ነበር፡፡ ነገር ግን መቸም አንዴ የወረፈህ ነገር አይለቅምና፤ታደሰ ይሄንን ነጥብ በ2008 ዓ.ም የታህድሶ መድረክ ላይ ደገመው፡፡ ያኔ አለምነው መኮንን ታደሰን ውቃቢውን አራቀው፡፡ ብቻ ምን ለማለት ነው፤ግለሰቦቹ እንደ ወደል ጅንግላ ተጭነውን ነው የከረሙ ለማለት ነው፡፡ ስለሆነም በነዚህ ሰዎች ላይ የሚቀርብ ክስ እነዚህን ሌሎች መሰል ጉዳዮችንም ባካተት መልኩ መሆን አለበት፡፡ አዴፓም ወይ ባልጀመርከው እንጅ፤አንዴ ከጀመርከው በኃላ ፤ሰበብ መፍጠር የለብህም፡፡ ይሄን ካላደረግክ ደግሞ እንደለመድከው እንደ ጉርና እንገፋሀለን፡፡
————–//////////————-
በረከት ሥምኦንን  በተመለከተ  መጣራት ያለበት ተጨማሪ የሙስና ጉዳይ፡-
በ2003/2004 ዓ.ም ጎንደር በተዘረፈችበት ወቅት፤ጉዳዩን በደንብ የሚያውቁ ምስክሮቸ የሚከተሉት ናቸው፡፡ የአማራ ህዝብ ይሄን መረጃ ወስዶ እነዚህን ሰዎች ቢያንስ ጎንደር ላይ የነበረውን ዝርፍያ  እንዲመሰክሩ ማስገደድ አለበት፡፡ ለሁሉም  ጎንደር ስትዘረፍ በተገቢው የሚያውቁና መረጃ ያላቸው ዋና ዋና ምስክሮቸ የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. አቶ አያሌው ጎበዜ- በወቅቱ ፕሬዝዳንት፤
2. አቶ ገዱ አንዳርጋቸው( በወቅቱ ም/ፕሬዝዳንት)፤
3. ብናልፍ አንዱ አለም( በወቅቱ የብአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ የነበረ)፤
4. አቶ አህመድ አብተው( በወቅቱ የከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ የነበረና ጉዳዩን ከማንም በላይ የሚያውቅ)፤
5. ዶ/ር ደመቀ አጥላው (በወቅቱ የብአዴን የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የነበረ፡፡ በነገራችን ላይ ዶ/ር ደመቀ በወቅቱ ያደረግነውን ትግል በመደገፍ ለተጫወትከው እውነተኛ ትግል ምስጋናየ ይድረስህ)፡፡ የአማራ ወጣቶችም ይሄንን ሰውየ እወቁት( ሽዋ ነፍጠኛ መሰለኝ)፡፡
6. ደሳለኝ አስራደ( በወቅቱ ጎንደር ከተማ ብአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ የነበረና፤ ከእኔ ጋር በትሯን አብሮ የቀመሰ፤
7. አምሳሉ ደረጀ- በወቅቱ የጎንደር መዘጋጃ ቤት ኃላፊ የነበረ፤
8. ብርሀን ኃይሉ (በወቅቱ የፍትህ ሚኒስቴር የነበረና፤የጎንደርን ጉዳይ እንዲያጣራ የተላከው ቡድን አባል)፤
9. ተፈራ ደርበው( በወቅቱ የግብርና ሚኒስትር መሰለኝ፤የአጣሪ ቡድኑ አባል)፡፡
10. እርዚቅ ኢሳ፤ድርጅት ጽ/ቤት
11. አወቀ አስሬ፤ ድርጅት ጽ/ቤትወዘተ….
ካስፈለገ ሌሎቹም አሉ፡፡ ግን ቅድምያ እነዚህ ይናገሩ፡፡ በተለይም ገዱና ብናልፍ ተናገሩ፡፡ ሁለታችሁ እኔንና አሁን አሜሪካ ያለውን ወዳጀ ከጎንደር አስመጣታችሁ ለማስታረቅ ጥር ባደረጋችሁበት፤ ያኔ በድፍረትና በሙሉ ልብነት የተናገርኳችሁን ነገር መስክሯት፡፡ምን ነበር ያለልኳችሁ? እኔ ሰው የለኝም፤ በኔ ላይ ስለሚሳ ነገር ሰው የሚላችሁን ብቻ እየሰማችሁ እንዳትቀጩኝ! አላልኩም፤በተለይም ብናልፍ ምን ትላህ? ሁለታችን ታርቀን እንድንመለስ ስትጠይቁን የኔ መልስ ምን ነበር? ሁለታችን ታርቀን አብረን ልንሰራ አንችልም፤ ስለሆነም እኔ ከሀላፊነት መነሳት አለብኝ፤ያ ወዳጀ ግን ወንጀል ስለሰራ በህግ መጠየቅ አለበት ብየ አልሞገትኳችሁም? ዋሸሁ? ያኔ ወዳጀ ገዱ ምን ነበር መልስህ? በወንጀል የመጠየቁን ጉዳይ ቀስ ብለን እናየዋለን፤ስህተት የሰራ ሰው ሁሉ በህግ ይጠየቃል ማለት አይደለም ነበር ያልከኝ፡፡ ለማስታወስ  ያክል ብቻ ነው፡፡ መጨረሻ ላይ ካልተስማማችሁማ፤ ሁለታችሁም ከስልጣን ተነሱ አላችሁን ተቀበልነው፤ ይሄን ውሳኔ ብናልፍ  ጎንደር መጥቶ አስፈጸመው፡፡
እንዲሁም ተፈራ ደርበውና ብርሀን ሀይሉ፤በነበረከት ተልካችሁ ጎንደር ድረስ መጥታችሁ፤አጣርታችሁ ያገኛችሁትን ነገር ለህዝባችን ተናገሩ፤እምቢ ካላችሁ የራሳችሁ ጉዳይ፡፡
መጨረሻ ላይ፤እኔም ተባርሬ ሁለተኛ ዲግሪየን ተማርኩ፡፡ ያ ወዳጀም ጉዳዩ ተጣርቶ በህግ እንዲጠየቅ ከተወሰነ በኋላ፤ ወደ ውጭ አገር ወጥቷል ተባለና ነገሩ በዚሁ ቀረ እላችኃለሁ፡፡
—————///////——
እዚህ ላይ ላነሳ የፈልግኩት አንድ ቁም ነገር አለ፡፡ ይሄውም የጎንደር 105 የመንግስት ቤቶች በህገ-ወጥ መንገድ መሸጣቸው(በመረጃ የደረስንባቸው ብቻ ናቸው)፤የመብራት ሀይል ግቢን ለባለሀብት ለመሸጥ ስምመነት መደረሱን፤ ደርስንበት በማስቆማችን፤ ፔፕሲ አጠገብ ያለውን የጅንአድ ግቢ ለግለሰብ ለመሸጥ ስምምነት ተደርሶ እንደነበር በማወቃችንና እሱንም አንሰጥም በማለታችን የወረደብን መከራ ህዝብ እንዲያውቀው ብየ ነው፡፡ ተገዝቶ የጠፋው አውቶብስ፤ ያልተሰራው አስፓልት ተሰርቷል ተብሎ ክፍያ ተፈጽሞበት ያገኘነው ባለቤት አልባ መንገድ፤ ወዘተን …ትቸው ነው፡፡ የአስፓልቱና የመኪናውን ነገር ከዋሸሁ ደግሞ በተለይም ደሳለኝ አስራደ ፤እረዚቅ ኢሳና አወቀ አስሬ ውጡና  እውነቱን  ተናገሩ፤እኔንም ብቸኛ  ውሸተኛ አታስመስሉኝ፡፡
ጎበዝ! ጎንደር እኮ አጥንቷ  ቀርቷል! ግን ጎንደር ምንጊዜም ጠንካራናት፤ሁሉንም መከራ ትችለዋለች፡፡ አሳዛኙ ነገር ደግሞ :ጎንደር የምትበሳቆላው በራሷ ልጆች መሆኑ ነው፡፡ ጎንደር ጥናቱን ይስጥሽ፤ሌላ ምን አቅም አለኝ፡፡ ለሁሉም በ2003/2004 ዓ.ም ጎንደር ውስጥ በአመራሩ  መካከል በተለይም በእኔና በወቅቱ ከንቲባ በነበረው ወዳጀ፤እስከ ሂዎት መጠፋፋት የደረሰ ግጭት ተገብቶ የነበረው፤መነሻው ምንም አይደለም፤በወቅቱ ጎንደር ውስጥ የህዝብ ንብረት ክፉኛ ስለተመዘበረ፤ይሄንን ወንጀል ለመደበቅና ለማጋለጥ በነበረ ትንቅንቅ የተፈጠረ ችግር ነበር፡፡ እንግዲህ በወቅቱ  በኔና በዛ ወዳጀ መካከል የነበረውን ሀይለኛ ትንቅንቅ፤ በወቅቱ የነበራችሁ ብአዴን አባላት አስተውሱት፡፡
ዛሬም ላይ ሁኘ የሚገርምኝ አንድ ነገር አለ፡፡ በዛን ወቅት  በሰራው ጥሩ ስራ መሸለም የሚገባው ቹቹ አለባቸው  እንዴት ተባረረ? ጉድ እኮ ነው! ስለ እውነት እኔ እኮ በ2004 ዓ.ም ጎንደር ላይ በነበረው ትግል መሸለም የሚገባኝ እንጅ የምባረር ሰው አልነበርኩም፤ ግን እንኳን ተባረረርኩ፡፡ ለነገሩ በ2008 ዓ.ም በነበረው ትግልም መሸለም የሚገባን ሰዎች (በተላይም ሻንበል ከበደና እኔ)ተባረን፤መባረር የሚገባቸው እነ እንቶኔ  በሰልጣን መቀጠላቸውን ሳስበው፤ የብአዴን ነገረ ዛሬም ይገርመኛል፡፡
ለሁሉም በ2003/4/ ጎንደር  ክፉኛ ተመዝብራለች ፤አጥፊዎቹ ይጠየቁ በማለታችን ዋጋ ከፍለናል፡፡ ስለ እውነት በወቅቱ የኔም ሆነ የኔ መሰሎቹ ጓደኞቸ፤ ዋነኛው ትግላችን የከተማውን አመራር ለማጥቃት አልነበረም፤ በፍጹም አልነበረም፡፡የፈለግነው በረከትን ማግኘት ነበር፡፡ ምከንያቱም ጎንደር እንደዛ አጥንቷ እስኪወጣ ድረስ፤ እንድትመዘበር ያደረገው፤ ባልተወለደ አንጀቱ በረከት ለሚቀርባቸው አመራሮች ስልክ እየደወለ እንዳስፈጸመው ጠንቅቀን ስለምናውቅ ነበር፡፡ ነገሩ የገባው አንበርብርዋ ደግሞ፤ይሄ ቹቹ የሚባል ትምክተኞ፤ የጎንደር ከተማን ከንቲባና አመራር ስራ አላሰራቸው ስላለ፤ከስልጣኑ አንሱት የምትል ቀጭን ትእዛዝ ሰጠ፤ እነ እንቶኔ አስፈጸሟት፡፡
ለሁሉም፤ በተለይም የበረከት ወንጀል ሲጣራ፤ተጣርቶ ያደረ የጎንደር ጉዳይ አለና፤አዴፓ ብትፈልግ በተራ ሙስና ደርበህ፤ ያለበለዝያም በፖለቲካዊ ሙስና ደርበህ ክሰስው፤ ነገ ለኔ የሚል ነገር አስወግድ፡
Filed in: Amharic