ሀይለገብርኤል አያሌው
የሰላማዊ ትግል አምድ ‘’I Have a Dream ‘’ በሚል የተስፋና የትንቢት ቃሉ የሚታወቀው የጥቁሮች የነጻነት አባት Martin Luther King Jr ልደት ተከብሮ የሚውልበት የአሜሪካብሄራዊ በአል እለት ነው::
ይህ ጀግና ለሕግ ልዕልና ለዜጎች እኩልነት እስከ ሕይወቱ ፍጻሜ በጽናት ታግሎ ታሪክ ጥሎ አልፏል:;
በአለም ላይ ከነገሱ ነገስታትና ሃያላን በላይ ስሙ የገነነ ዘወትር በበጎ ተምሳሌትነቱ ሲወሳ የሚኖር የምድራችን ልዩ ባለዝናና ተወዳጅ የሰላም ሰው ለመሆኑ የሚወዱት ብቻ ሳይሆን የሚጠሉትና ያስገደሉት ጭምር የሚመሰክሩት እውነት ነው:: ማርቲን ሉተር ኪንግ ሕልም አለኝ! በሚለው ዘመን ተሻጋሪ ንግግሩ አንድ ቀን በዚህች ሃገር የቀለም ልዩነት ጠፍቶ ሰዎች በሰውነታቸው እንደሚከበሩ ተናግሮት የነበረው ትንቢታዊ ቃል እርሱ ባያየውም በቀጣዩ ትውልድ ዘመን ተግባራዊ ሆኗል:: ሕዝቡም ጀግናውን የማይረሳ ታሪኩንም የማይዘነጋ በመሆኑ ይህው ዛሬ በሕይወት ካሉት የአሜሪካ መሪዎች ልቆ ልደቱ የሚከበር ተጋድሎው ሲዘከርና ሲታወስ ይኖራል::

ይህ ወቅት ሲታሰብ ለዲሞክራሲ ለዜጎች እኩልነት ለመብትና ነጻነት የታገሉ ሁሉ የሚከብሩበት:: ስማቸው ከፍ ብሎ የሚነሳበትና ታሪካቸው የሚነገርበት አጋጣሚ ነው:: እስክንድር ባለመሸነፍ አቋሙ በጽናት በቁርጠኝነቱ እና በትውልድ ተምሳሌትነቱ በኢትዮጵያ የትግል ታሪክ ውስጥ ስሙ ለዘመናት ከፍ ብሎ ሲነሳ ይኖራል:: እስክንድር በትንታግ ጋዜጠኝነቱና በመብት ታጋይነቱ በአለማችን ካሉ ስመጥር ታጋዮች ጎን የተደመረና አለም አቀፍ እውቅና የተቸረ የሰላም አርበኛ በመሆኑም ምሳሌና አዐያነቱም ሌሎች የምድራችን ሃገራት ሕዝቦች የሚጋሩት ባለ ታሪክ ያደርገዋል::
እኛ ኢትዮጵያውያን በተግባራዊ ስራቸው በሃገራዊ አስተዋጽዖቸውና በተጋድሏቸው የምንዘክራቸው ለትውልድ ምሳሌ ለሃገሪቷም አሴት የሚሆኑ የጋራ ብሄራዊ ጀግኖች ልናከብር ይገባል:: ይህ ደግሞ በቅርቡ እንደሚሆን :
” ሕልም አለኝ”
‘ድል ለዲሞክራሲ’!