>

አሳ ጎርጉዋሪ ዘንዶ ያወጣል!!! (ተስፋዬ ተሰማ)

አሳ ጎርጉዋሪ ዘንዶ ያወጣል!!!
ተስፋዬ ተሰማ
አንድ ወዳጀ የሰሞኑን የጀዋርን እርስ በርስ የሚጣረስ ወሬ ሰምቶ “የኢትዮጵያ ህዝብ ( ( የአዲስ አበባ ነዋሪ) ከጀዋር ቄሮ መጣባችሁ ማስፈራራት መች ነው የሚገላገለው?”  ብሎ አንዱን የፓለቲካ ተንታኘ ጠየቀው
የፓለቲካ ተንታኙም ጀዋርን  በ3 ቃላት ግለፅ ብባል የምናገረው ነገር አለ “ጀዋር የራሱ የሆነ ምንም አይነት  አላማ  (INTENTION) የሌለው ፣ የሚያወራው ነገር ጀዋር እንዲህ አለ ተብሎ የሰውን ትኩረት  (ATTENTION) ወደሱ ለመሳብ ብቻ የሚወራ ፣ ለውጡ ከመጣ ጀምሮ ያወራቸው ነገሮች አንዱም ወደ ተግባር (ACTION) ያልተፈፀመለት ቀባጣሪ ነው።  አለ
ሰሞኑን ስለአዲስ አበባ በፌስቡክ ገፁ ላይ  “በግልጽ እንደሚታወቀው  ፊንፊኔ የኦሮሚያ ዋና ከተማ የብሄር ብሄርሰቦች መኖሪያ ናት” ይህ ነገር እንዲፈፀም
“ድርድር” ይደረግ ብሎ ፅፎ ነበር ። የሰው ትኩረት የመሳብ ሱስ የተጠናወተው ስለሆነ በአንድ ሰአት ልዩነት በዚሁ ጉዳይ በራሱ ሚዲያ ኢንተርቪው ተደርጎ በፌስቡኩ ለቆታል።በነገራችን ላይ በዚህ ነገር ላይ በቀጥታ  የሚመለከታቸው ባለስልጣናት እንደሱ በየጊዜው እየተነሱ አይቀባጥሩም
የጀዋር በህገመንግስቱ  እንደራደር ጥያቄ ግራ የሚያጋባ ( Confusing ) እና   ከየት ጀምሮ የት እንደሚያልቅ የማይታወቅ  (disorentating)  ጥያቄ ነው።
በኢትዮጵያ ህገመንግስት በግልፅ እንደተቀመጠው አዲስ አበባ የፌዴራል መንግሰቱ ዋና መቀመጫ እንጅ የኦሮሚያ ዋና ከተማ አይደለችም ። በታሪክም አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ፣ የሸዋ ክፍለሀገር ዋና ከተማ እንጅ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ሆና አታውቅም።
ከ27 አመት በፊት በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ኦሮሚያ የሚባል ክልልም ኖሮ አያውቅም ( በረራ የሚለውን በማስረጃ የተጠናከረውን የአዲስ አበባን የጥንት ታሪክ ለግዜው አቆይተነው ማለት ነው)
ከተሞችን በተመለከተ በህገመንግስቱ ላይ ድርድር ይደረግ ከተባለ ደግሞ ድሬድዋ 40 ፐርሰንት  ኦሮሞ – 40 ፐርሰንት ሶማሌ  – የቀረውን 20 ፐርንሰት ሌላው ኢትዮጵያዊ በኮታ ያስተዳድራት የሚል በአለም ያልታየ ዘረኛ አሰራር አብሮ ለድርድር መቅረብ አለበት። የድሬድዋ ሰው በኮታ ሳይሆን በመረጥኩት ሰው ልተዳደር የሚል አጭር እና ግልፅ ጥያቄ ጠይቆአል። በዚህ ጉዳይ ከድሬድዋ ህዝብ ጋር ተደራደር
ይሄ አሁን ያለው ህገመንግስት ለድርድር ይቅረብ ከተባለ አዲስ አበባ በተመለከተ ሳይሆን በህውሀት ኢሀዲግ ዘመን ኦነግ አጭበርብሮ የወሰደው የከፋ ፣የየም የሌሎች ኢትዮጵያዊያን የጋራ ከተማ የሆነችው የጅማ ከተማ ለምን በኦሮሞ ብቻ ትተዳደራለች የሚለው የተዳፈነው የህዝብ ጥያቄ ተነስቶ ለድርድር መቅረብ አለበት። ጀዋር ለዚህም ድርድር መዘጋጀት ይኖርበታል
የናዝሬት ፣ የደብረዘይት ፣ የሀረር ከተማ የሌሎች የኦሮሚያ ከተማ  ነዋሪወችም ቀን የሚጠብቁለት  የራሳቸው የመብት ፣ የእኩልነት እና የነፃነት  ጥያቄ አላቸው ። ጀዋር ከነዚህ ኢትዮጵያዊያን የመብት ፣ የእኩልነት እና የነፃነት ጥያቄ ካላቸው ወገኖች ጋር ለድርድር መዘጋጀት አለበት
እስክንድር እንዳለው በመጭው የአዲስ አበባ  ምርጫ ጥሩ ተመራጭ ለመሆን የሚያስብ ተወዳዳሪ፣  ግለሰብ ወይም ፓርቲ  “ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ልዩ  ጥቅም አላት ” ብሎ ለአዲስ አበባ ከተማ መወዳደር አያዋጣውም ።
አዲስ አበባ እና በአካባቢው ያሉ ትንንሽ ከተሞች በሌላው የአሜሪካን እና የአውሮፓ ትልልቅ ከተሞች እንደተለመደው  በትራንስፓርት  (better commuter belt) ፣ በመሰረተ ልማት  (infrastructure) እና በተቀለጣጠፈ አሰራር  (facilities) እንዴት አብረው መጠቃቀም ይችላሉ ብሎ መደራደር አስፈላጊ ነው።ይህ መጠቃቀም ነው።
ኦሮሚያ  ከአዲስ አበባ ልዮ ጥቅም ያግኘ ማለት ግን መጠቃቀም ሳይሆን ተራ ብልጣብልጥነት ነው። ይህ የልዮ ጥቅም ጥያቄ አንድነትን የማያመጣ ፣ ዘረኛ ፣ ኢፍትሀዊ ፣ በዜጎች መካከል እኩልነት እንዳይኖር የሚያደርግ  አሰራር ነው።
 “በግልጽ እንደሚታወቀው  ፊንፊኔ የኦሮሚያ ዋና ከተማ የብሄር ብሄርሰቦች መኖሪያ ናት”  የሚለው የጀዋር የፌስቡክ መልእክት ፣ ይህ ነገር ካልተፈፀመ ቄሮን እልካለሁ ብሎ ለማስፈራራት የሚያደርገው ጥረት ደግሞ የለየለትእብደት ነው። ጥሩ ነገሩ ይህን  ነገር የተናገረው ጀዋር ነው።ባለፋት ወራት በተደረገው የለውጥ እንቅስቃሴ  ጀዋር ብዙ አውርቶ አንድም የተፈፀመ ነገር ስለሌለ ይሄም ቅዠት ያንድ ሰሞን ወሬ ሆኖ ይቀራል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ።
ኢፍትሀዊ የሆነው የይገባኛል ጥያቄ ከቀጠለ ግን ሌላውም ማህበረሰብ አፍኖ ያስቀመጠው ጥያቄ ስላለ አሳ ጎርጉዋሪ ዘንዶ ያወጣል የሚለውን ተረት እውን የሚሆን ይመስላል።
Filed in: Amharic