>
1:57 am - Saturday December 10, 2022

ዝክረ - አድዋ የወሊሶው የአፄ ምንሊክ  ጦር አዝማች ደጀዝማች ገረሱ ዱኪ (በጋዜጠኛ ቶማስ ደርቤ)

ዝክረ – አድዋ
የወሊሶው የአፄ ምንሊክ  ጦር አዝማች ደጀዝማች ገረሱ ዱኪ
 
የፋሺሽት ኢጣሊያን ዳግም ወረራ ድባቅ የመቱ ጀግና ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ(አባ ቦራ)
በጋዜጠኛ ቶማስ ደርቤ
      አፄ ሚኒሊክ ሀገር ለህዝብ ሰርተው ሰተዋል።ልዮነታችን አጥበው አንድነታችንን በኢትዮጵያዊነት አሰረው ህያው ሰራ ሰርተው አልፈዋል።ሰልጣኔ ፣ጀግንነት ፣የሀገር ፍቅር ፣የባንድራ ክብር እና ነፃነት ቀድመው አውቀ ብዙ ጀግናዎች አፍርተው ፤ እኛ ኢትዮጵያዎያን ደግሞ ሌሎቹ ከባርነት ነፃ የወጡበት ሊያከብሩ ቀን ሲቆርጡ ፤ እኛ ግን ትላንት በተከፈለ ደም አደባባይ ላይ የምንወጣው የድል በአል ልናከብር ብቻ ነው።
እምዬ ሚኒሊክ በሀገራችን ኢትዮጵያ የሰሩትን ታሪካዊ ገድል ተከትሎ ብዙ ጀግናዎች ከእሳቸው በሃላ አፍርተዋል።ዘር ፣ቀለም ፣ብሄር ሳይለይ ሚኒልካዊ ጀግኖች አይተናል።ከብዙዎቹ አንደኛው ጣልያን በ1936 እስከ 41 ተመልሶ  ሀገራችን ላይ የባርነት ቀንበር ሊጭንብን ሲሞክር ሀገር የጠበቁት ደጃዝችማች ገረሱ ዱኪን ዛሬ እናነሳለን።
በአዲስ አበባ ጀማ በሚወስደው መንገድ 109 ኪሎ ሜትር ከሸገር በምትርቀው በወሊሶ ከተማ የአፆ ሚኒልክ የመንፈሰ ልጅ ገረሱ ዱኩ ብዙ ይታወሳሉ።በ1905  በማሩ ወሊሶ አቅራቢያ የተወለዱት እኝ ጀግና የሀገር ዘብ የሆኑት ገና በለጋ እድሜቸው ነው። ጠላት ጣሊያንን በደቡብ ኦሮሚያ እስከ እስከ ኦሞ አካባቢ ነጩን ጦር የፈተኑት ናቸው።
የዱኪ ጉልማ ልጅ ገረሱ ዱኪ ለእናታቸው ወርቄ ኤልሞ ልዮ ፍቅር ነበራቸው ይባላል።እናታቸው ለቀድሞ አባት አርበኖች ያላቸው ክብር ገና በልጅነታቸው ለገረሱ ሰለሚያወሩለት ገረሱ የአድዋን ታሪክ ሰምተው ፣ እራሳቸው ታሪክ ፅፈው አሳዮን።ገረሱ ዱኪ የብሄር ፖለቲካ ሳይሆን የሀገር ፍቅርን ሰምተው ለሀገር የሰሩ ጀግና አርበኛም ናቸው።ኦሮምኛ እና አማርኛ አቀላጥፈው የሚናገሩት እኚው አርበኛ ሀገር ነፃነት ለተማረም ላልተማረም በልጅነታቸው አሰተምረው ፣አርአያ ሆነው አሳይተዋል።
በጀግንነት ስማቸው አባ ቦራ ፋሺት ኢጣልያንን እሳቸው ባሉበት ከደቡብ ኦሮሚያ እስከ ኦሞ ወንዝ መቀመጫ አሳጥተውታል።የኦሮሚያ ገበሬዎች አሰባሰበው በደፈጣ ተዋግተዋል።50 ሺ የአካባቢው ነዋሪዎች ሀገርን ከቀኝ ገዢ ፣ኢትዮጵያን ለኢትዮጵያን ለማሰቀረት ደማቸው ገብረዋል።
ፋሺሺት ኢጣሊያን በአምስት አመት ቆይታው የተቃወመውን አይደለም ለመቃወም ያሰበውን በአደባባይ በዘመናዊ መሳሪያ ሲረሽን ፤ ወጣቱ ጀግና ገረሱ ግን ብርታት ሆናቸው።የእሳቸው አልሸነፍ ባይነት በደቡብ ምዕራብ ሸዋ እስከ ጀማ ድረስ ብዙ ሺ ጀግና ወጣቶችን ጫካ አሰገባ።ፋሺሽት ወጣት እየረሸነ በእየጉዳናው ሲያሰፈራራ ወጣቱ ግን ጀግናውን አርበኛ ተከትሎ ጫካ ከተመ።
አባ ቦራ በዛ የሞት ሸረት ውጊያ ላይ ገና ለጦርነት ያልደረሰው የ15 አመት ልጃቸው ተፈራ ገረሱን በጦርነቱ አሳትፈዋል።ሀገር ከምንም ይቀድማል ያሉት ጀግናው አርበኛ ብላቴናው ልጃቸው ጀግንነት አሰተማሩት።እሳቸው ከአድዋ ጀግንነት ሲማሩ አልተወለዱም ፤ ለልጃቸው ግን በግንባር አሳዮት።
ጎጃም በላይ ዘለቀ ጣሊያንን ሲያንቀጠቅጥ ፤ገረሱ በከፍታዋ የወሊሶ ምድር ጣሊያንን ርዝራዥ ድል ነሳው።ጣሊያን መላው ኢትዮጵያን በባርነት እንዳይገዛ ካደረጉት ጀግኖች አንደኛው ሆነው ታሪክ ላይ ሰፍረዋል።
እንደ እኛ በወሊሶ ለተወለደ በልጅነታችን ፊደል ልንቆጥር ስንሄድ ነው ደጃዝማች ገረሱ ዱኪን በትምህርት ቤት መንፈሳቸውን የሰጡን።ትምህርት ቤቱ የእሳቸው ገድል ሲያሰታውሰ ፤ እኛ ደግሞ የእሳቸው የሀገር ፍቅር በልጅነታችን ወስደናል።
በወሊሶ ከተማ ግንባር ላይ በመጀመሪያወ ረድፍ ሰማቸው የሰፈረ ዝነኛ እና ጀግናው ገረሱ ዱኪ መላው የአካባቢው ሰው ታሪክ ብቻ ሳይሆኑ የሀገር ቅርስ ናቸው።
በ1980ዎቹ ሚኒሊክ ጥቁር ሰው ለሀገር ፀሃይ ሆነ።በ1936 እስከ 41 ደግሞ የአድዋውን የእምዬ ሚኒሊክ ፀሃይ አይተው ብዙ ጀግና አባቶች በመላዊ ኢትዮጵያ ሚሊየኖችን አሰለፉ።ታሪክ እንዲ ነው ጥቂቶች በምጡቅ አእምሮ ሚሊየኖችን ይመራሉ።
የአድዋ ታሪክ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካም ነው።የጥቁር ህዝቦች ድል ነው።የአድዋ ጦር መሪ ደሞ አመንክም አላመንክም አፄ ሚኒሊክ ናቸው።ህዝብ በመሪዉ ይወከላል ፣ይመራል።ሚኒልክ ከክብር በላይ ክብር ይገባዋል።ዛሬም ጀግና ለመሆን የትላንቶቹን እናክብር ፣እውነት እንደ እውነት እንቀበል ፣ሀቅ ሀቅ ነው።ከሀቅ ጋር አትከራከር።የትላንት ጀግናዎችን ካላከበርክ ዛሬም የአንተ ጀግንነት የነገ ላይ አይነገርልህም።
የእኚን አባት አርበኛ ታሪክ የምዘክር ሙዚየም ከወሊሶ ከተማ በ10 ኪሎ ሜትር በሚርቀዉ ቁልቢ ገብርኤል አጠገብ ይገኛል።በጅግነታቸው የሰሩቸው ስራዎች እና ሀገራዊ ታላላቅ ሽልማቶችም የያዘ ነው።የአርበኛው ገድል በታላላቅ  የውጪ ሀገር መፅሃፍት ጭምር ያላቸውን ታሪኮች በአነሰተኛው ቤተ መዘክር ይገኛል።የእሳቸው የሀገር ፍቅር ስሜት እና ለሀገር መኖር ያለው ክብር በወጣት እና እልህ በተሞላበት ቁጡ ፊታቸው በፎቶዎች ላይ ይታዘባሉ።
እኛ የገረሱ ልጆች ዛሬም ሀገራችንን እንጠብቃለን።ኢትዮጵያን ለማጥፋት ለሚሰራ እና የትላንት ሀቅ ለመካድ ለተዘጋጀ ሁሉ ዛሬም አርበኛ ነን።ክብር ለደጃዝማች ገረሱ ዱኪ።
Filed in: Amharic