>
11:52 am - Sunday May 22, 2022

የኢሃድግ ካድሬዎች ለ"መ+ደ+መ+ር"ሥልጠና ያስፈልጋቸዋል፤.... (ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ)

የኢሃድግ ካድሬዎች ለ”መ+ደ+መ+ር”ሥልጠና ያስፈልጋቸዋል፤ “አልፈልግም” የሚሉ አይገደዱም፤ምዝገባው ግን  የዜግነት ግዴታ መሆኑን ሊያውቁት ይገባል።

 ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ 
 

“የቀጠለ”ከአንዲቷ አዝማሪ።
 
እንረስ ካላችሁ ተስማምተን እንረስ፤
እንተወው ካላችሁ ተዉት አይታረስ፤
የናንተ ፈርሶ ነው የእኛ ቤት የሚፈርስ።
ባቴን ደነዘዘኝ፣ምላሴን እንደ እግር፤
ለካስ ነፃነት ነው እንዳሻ የሚያናግር።….
እሳት ነዶ ነዶ ዳርሆኖ ይሞቃል፤
እስኪደርሰው ድረስ ሰው በሰው ይስቃል።
ቆስቁሰው ቆስቁሰው ያቃጠሉት ክምር፤
ብቻውን አይነድም ቆስቋሹን ሳይጨምር።
ምነው አላማጣን ግሙ ዝምብ ወረረው፤
አልፎ የሚከለክል ጌታ እንዳልነበረው።”
          እነሆ ላለፉት ስምንት ወራት ኢትዮጵያውያን በዶክተር ዐቢይ አህመድ አመራር እና በክቡር አቶ ለማ መገርሳ ቡድን ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ወደሽግግር መንግሥት ለማምራት ለለውጥ እየተዘጋጀን እንገኛለን።ዝግጅቶቹ ደግሞ ውስብስብና ሰው ሰራሽ ችግሮች ያሉባቸው ትግል ናቸው፤ የሚያወሳስቡባቸውም ሦስት ቡድናዊ ምክንያቶች አሏቸው።እነርሱም በትግል ዝግጅታችን ውስጥ በቡድን ተከፋፍለው፦”መ+ደ+መ+ር”ን የሚደግፉ፣”መ+ደ+መ+ር”ን የሚነቅፉ እና በ”መ+ደ+መ+ር” የሚያጭበረብሩ አካላት መኖራቸውን  ያመላክቱናል።
ሁለቱ ተፎካካሪ አካላት፣ማለትም “መ+ደ+መ+ር”ን ደጋፊ እና የማይደግፉ ተፎካካሪዎች ሲሆኑ፤ሦስተኛው አካል ግን በሁለቱ መካከል በፈለገው ጊዜ በመካከላቸው እየገባ እና እየወጣ፤ልዩነታቸውን የሚያጠብና የሚያሠፋ ችግር ፈጣሪ ስለሆነ በሕዝብም ተፈላጊዎች አይደሉም፤ስለዚህም ነው ድብቁ”ሦስተኛው”እጅ ተብሎ የሚጠራው፣በተዘረፈ ገንዘብ የሚንቀሳቀስ፤በሕገ-ወጥ መሳሪያዎች ሕዝብን የሚያሸብር ስለሆነ ነው።
      የኢትዮጵያን የለውጥ ፈተናችንን በጥልቀት ስንመለከት፤የለውጡ ባለቤት የሆነውን የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ለዳኝነት ማዕከል አድርገው በመንግሥት አሰራር መሠረት የፖለቲካ ድርጅቶች ሕጋዊ ውሳኔዎችን ለመከተል በትግል መሥመር ላይ በሃሳብ እየተፋለሙ ይገኛሉ።ይሁን እንጂ የ”ሦስተኛው እጅ”በሕገወጥ መንገድ በጦር መሳሪያ ዝውውር እና ገንዘብ ዝርፊያን ጨምሮ፤በስውር ሥልጣንን በመጠቀምም ጭምር የሰውን ሕይወት በማጥፋት ላይ ይገኛሉ።እናም የሕዝቦችን መፈናቀል እና መገደል ሰበቦቹን እና ምክንያቶቹን ከስድስት ወራት በፊት አመላክቻለው፤ለዚህም የማሸነፍ ግቡ በመቅደም እንደሚጀምር ለማስረዳት ሞክሬአለሁ።
 
የሶስተኛውን እጅ  ያለ ይሉኝታ በአደባባይ የመዋጋት፤ ወቅቱ አሁን ነው (አቢይ…) 
 
የቁም-እስር”ሕዝቡን እንዳይፈናቀል ከረዳ፥ …..  (ዐቢይ ኢትዮጵያዊ )
 
ሌሎችንም ጦማሮች ማውጣቴን እየገለፅኩ ዳሩ ግን ዛሬም ችግሮቹ እየሰፉ መጥተው ወደየዋና ከተሞቹ ዘልቀዋል።በተለይም ለውጡን መራራ የሕይወት ዋጋ እያስከፈሉት ሠላምን ለማሳጣት፤ በኢሕአድግ ሥም  የሕውሃት ፓርቲ ካድሬዎች እና አባላት  አፍራሽ ተግባሮችን እየፈፀሙ ይገኛሉ።ስለዚህ የትግል ስልቱ አሉታዊ እንዳይሆንና አዎንታዊ መንገዱ ወደ ሕዝብ አመፅ እንዳያመራ፤ምንጊዜም የሕዝብን ችግሮች ለመፍታት ዝግጁ መሆን ይገባል።ከዚህም አንፃር የቅደም ተከተል ችግሮቹን”ይሄ ይሻላል” ብዬ እንደ እኔ ፍላጎት አቅጣጫ እንዲቀየር ለማሳሰብ ሳይሆን፤የ”መ+ደ+መ+ር”ዓላማ ሳይገባቸውም ይሁን፤ገብቷቸው እንዳልገባቸው ሆነው ለሌላ የአፍራሽነት ዓላማ የተሰለፉ በመሆናቸው፤የቀዳሚነት መልካም መንፈስ በማስረፅ የበኩሌን አስተዋፅኦ ለማበርከት ነው፤ስለሆነም እነሆ በነቂስ የመፍትሔ ሃሳቦዎቼን ዛሬም አስቀምጫለሁ፤ልብ ያለው ልብ ይበል።
         በቅድሚያ ከሁሉም በፊት”መ+ደ+መ+ር”ማለት እኔ ወይም ሌላው ሰው በቅንነት ለማስረዳት እንደምንሞክረው አይደለም፤በተገቢው መንገድ ሥልጠና የሚያስፈልገው ነው።በተለይም ባለፈው ሥርዓት ውስጥ ሲያገለግሉ ለነበሩት የጥላቻ ልቦናቸውን ለማደስ፣ዶክተር ዐቢይ አህመድ በአደባባይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ተጎናብሰው የኢትዮጵያውያንን የእሺታ ሕዝበ-ይቅርታ በጭብጨባ ተቀብለዋል።አሁን ያለው የተባረከ አዋቂ ጨቅላ መንግሥት ሕዝባዊነቱ የተረጋገጠው፤ሙሉ በሙሉ እየተናደ ካለውና እየመሸበት ከጨለመበት ሥርዓት ጋር:- ፍፁም ተቃራኒ የሆነ ዓላማ ያለው ስለሆነ ነው።እናም መጀመሪያ የትኛውም ካድሬ እና አባል ተመዝግቦ የ”መ+ደ+መ+ር”ፅንሰ-ሃሳብን ትምህርት ሊወስድ ይገባል።ትምህርቱን መውሰድ ባይፈልግም መመዝገብ ግን የዜግነት ኃላፊነት  ነው፤ይህም በሽግግር ወቅት በማህበር ውስጥ የሚደረግ በመሆኑም ኢሠፓዎችም ለለውጥ ይሁንታቸው ስልጠናና ምዝገባ መፈፀማቸውም አይዘነጋም።እንግዲህ የኢሓድግም ሥርዓት እያከተመ በመሆኑ አዲስ የ”መ+ደ+መ+ር”ሥርዓት መጥቷል፤ይህንንም ለውጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ በይቅርታ ተቀብሎታል።የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢትዮጵያን እንደ አገር በዓለም-አቀፍ ደረጃ ለማዳን፣ በኢኮኖሚም ሆነ በማሕበራዊ ዘርፍ ለፖለቲካው የትግል ሕልውና ሲባል ከመጠፋፋት አድነዋታል።ስለዚህ”ያ!!!”አገርን የማዳን ትግል የተሳካው ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ተ+ደ+ማ+ም+ሮ ነው።ይኸውም ከየአገሩ እስርቤቶች እንዲፈቱ ከተደረጉት ጀምሮ፣ከስደት ተመልሰው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ከተቀላቀሉት እና ወደ ውድ አገራቸው ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ከተደረጉት፣በአገር ውስጥም ካሉት እስር ቤቶች የነበሩት የፖለቲከኛ እስረኞች በሙሉ ከተፈቱ በኋላ ነው።
       እንግዲህ በአሁኑ ጊዜ የምናይበት የዶክተር ዐቢይ አህመድ መነፅር ሰከን ብሎ የ”መ+ደ+መ+ር”ቢሆንም ያለፈው ሥርዓት ጥፋቶች ግን፣በሕግ መልክ ተቀርፀው፣በፖሊሲ ሥም ተነድፈው፣በየትኛውም እንቅስቃሴዎች ላይ በሳንካነት እየተገኙ የፈለግነውን ያህል እንድንጓዝ አላደርጉንም።
             ስለሆነም ችግሮቹን ነቅሶ ማውጣት ይገባናልና እንዲህ ደክመንበትም፤ብዙዎች መስዋዕትነት ከፍለውበታል፣እናም የተሻለ ሥርዓት መገንባት ጀምረናል። የትኛውንም ያህል ርቀት፣ለዲሞክራሲ ግንባታ ብንጓዝም ሕዝብ ላይ ተንኮል መስራት የሚሹና የራሳቸውን ጥቅም ለማስከበር የሚፈልጉ የአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አራማጆች ሁሉ፤ለሕዝብ ደንታ ቢሶች ናቸው።ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ወደሽግግር መንግሥት ለማምራት ለለውጥ የምናይበት መነፅር ሰከን ያለው የ”መ+ደ+መ+ር”ጥበብ ነው።
        ያለፈው ሥርዓት ጥፋቶችን ለመንቀል በቅድሚያ የኢሃድግ ካድሬዎች በ”መ+ደ+መ+ር”ኢትዮጵያን ለማዳን የሚፈልግ ሁሉ ሥልጠና ያስፈልጋቸዋል፤ሥልጠናውን አንፈልግም የሚሉት ደግሞ ሊገደዱ አይገባም፤ምዝገባው ግን የዜግነት ግዴታ ነው፤እናም ወቅቱ የሽግግር  በመሆኑ በሥርዓቱ ውስጥ የነበሩት ሁሉ ሊመዘገቡ ይገባል።
    አንድ የሕውሃት ባለሥልጣን በገዛ ፈቃዳቸው ከሕውሃት ሲለቁ በቅርቡ በአደባባይ ለሕዝብ እንደገለፁት፣”በዶክተር ዐቢይ አህመድ”በቅንነት ሁላችንም አገራችንን በጋራ እንድነገነባ “የተሰጠው ዕድል ልንጠቀምበት ይገባል” ብለዋል።ሆኖም “አሉ”፣አያይዘውም ከዚህ የሕውሃት ድርጅት ጋር መቀጠል ስህተት ብቻ ሳይሆን ወንጀልም ጭምር ነው፤”ብለው አሳስበዋል።ስለዚህ የዶክተር ዐቢይ አህመድ የይቅርታ መ+ደ+መ+ር በሩን አልተዘጋምና በአፍራሽነት ሳይሆን የዜግነት ግዴታቸንን ልንወጣ ይገባናል።በቅድሚያም   ምዝገባችሁ ግዴታ መሆኑን ልናውቅ ይገባል።
     ዶክተር ዐቢይ አህመድም ይህን የምዝገባ አፈፃፀም በሕግ አስቀርፀው እንዲወጣ ካላደረጉ የመጀመሪያው በሰው ኃይል ምዝገባ ተጠቂው መንግሥት መሆኑን ላሳስብ እወዳለሁ፤የኢሃድግ ካድሬዎችም ለ”መ+ደ+መ+ር” ሥልጠና ያስፈልጋቸዋል፤አንፈልግም የሚሉት አይገደዱም፤ምዝገባው ግን ሁሉንም ሊመለከት ይገባል።
Filed in: Amharic