>
5:44 pm - Wednesday November 30, 2022

የኢሳት ሚዲያ አባላት ከም/ጠቅላይ ምኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተወያዩ!!!

የኢሳት ሚዲያ አባላት ከም/ጠቅላይ ምኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተወያዩ!!!
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የኢሳት ሚዲያ ቡደን አባላትን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኢሳት ሚዲያ ቡድን አባላቱ በሃገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ዙሪያ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በለውጡ ጉዞ እየገጠሙ ያሉ ፈተናዎችን እና ዕድሎችን ያብራሩ አብራርተው ሚዲያው ለለውጡ ስኬት ሚዛናዊ እና ገንቢ ሚናውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የኢሳት ሚዲያ የቡድኑ አባላት በበኩላቸው የተጀመረው ለውጥ ዳር እስከ ዳር እንዲሰርጽ ሙያዊ ሃላፊነታቸውን በሚዛኑ አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉ ተናግረዋል፡፡
ህዝብን እና ሃገርን ባስቀደሙ አጀንዳዎች ዙሪያ የጎደለው እንዲታረም – የተሻለው ደግሞ እንዲጠናከር በትኩረት እንደሚሰሩ የኢሳት ሚዲያ የቡድኑ አባላት አረጋግጠዋል፡፡
Office of Deputy Prime Minister of Ethiopia
Filed in: Amharic