>

ሰማያዊ ፓርቲ ከስሟል፤ ግንቦት 7 አባላት ምልመላ ላይ ተጠምዷል፤ ኢዴፓ አድፍጧል!!!  (ያሬድ አማረ)

ሰማያዊ ፓርቲ ከስሟል፤ ግንቦት 7 አባላት ምልመላ ላይ ተጠምዷል፤ ኢዴፓ አድፍጧል!!!
 ያሬድ አማረ
*የ97ቱን ቅንጅት የሚያስታውስ ከፊት አፍጦ የመጣ እውነት!
 
በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ያልተጠበቀ ለውጥ ተከትሎ የተለያዩ ፓርቲዎች ወደ ሀገር ቤት በመግባት ህጋዊ ትግል ለማድርግ በመሰባሰብ ላይ ይገኛሉ፡፡ በተለይ በዜግነት መብቶች ላይ መሰረት ያደረጉት የአንድነት ሀይል ሀሳባውያን ተግባብተውበታል ወይም ስምምነት ላይ ደርሰውበታል በተባለው የቀደመ ድርጅትን አክስሞ ከታች ወደላይ በሚዘረጋ መዋቅር አንድ ጠንካራ ሀገራዊ ፓርቲን የመመስረት ራዕይ እውን ለማድረግ በግንባር ቀደምነት ሰማያዊ ፓርቲ ራሱን በማክሰም አባላቱን በመበተን ወዳጆቹን ቢጠባበቅም እነ ግንቦት ሰባት በተለያዩ የምርጫ ወረዳዎች አዳዲስ አባላትን በመመልምል በግንቦት 7 ስም በማደራጀት ድርጅታዊ መዋቅራቸውን እያጠነከሩ ባላየ ግስጋሴአቸውን ቀጥለዋል፡፡ በአንጻሩ ህልውናውን ያከሰመው ሰማያዊም ሆነ የቀድሞ አንድነት ፓርቲ አባላትን እንቁልልጭ እያለ ያለበትን ሁኔታ እያስተዋልን እንገኛልን ፡፡ወትሮም ነገሮችን በጥርጣሬ የመመልከት ልምድ አለው የሚባለው ኢዴፓም ጠቅላላ ጉባዔውን በዚህ ወር በሀያዎቹ ይጠራል ተብሎ ቢጠበቀም እስካሁን ስለጠቅላላ ጉባኤው የተባለም እየተደረገ ስላለው እንቅስቃሴ ምንም  ሳይል አድፍጦ የግንቦት ሰባትን እንቅስቃሴ በጎሪጥ እኮመኮመ አንደበቱን ለጉሞ ተቀምጧል፡፡ ይህ ሁኔታ በቀጣይ ወዴት ያመራ ይሆን? ድርጅቶች ይከስማሉ በየወረዳው እንደ አዲስ በአዲሱ ፓርቲ ስም ይደራጃሉ የሚል የጋራ መግባባት ካለ ግንቦት 7 ለብቻው በስሙ በየምርጫ ወረዳዎች እያደረጋቸው ያሉ የአደረጃጀት በምን አግባብና ምንን ፍርሃት ነው የሚለውን ጥርጣሬ ከማስነሳቱም በላይ
* ሌሎች እንዲከስሙ ጠጠር አቀብሎ የራሱን አደረጃጀት እየገነባ እየሄደ ያለው ግንቦት 7 መቆሚያው የት ይሆን?
* ግንቦት ሰባት ድርጅቱን ለማክሰም ለምን ፈራ ?ለምንስ አዲሱን አደረጃጀት ቸል በማለት የራሱን አደረጃጀት እየገነባ መሄድ አስፈለገው?
* የቀድሞው ሰማያዊና አንድነት ፓርቲ አባላት ቀጣይ ሚና ምን ሊሆን ይችላል?
* አዲስ አደረጃጀት መኖር አለበት ያለው ኢዴፓም ከግንቦት 7 ጋር የጎሪጥ መጠባበቁን ትቶ ፓርቲውን ያከስም ይሆን?
የሚሉት ጥቄዎች ዛሬም መልስ የሚያሻቸው ከመሆናቸውም በላይ አሁን እየተደረገ ባለው እንቅስቃሴ የ97ቱን ቅንጅት የሚያስታውስ ከፊት አፍጦ የመጣ እውነት ሆኗል፡፡አለባብሰው ቢያርሱ ባረም ይመለሱ የሚለው ብሂል እንዳይደገም ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡
Filed in: Amharic