>

በ30 ዓመታት ውስጥ እጅግ ያፈርኩባቸው ሁለት ፖለቲካዊ ክስተቶች (ምሕረት ዘገዬ)

በ30 ዓመታት ውስጥ እጅግ ያፈርኩባቸው ሁለት ፖለቲካዊ ክስተቶች

ምሕረት ዘገዬ

የሰው ልጅ ከቅዱስና ርኩስ መናፍስት የጠበቀ ቁርኝት ያለው እንደመሆኑ ደግም ክፉም የመሆን ጠባይ አለው፡፡ በአንድ ሰው ውስጥ ሰውዬው ኮትኩቶና አርሞ እንደየሚያሳድገው የጠባይ ዓይነት ደግም የመሆን መጥፎም የመሆን ዝንባሌዎች በአንድ ጊዜ ባይሆንም በተወራራሽነት ይታዩበታል፡፡ በዚያ ላይ በ Criminology የጥናት ፈለግ የወንጀለኝነትን ጠባይ እንደሚጠቁሙ የሚነገርላቸው የDNA እና የ “X” እና “Y” chromosomes ነገር እንዳይረሳ፡፡
በተማሪነት ዘመኔ የማውቀውን ፕሮፌሰር ሳምነርን የመሰለ ከሞላ ጎደል ሁሉንም ደሞዙን ለሕጻናት ማሳደጊያ በጎ አድራጎት ድርጅት የሚሰጥ መልካም ሰው የመኖሩን ያህል መለስ ዜናዊን የመሰለ ሕዝብን በዘርና በጎሣ ከፋፍሎ በማፋጀት የሚደሰት ጨካኝ ዐውሬ ደግሞ አለ – sadist፡፡ ማዘር ቴሬዛን የመሰሉ ራኅራኂተ-ልብ እናት የመኖራቸውን ያህል መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን የመሰለ ትውልድን አራጅ ሰውም አለ፡፡ ኔልሰን ማንዴላንና ማኅተመ ጋንዲን የመሰሉ ለሰው ልጆች ነፃነትና እኩልነት የታገሉ የመኖራቸውን ያህል ሂትለርንና ሙሶሊንን የመሰሉ ሰውን ባርያ ለማድረግ የጣሩ ዐረመኔዎችም አሉ፡፡ ሕወሓትን የመሰለ ዐውሬ ድርጅት የመኖሩን ያህል “ኦህዴድን የመሰለ ለኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ነፃነትና እኩልነት ሌት ተቀን ተግቶ የሚሠራ አመዛዛኝ ድርጅት”ም አለ፡፡ ጣሊያን Cosi é la vita ይላል – such(that?) is life ወይም C’est la vie ለማለት እንደ እንግሊዞቹና ፈረንሣዮቹ፡፡ አዎ፣ እኛም እንላለን – ሕይወት እንደዚህ ናት፡፡ ትናንት ዛሬ አይደለም፤ ነገም ዛሬን አትሆንም፡፡ የጨለማው ግዛት ዜጎች ነገን አያውቋትም፡፡ ስለትናንትም ደንታቸው አይደለም፡፡ ጭንቀታቸው ዛሬን ተሯሩጠው ጌታቸውን የታችኛውን ዓለም ገዢ ማስደሰት ብቻ ነው፡፡ የነዚህ ገልቱዎች ነገር ደግሞ ከሁሉ የባሰ ሆነና ዐረፈው – ያቺን የተማሪውን ደብተር ታበላሽ የነበረችዋንና በደንደሱ በኩል ቢያሳያት በስለቱ በኩል አንገቷን ሸርክታ የሞተችውን ጦጣም መሰሉኝ፡፡ ምን አስቸኮላቸው?! ይደርሱበት ነበር እኮ!

እጅግ ያፈርኩባቸው ጉዳዮች እነዚህ ናቸው፡


1ኛ በየእሥር ቤቱ ሕወሓት ወገኖቻችንን እንዴት ያሰቃይ እንደነበር የሰማሁ ሰሞን በወያኔ ብቻ ሳይሆን በሰው ልጅ አጠቃላይ የስብዕና ውርደት አዘንኩ፡፡ ፈጣሪያችን በዚያ ድርጊት እንዴት ሊያለቅስ እንደሚችልም ገመትኩ – ሰውን በመፍጠሩም ዳግም መጸጸቱ እንደማይቀር ገመትኩ፡፡(“ዋሽ ቢሉኝ እዋሻለሁ ንፋስ በወጥመድ እይዛለሁ” አለ አንዱ፡፡ ያ መሮ የተባለው የኦነግ የጦር ‹ጄኔራል‹ “ከጦራችን 95% በላይ በጫካ ነው” ማለቱን ሰማሁ ልበል? ወይ መቀደድ፡፡ ያን ሁሉ ዓመት የት ነበሩ? ማንስ እንዲህ በል አለው? ጠይቁ፡፡ካለመጠየቅ ማወቅ ይቀራል፡፡ “ይቺ ሰው ቸኮለች ልታድር ነው መሰል” አለ አንዱ – ሌላው ቀበል አደረገና “ይቺ ጎንበስ ጎንበስ ዕቃ ለማንሳት ነው፡፡” አለ አሉ፡፡ ከዕድሜው ገፋ አድርጎ ቢሰጠን ቆይተን ማየት ነው፡፡)

2ኛው ሰሞኑን በአማራ ጥላቻ ያበዱ ኦህዲዶች ሥልጣናቸውን ለማደላደልና በእግረ መንገድም ፈጣሪያቸውን ሕወሓትን ለማስደሰት በአዲስ አበባ ዙሪያ በተለይም ሰሞኑን በለገጣፎ የሚያካሂዱትን የቤት ማፍረስ ዘመቻ ስሰማ በሰው ልጅ ከንቱነት አዘንኩ፡፡ ዛሬን አምሮበት ነገን ለሚጠወልግ ሰውነት ይህን የመሰለ ለሰሚ ግራ የሆነና ለሰማይና ለምድር ፍርድ የማያመች ዕኩይ ተግባር በዚህ የሽግግር ወቅት ማከናወን ምን ያህል ዐረመኔነትና ዝቅ ሲልም ሞኝነት እንደሆነ ተረዳሁ፡፡
ይህ ድርጊት ይበልጥ የሚያመኝና ሊያስታውከኝ እየደረሰ የሚያቅለሸልሸኝ ደግሞ እያንዳንዱ ባለሥልጣን በራሱና በዘመዶቹ ስም አሥርና ሃያ ቤትና ኮንዶምንየም እንዳልያዘ እርሱ ንጹሕና ህግ አክባሪ ሆኖ እነዚህን ምሥኪኖች አማራ ሆነው በመገኘታቸው ብቻ እንዲህ ማሰቃየታቸው ሂሳቡን ስለማወራረዳቸው ቅንጣት ባልጠራጠርም ለጊዜው ግን አልዋሽም አናዶኛል፡፡ ጥንጥዬ ልራቀቅባችሁና – just by default – እንደውነቱ ከሆነ በኢትዮጵያ ህግን የሚያከብር ህገ ወጥ ነው፡፡

መንግሥት ተብዬዎቻችን ህግ በማውጣትም ያወጡትን ህግ በቀን መቶ ጊዜ በመደፍጠጥም በዓለም አንደኛ ናቸው፡፡ የሀገራችን ህግ አውጭ፣ ህግ ተርጓሚና ህግ አስፈጻሚ ሁላ ዝንጀሮና ጦጣ የሚነዳና የሚገዛ ይመስለዋል መሰለኝ ህጎቹ ሁሉ እሱን የሚመለከተው አይመስለውም፡፡ ቱባ ቱባው ባለሥልጣን ጭንቅላት የሚባል ነገር አልፈጠረበትም፡፡ አለምክንያት ተፈጥሮ፣ አለምክንያት ኑሮ በምክንያት የሚሞተው ባለሥልጣን ይበዛል፡፡ ሲፈልጉ እኮ በስልክ ሞት ያስበይኑብሃል፤ በቁራጭ ወረቀት ያሳስሩሃል፣ ያስፈቱሃል፡፡ ወንጀል ፈብርከው ያስታቅፉሃል፡፡ ሰብኣዊነት ብሎ ነገር የላቸውም- ምን አድርገን ነው እነዚህን በላዔ-ሰቦች የጣለብን ግን? የገጠመን ነገር እኮ ትልቅ ዕዳ ነው፡፡ አሁን ማን ይሙት አባዱላና ስንቱ በሙስናና በምዝበራ የናጠጠ ባለሥልጣን አዲስ አበባ ላይ በጠሚው አቢይ ዕቅፍ ውስጥ እየተሞላቀቀ እነዚህ ከዐረብ አገር ከፎቅ መወርወርና ከበረሃ ዘንዶ አምልጠው ያፈሩዋትን ትንሽ ጥሪት ማፍረስ ምን ትርጉም ሊሰጠው ይችላል? ለዘረኝነታቸው ትንሽ ልጓም ቢያበጁለት ምን አለበት? እግዚአብሔር በቶሎ ይፍረድ፡፡ የራሔልን ዕንባ ያዬ አምላከ ኢትዮጵያ ጦሩን ወደ ኢትዮጵያ  ያዝምት፤ አሜን፡፡

በመሠረቱ ህግን የማያከብር ሰው ህግን ለማስከበር ምንም ዓይነት ህጋዊም ሆነ ሞራላዊ ብቃት የለውም – አይደለም ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት የተሠራን ቤት በዶዘር ለማፍረስ፡፡ እያንዳንዳቸው ይጠየቁበታል፡፡ Not only ይጠየቁበታል Now and as of now, I think and feel the possibility of facing another REVOLUTION, for this so called Reformation is irreversibly poisoned by tribalism and is about to die. Mesmerizing discourses and sugar coated tantalizing words of PM Abiy are getting old before they even enjoy their infanthood. Poverino!

Filed in: Amharic